Get Mystery Box with random crypto!

Ayto fikrsh

የቴሌግራም ቻናል አርማ ayto_fkrshe — Ayto fikrsh A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ayto_fkrshe — Ayto fikrsh
የሰርጥ አድራሻ: @ayto_fkrshe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 857
የሰርጥ መግለጫ

♔ስለ ፍቅርብቻ የሚወራበት ቻናል ♔
┈┈┈❀♡❀┈┈┈
☞የፍቅር ግጥም ✎
💝💝💝💝💝
☞የፍቅር ጥቅስ ♧♡∕
💝💝💝💝💝
☞የፍቅር አባባሎች∰
💝💝💝💝💝
☞የፍቅር ሙዚቃዎች ♪
💝💝💝💝💝
☞ከመጽሐፍ የተወሰዱ ታሪኮች✄
💝💝💝💝💝
♡የራስ ታሪክን ማካፈል♡
ለበለጠ መረጃ ያነጋግሩኝ:
💌 @aytofkrsh 💌

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-28 19:46:49 ┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አምስት ❲➄❳
╰───── • ❊ • ─────╯

'ሰአቱን ሳየዉ ገና ከምሽቱ አንድ ሰአት ነዉ ብቻ ሄጄ ሳሎናቸዉ ተቀመጥኩ ተመኒም ተከትላኝ ተቀመጠችና ማልቀስ ጀመረች ግራ ተጋብቼ
<<እረ እህት ተመኒ አታልቅሺ ምን ሆነሽ ነዉ ደሞ የምታለቅሺዉ
<አይ ምንም ግን ዛሬ የምር በጣም ነዉ ደስ ያለኝ ለቤታችን የሚጨነቅ ወንድም ያገኘዉ ያህል ነዉ የተደሰትኩት
<<ቆይ እዚ ትልቅ ቤት ዉስጥ አንቺና እሷ ብቻ ናቹ የምትኖሩት
<አዎ
<<ሌላ የቤተሰብ አባል የላቹሁምንዴ
<አባቴ ዉጪ ነዉ የሚኖረዉ በአመት አንዴ ይመጣና ይሄዳል እናት ግን የለንም ከሶስት አመት በፊት ነበር ወደ አኼራ የሄደችዉ እናም አባቴ ሁሌም ለኛ ሲል ይለፋል
<<ሀኒስ ከበፊትም ነዉ ህመሟ
<አይደለም እናታችን ስትሞት በድንጋጤ ነዉ እንደዚሆና የቀረችዉ ከዛም ለትምርትም አትላክም ካለኔ ወዴትም አትወጣም እኔ አባቴ ከፍቶ የተወዉ ሱቅ አለ እየተማርኩ ሱቁንም አስተዳድረዋለሁ
<<ማሻአላህ ደስ ይላል ግን ስንት አመትሽ ነዉ
<21
<<ይገርማል እህትሽ ግን የምር ታሳዝናለች በጣም የእህትነት ስሜት ያላት ልጅ ናት እኔ ከማንም ጋር እንደዚ ተጫዉቼ አላዉቅም እሷ ጋር ስቀርብ ግን ክፋት አለማወቋ የምር ደስተኛ አድርጋኛለች
<ሀኒ ከህመሟ ቡሀላ በጣም ከባድ ሁኔታ ዉስጥ ነበረች ታዉቃለህ ሁሉንም ነገር እረስታ በሽተኛ ካሏት በጣም ነዉ የምታለቅሰዉ ብቻ አልሀምዱሊላህ አሁን ወንድም አጊንታ ተደስታለች
<<ኦዉ ደስ ይላ ወንድምም አላቹ
<አይ አንተን አገኘች ለማለት ፈልጌ ነዉ እኔ ምልህ ግን አንድ ነገር መጠየቅ እችላለሁ
<<ይቻላል ጠይቂኝ
<ለምንድ ነዉ የምትሰርቀዉ ሰርቀህስ ለምንድ ነዉ የምትበላዉ ስርቆትኮ በጣም መጥፎ ነገር ነዉ ደሞ የሰዉ ሀቅ መዉሰድ ጥቅሙ ምንድ ነዉ ብላ ሳትጨርስ ተነስቼ በጥፊ መታዋት እሷም ደነገጠች ምን አላለችኝም አላለቀሰችም ግን ደሞ አይኗ በጣም ቀልቷል እናም አይኗን ማየት እየፈራሁ ቀና ስል ተመኒ ነስር ከአፍንጫዋ ይወርድ ጀመር ግራ ገባኝ ለምን መታዋት እስከዛሬ ሴት ልጅ ላይ እጄን አንስቼ አላዉቅም ነበር ዛሬ በሷ ላን ግን ለምን ብዬ እምባዬን መቆጣር አቅቶኝ እሷን ለመታዋት እኔ ቆሜ ማልቀስ ጀመር ተመኒ እንደሚያዉቀኝ ሰዉ ሆና እንባዬን በሶፍት አስቀምጣኝ ትጠርግልኝ ጀመር የምር የሆነ ነገር ተሰማኝ ተመኒ ቆይ ለምንድ ነዉ በስስት እያየችኝ የሷን ነስር ሳልጠርግላት የኔን ዉሃ የሆነ እንባ የምትጠርግልኝ ብዬ አይኔን መስበር ጀመርኩ አዎ መስበርም አለብኝ የምር በሷ ዉስጥ የሆነ የማላዉቀዉ ነገር ይታየኝ ጀመር ምንም ሳታወራኝ አቅፋኝ ፀጉሬን እንደ እናት መደባበስ ጀመረች እኔም እዛዉ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ያዘኝ.......................

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ስድስት ❲➅❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
167 views✿Smart girl , 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:44:33 ┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አራት ❲➃❳
╰───── • ❊ • ─────╯

""ጊቢዉ ጋር ስንደርስ አበሸር ፈታ በል ብላኝ በቁልፉ ከፍታ ይዛኝ ወደ ዉስጥ ገባች ነገር ግን ወደዉስጥ ስገባ ሀኒ ቁጭ ብላ እየጠበቀችኝ ነዉ መሰለኝ መጥታ ተጠመጠመችብኝ ግራ ተጋባሁ ለኔ ለምንድ ነዉ የዚህን ያህል የምትንሰፈሰፈዉ ነዉ ወይስ በሽታዋ ነዉ እያልኩ ግንባሯን ስሜ እንደ ታናሽ እህቴ አጠገቤ አስቀምጬ አጫዉታት ጀመር ተመኒ በኔና በሀናን ሁኔታ ፈገግ ብላ ወደ ዉስጥ እንድንገባ ጋበዘችን እኔም ሀናንን ያዣት ገባሁ እናም ተመኒ ምግብ አስቀርባ መብላት ጀምረን እኔ ከሀናን ጋር እየተያየዉ በመሀል ወደ ተመኒ ስዞር እሷ አይኗን ትሰብራለች እኔም ምግብ በልተን እስክንጨርስ ምንም ሳላወራ አሁን ብሩን ስጪኝና ልሂድ ብዬ አልኳት እሷም ተነስታ ተከተለኝ አለችኝ እኔም እሺ ብዬ ሀኒን ትቼ ወደ ፎቅ ላይ ተከተልኳት ከአንድ ክፍል ገባች እኔም ተከትያት ገባሁ እሷም ወደኔ ሳታይ ቼክ አዉጥታ መፃፍ ጀመረች ግራ ገባኝ ለሀምሳ ሺ ብር ቼክ ለምን ታባክኚያለሽ ብዬ ፈገግ አልኩና ልወጣ ስል
<ስምህን ግን አልነገርከኝም
<<ሃሚ እባላለሁ
<እኔ ደሞ ተመኒ እባላለሁ ግን ስለሁሉም በጣም ነዉ የማመሰግነዉ
<<ለምንድ ነዉ የምታመሰግኚኝ ዘረፍኩሽ እንጂኮ አረዳሁሽም ስለዚ መመስገን አያስፈልገኝምኮ
<ሲጀመር እኔ አዉፍ ብዬ ሀለዉ ለወደፊትህ ስትቸገር ግን ወደኔ ና ከሌሎች ግን ምንም ቢሆን እንዳትሰርቅ ስትቸገር ወደኔ ና ብላ አንድ የተጠቀለለ መፅሀፍ በእጄ ሰጠችኝ ምንድ ነዉ ስላት ቁረአን ነዉ አለችኝ እኔም በየዋህነቷ እየተገረምኩ ወደ ቤት ተመለስኩ

"""ሳሪ ግን ለምንድ ነዉ የወጣሽዉ ቆይ ያምሻልንዴ ደሞ ሃሚ ሰምቶ ተበሳጭቷል ቆይ እሱስ አያሳዝንሽምንዴ የእናንተን ሂወት ለመመለስ ብሎ ይለፋል አንቺ ደሞ ጭራሽ ለሰዉ ቦታም የለሽም
<ሰኢዲ እኔ ቦታ ስለሌለኝኮ አይደለም ምግብኮ ተራብን ደሞም እኔ ሴት ነኝ ሰርቼ ማግኘት ስላለብኝ ነዉ ደሞ ትላንትና ሃሚ መጥቶ ነዉ የሄደዉ
<<እና ምን አለሽ
<አስፈራርቶኝ ነዉ የሄደዉ
<<እሱኮ ለኛ ብሎ ሌብነት ጀምሯል እኛ ግን ለሱ ምንም እያሰብን አይደለም አንቺም እየተረዳሽዉ አይደለም ከሱ በበለጠ ደሞ የአሊ ነገር ነዉ ልታስቢ የሚገባ እህቴ
<እሺ ሰኢዲ አሁን ግን ለእታባ መታከሚያ የምናገኝ ይመስልሀል
<<ኢንሻአላህ እናገኛለን ደሞም ሃሚ ያግዘናል
<ሰኢዲ የሆነ ነገር ልንገርህ ግን ሚስጥር ነዉ
<<አብሽሪ እህቴ የአንቺን አይብኮ እስከዛሬም እየጠበኩ ነዉ እና አሁን ለምን ሚስጥርሽን አባክነዋለሁ
<ሃሚንኮ እወደዋለሁ
<<እህቴ አላት ይዉደድሽ ግን መዉደድ ጥሩ ነዉ እና ሰኢድ ይጠላዋል አሉሽ
<አይ ሰኢዲ እኔ ምወደዉ ማለቴ አፍቅሬዋለሁ
<<ሳሪ ሁለተኛ እንዳትደግሚዉ ይሄን ሀሳብሽን ሃሚ ቢሰማ እዚ ቤት አይረግጥልሽም እሺ እሱ እንዳያዉቅ እሺ ሳሪ
<እሺ ግን ባጣዉስ
<<እረ አንቺ የአሊ ሚስት ነዉ መሆን የምትችይዉ ገባሽ አለበለዚያ ሃሚን ለእይታም አታገኚዉም
<እሺ ወንድሜ ብዬ ዝም አልኩ አዎ ዝምታ ነዉ የሚሻለኝ ሃሚን በጣም እንደማፈቅረዉ ከኔ ዉጪ ይህዉ ለወንድሜ ብቻ ነዉ የነገርኩት።

""ቤት ተመልሼ ወደ ወንድሜ ጋር ስገባ ተኝቶ ነበር እናም ምንም ሳልል ወደ ራሴ ክፍል ሄጄ ለመተኛት ስሞክር እንቅልፍ እምቢ አለኝ ተነስቼ ቁረአን ልቀራም ፈልጌ ነበር ግን ብዙም መቅራት አልቻልኩም ትዝ ሲለኝ ለካ ተመኒ የሰጠችኝን ቼክ አልከፈትኩትም ነበር እረ ለማየት ጓጉቼ ስከፍተዉ ግን በጣም ደነገጥኩ ተመኒ የሁለት ሚሊየን አምስት መቶሺብር ቼክ ነበር የሰጠችኝ ደነገጥኩ ልጅቷ እያበደች መሆን አለበት ብዬ በሀኒ ስልክ ደወልኩላት
<<ሄለዉ
<አሰላም አለይኩም እንዴት ነህ ሰላም ገባህ
<<አዎ ሰላም ገብቻለሁ ግን አይተሽዉ ነዉ
<ምኑን
<<ቼኩን
<አዎ አይቼዉ ነዉ ምነዉ አነሰንዴ
<<እረ በዛ ግን በጣም ነዉ የማመሰግነዉ
<አብሽር ምስጋና አያስፈልገዉም ግን ከተቻለህ ከሀኒ አትራቅ
<<እረ አልርቅም
<እህቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ እንደዚ ደስተኛ ስትሆን ያየዋት ለእህቴ ብዙ ዋጋ ከፍዬባታለሁ ብሩን የሰጠሁህና በምንም ሁኔታ ያልወነጀልኩህ እዚ ስትመጣ እህቴን ፈገግ ስለምታረግልኝ ነዉ እናም ሁሌም ብትመጣ ደስ ይለኛል ከቻልክ አሁንም ብትመጣ ደስ ይለኛል
<<እረ የሆነ ጉዳይ ጨራርሼ መጣለሁ ብዬ በቀጥታ ወደ ሰኢድ ጋር ሄጄ ሳሪን ሰላም ካልኩኝ ቡሀላ እታባ ጋር ገብቼ አይቻት ሰኢዲን ይዤዉ ወጣሁ ና ሄደን ብሩን ወደ ሰኢድ አካዉን አዙረን ለህክምና የሚያስፈልገዉን ወጪና ለቤት የሚያስፈልገዉን ወጪ እንዲሸፍንለት አስተካክዬ ወደነ ተመኒ ቤት ሄድኩኝ ገና ከመግባቴ ሀናን ዉጪ ጭቃ እያቦካች አገኘዋት እኔም ተቀላቅዬ ማቡካት ጀመርኩ ሀኒ ጓደኛዋ ሆኜ ስለማቦካ በደስታ እየተፍለቀለቀች ነዉ። ተመኒ ግን አልወጣችም እናም ሀኒ ሀናን እያለች ስትወጣ አብረን ጭቃ እያቦካን ነበር ደነገጠች ይባስ ብላ ሳቋን መቆጣጠር ሲከብዳት ተመልሳ ገብታ ሳቋን ጨርሳ ወጣችና አጠገቤ ቆመች እኔም እንድትቀላቀለን ጋብዣት ሶስታችንም እያቦካን እንደ ህፃን እንጫወት ጀመር ሀኒ እንቅልፏ ሲመጣ እጇንና እግሯን አጣጥቤ ተሸክሜ ተመኒ የምትተኛበትን አሳይታኝ ወስጄ አስተኛዋት የእዉነት ሀኒ በጣም የምታሳዝን ልጅ ናት።
'ሰአቱን ሳየዉ ገና ከምሽቱ አንድ ሰአት ነዉ ብቻ ሄጄ ሳሎናቸዉ ተቀመጥኩ ተመኒም ተከትላኝ ተቀመጠችና ማልቀስ ጀመረች.............
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አምስት ❲➄❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝
.↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.
179 views✿Smart girl , 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 20:46:17 ┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሶስት ❲➂❳
╰───── • ❊ • ─────╯

"" ከሰፈሩ ስደርስ ሳሪን አገኘዋት ምንም ሳልላት ከዛሬ ወዲህ ስራ ብለሽ ብትወጪ አለቅሽም እሺ ብያት ወደ መስጂድ ተመለስኩ ሁሌም የኔ መሸሸጊያ መስጂድ ነዉ ሲከፋኝም ስደሰትም ወደ አሏህ ነዉ ከዛም ወደ ወንድሜ ሰኢድና ወደ ወንድሜ አሊ ነዉ አሊ ማለት በጣም የምወደዉ ታላቅ ወንድሜ ነዉ አሁን በእርግጥ መንቀሳቀስ ስለማይችል በዊልቸር ከመኝታ ክፍሉ አይወጣም ያአሏህ እሱን ወደ ሙሉ አፊያ እንዲመልስልኝ እማፀነዋለሁ

"""ዛሬ ለካ እሮብ ነዉ ማክሰኞ መጣለዉ ብያት ትምሩ ሲያወዛግበኝ ሳልሄድ እሮብ ደረሰ በቀጥታ እጄ ላይ ያለዉን ገንዘብ ይዤ ወደ ሱፐር ማርኬት ሄድኩና በጣም ብዙ ቸኮሌት ገዝቼ ዘመድ የምጠይቅ ይመስል ባለፈዉ ጅልባብ ከሰረኩበት ግቢ በር ደርሼ ቆምኩኝና አንኳኳሁ እሚገርመዉ የከፈተችልኝ ሰራተኛ ናት መሰለኝ ተኮሳትራ አቤት ብላ ማንን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ እኔም ባለፈዉ ስትናገር ስለሰማዋት
<< ይሄ የነ ተመኒ ቤት ነዉ አይደል
<አዎ ምን ነበር
<<ከቻልሽ እሷን እንድታገናኚኝ ፈልጌ ነበር ስላት ወደ ዉስጥ ገብተህ ጠብቃት ብላ ጋበዘችኝ ወደ ዉስጥ ስገባ ጊቢ ዉስጥ የተሰጣ ልብስ የለም በጣም ተናድጄ
<<ልብሶቹስ
<የምን ልብስ
<<ትዝ ሲለኝ ለካ የተናገረችኝ ሌላ ሴትናት እናም አይ ስልክ የማወራዉን እየተለማመድኩ ነዉ በጣም ይቅርታ ብዬ እሷን ተከትዬ ሳሎን ገባሁ እናም ሰራተኛዋ ጥላኝ ሄደች በአይኔ ሚሰረቅ ስፈልግ ከመጅሊሱ በስተቀር ምንም የሚሰረቅ ነገር የሌለበት ክፍል ነበር የገባሁት ብቻ መቀመጥ አስጠልቶኝ ልወጣ ስል የባለፈዋን ልጅ አገኘዋት መጣችና ተጠመጠመችብኝ እናም እንደምታቀኝ ሆና ታወራኝ ጀመር
<<ቆይ ለፍላፊት ስምሽ ግን ማነዉ
<ሀናን
<<ስንት አመትሽ ነዉ
<15 ምነዉ
<<ባለፈዉ ልብስ ይሰጣል ብለሽኝ አልነበር
<ማነዉ ሚሰጠዉ
<<አይደለም ታጥቦ ይሰጣል ብለሽኝ አልነበር
<አዎ ዛሬ ማሽኑ ስለተሰራ በሱ ነዉ ተመኒ አጥባ የሄደችዉ
<<እና ዝም ብለሽ ታስለፊኛለሽንዴ ብዬ ቸኮሌቱን ሰጥቻት ልወጣ ስል
<የተመኒ ክፍልኮ ልብስ በሽ ነዉ ከፈለክ ገብተህ ዉሰድ
<<የቅድሟ ልጅ ካየችኝስ
<እኔ አይንሽን ጨፍኚ እላታለሁ
<<አንቺ ያምሻልንዴ ብዬ ስጮህባት አለቀሰች በቃ አታልቅሺ ብያት አባበልኳትና ና ተመኒ ከመጣች ስለምትቆጣ ከሷ ክፍል ብዙ ነገር ይዘህ ሂድ ብላኝ ከሆነ ሚያምር ክፍል አስገባችኝ ኦዉ ማሻአላህ ስል ሀናን አይታ ሳቀች እኔ ምልሽ ሀኒ ቆይ ስንተኛ ክፍል ነሽ
<አልማርምኮ
<<እና ዝም ብለሽ ቁጭ
<አይ ተመኒ ስትመጣ ይዛኝ ትሄዳለች
<<ወዴት
<ወደ ጓደኞቼ
<<እሺ ሀናን ስልክ አለሽ
<አለኝ ግን አልደዉልም
<<ለምን
<ተመኒ ትቆጣለች
<<እሺ በቃ እኔ ምሰርቀዉን ልሰብስብ ብዬ ያገኘዉትን በቦርሳ ሰርቄ ማንም እንዳያየኝ ተጠንቅቄ ከግቢ ወጣሁ እናም ሰኢድ ጋር አስቀምጬ የምሸጥበትን ቦታ እያሰብኩ የሀናንን ስልክ ስለማትጠቀምበት ወስጄዉ ነበር ለካ ለጓደኛዬም አላዘንኩም ጉድኮ ነዉ ግን ተመኒ ማናት ምንድናት ግራ ተጋብቼ ለራሴ እያሰብኩ ሰኢድን ነገርኩት እሱም ግራ ተጋብቶ አይ ተዉ ልብሶቹንና የሰረከዉን ቦርሳ እንፈትሸዉ ብሎኝ መፈተሽ ጀመርን በዚ መሀል ከአንድ ቦርሳዉስጥ የሀናንን አዲስ ፓስፖርትና የህክምና ወረቀቶችን አገኘን ግራ ተጋብቼ ሳነበዉ ሀናን ለካ ጤነኛ ልጅ አይደለችም አይምሮዋ ከሀገር ዉስጥ አልፎ እስከ ዉጪ ድረስ ያስኬዳል በጣም ደነገጥኩ የልጅቷን ሁኔታ አስደነገጠኝ ብቻ ስልኳን ስፈትሸዉ ሀናን ከእህቷ ጋር አብራ የተነሳችዉ ፎቶ አለ ብቻ በግምት ነዉ እህቷ ያልኩት እናም በጣም ያምራሉ ብቻ ፎቶዋን እየፈተሽኩ ሳለ ላይ አንድ ስልክ ተደወለ ቱና ይላል ዘጋሁት አሁንም በድጋሚ ተደወለ ዘጋሁት ብቻ እየተደወለ አራት ጊዜ ሲደወል አንስቼ ዝም አልኩ በለስላሳ ድምፅ
<ሌባዉ
<<እ አቤት
<በፈጠረህ ሁሉንም ዉሰደዉና የእህቴን የሄክምና ወረቀትና ፓስፖርቷን ብቻ ስጠኝ እኔ የፈለከዉን ገንዘብ እሰጥሀለዉ
<<ድምጿ በጣም ያምራል እናም እሺ ስንት ብር ትሰጪኛለሽ
<የጠየከኝን
<<እኔ እህትሽን እንድትሰጪኝ ነዉ የምፈልገዉ
<ለምን
<<ለስራዬ ስለምታስፈልገኝ ብዬ ሳኩባት አዎ እስቃለሁ ምክንያቱም ሀናን ስለረዳችኝ እንጂ ለበሽታዋ አልጨነቅም ነበር የኔ ጫወታ ከገንዘብ ጋር ነዉ። እሺ ግን አንቺን ማን ልበል
<ተመኒ እባላለሁ የሀናን ታላቅና ብቸኛ እህቷ ነኝ
<<በቃ ተመኒ ነገ 50ሺ ብር ይዘሽ የምጠብቅሽ ቦታ ነይ በዛዉም ሀኒን ይዘሻት ነይ
<እሺ ግን ወረቀቱን አደራ
<<እሺ ብያት ቦታዉንና ሰአቱን ነግሬአት ስልኩ ዘጋሁት

""ባልኳትና በነገርኳት ቦታ ላይ አንዲት ሴት ቆማለች ሲመስለኝ ተመኒ ናት ግራ ተጋብቼ ልታሲዘኝ ነዉዴ ብዬ ተደብቄ ደወልኩላት እሷም እያለቀሰች እባክህ በአላህ ይሁንብህ ቶሎ በል አለችኝ እያወራዋት ስልኩን ሳልዘጋዉ ወደ ሷ ቀረብኩ
<አንተ ነህ ሌባዉ
<<አዎ እኔዉ ነኝ ሌባዉ ምነዉ የስራ ልምድ ካላሳየዉሽ አታምኚኝም እንዴ ብዬ ፈገግ አልኩ እሷ እሺ ና ገንዘቡን ልሰጥህ ብላኝ ወደቤት ይዛኝ መሄድ ጀመረች እሚገርመዉ አንዴ አይታኝ ነበር ያቀረቀረችዉ ግራ ተጋብቼ አምኜ ተከተልኳት ጊቢዉ ጋር ስንደርስ አበሸር ፈታ በል ብላኝ በቁልፉ ከፍታ ይዛኝ ወደ ዉስጥ ገባች ነገር ግን ወደዉስጥ ስገባ.................
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አራት ❲➃❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝
.↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.
195 views✿Smart girl , 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 20:06:26 ┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሁለት ❲➁❳
╰───── • ❊ • ─────╯

"" አልሀምዱሊላህ ፈጣሪዬን ሳመሰግንኮ ብዙ ነዉ የሚሰጠኝ አላህዬ ቸኩል በኔ በኩል ብዬ ለምኜ ወደ መስጂድ ሄድኩኝ መስጂድም ከመግባቴ ወንድሜ አንተ የት ገበርክ ልጆቹ ደርስ ገብተዉ ብሎ ጮህብኝ እኔም እረ አለሁ ብዬ እንዳይመታኝ በቶሎ ኡዱ አድርጌ ወደ ዉስጥ ገባሁ አንዱ ጓደኛዬ ጠርቶኝ ወደሱ ሄድኩኝ
<የት ሄደህ ነዉ የጠፋህዉ
<<እረ አለሁ ምነዉ ችግር አለንዴ
<አይ የለም ግን
<<ግን ምንድ ነዉ አቦ አታስጨንቀኝ ኡፏ ከተናገርክ ተናገር ብዬ ስጮህበት የመሰሰጂዱ ጀመአዎች በሙሉ ትኩረታቸዉን ወደኔ አደረጉ እኔም ድምፄን ቀንሼ ወጣሁ ጓደኛዬም ተከትሎኝ ወጣ ወንድሜ በዚህን ጊዜ ወጣና ቆይ ጉርምሰሰና ነዉ እንደዚ የሚያረግህ ብሎኝ አጠገቤ በፍጥነት መጥቶ በጥፊ ከደነብኝ ብቻ ምንም ሳልለዉ ከመስጂዱ ጊቢ ለቅቄ ወጣሁ በኔ መጨከን የማይችለዉ ጓደኛዬ መጣ
<ሃሚ እረ ሃሚ ስማኝ እንጂ
<<እ ምን ሆንክ የጎደለ ነገር አለ
<የለም ግን ሳሪ መቼ ነዉ ሃሚ መጥቶ የሚዘይረኝ እያለችኝ ነወ
<<መቼስ በአሁን ሰአት ወደሷ ጋር መሄድ እንደማልችል ታዉቃለሀአ
<አዎ አዉቃለሁ ግን ማታ ስራ ወጥታ ነዉ የተመለሰችዉ
<<ሰኢድ እየዋሸህኝ ነዋ
<እረ ሃሚዬ በፍፁም አልዋሽህም ምነዉ ተጠራጠርከኝንዴ አይ ተወዉ በቃ ብዬ የሰራዉትን ብዙም ባይባል ግን ለዛሬ የሚሆን አስቢዛ ግዛ እሺ ብዬ አስጠንቅቄ ሰጠዉት
ሰኢድም ደስ እያለዉ ግን ከየት አመጣህ አለኝ
<<እሱ አንተን አያገባህም ዝም ብለህ ተቀበል ብዬ ወደ ስራዬ ለመሄድ አስቤ ግን የዛሬዉ ሁኔታዬን ለሰኢድ እየነገርኩት ወደ ሰፈር እሸኘዉ ጀመር ሰኢዲም ገርሞት አፉን ከፍቶ ሰማኝ ያዉ እሱ እንደምሰርቅ ያዉቃል ግን ተዉ ሲለኝ ስለማልሰማዉ ደሞ የግድ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ቢደብረዉም ይቀበለኛል አለበለዚያ ግን እኔ አኮርፈዋለዉ ስለዚ ሳይወድ በግዱ ይሰማኛል
<እኔ ምልህ ሃሚዬ ልጅቷ ግን ጤነኛ ናትንዴ ስትሰርቃት ዝም የምትልህ ነዉ ወይስ ወዳህ ነዉ
<<በይ ሰያ አፍሽን አታስረዝሚዉ አንቺ ጩጬ በይ እኔ ወደ ቤት ልግባ ብዬዉ እሱን የተወሰነ ሰፈር ካስገባሁት ቡሀላ በቀጥታ ወደ ቤት ገባሁ እናም አባት ተብዬዉ ከደጁ ዘፍ ብሎ ተቀምጧል
-ጎሮምሳዉ ቆይ በዚ ሰአት ከየት ነዉ
<<ከሰኢድ ጋር ነበርኩ
-የዚህን ወፍ ዘራሽና ድሀ መናጢ ድሀ ስም አትጥራብኝ ተዉ ከሱ ጋር አትሁን ብልህ አልሰማ አልከኛአ
<<እሱ ያለዉን ሀብት አንተ ብታዉቅ ኖሮ ከነ ጓደኞችህ ትዘርፈዉ ነበር ብዬ እየሳኩኝ ወደ ዉስጥ ገባሁ ዉስጥ እንደ ገባሁ ግን የኔ ልጅ ብላ የኔ ዉድ እናት የሆነችዋ ሴት መጥታ ግንባሬን ሳመችኝ ኡሚዬ ስወድሽኮ ታዉቂያለሽ አንቺ የሌላ ሰዉ እንትኮ ብትሆኚ ኖሮ በቅናት እርር ብዬ አልቅ ነበር ብዬ በቶሎ ወንድሜስ ብያት ወደ ላይኛዉ ፎቅ ወጣሁ

"ወንድሜ ግን በጥሩ ሁኔታ ከዊልቸሩ ተቀምጦ መፅሀፍ እያነበበ ነበር ሳላንኳኳ በቀስታ ገብቼ ልወጣ ስል ሃሚ ተመለስ የሚል ድምፅ ሰማሁ
<<ወዬ የኔ ዉድ ወንድም ብዬ ሄጄ ግንባሩን ስሜ አጠገቡ ተቀመጥኩ ከጉልበቱ በታች ተቀምጬ እሱን ወደላይ ቀና ብዬ እየተመለከትኩት ያየህኝ አልመሰለኝም ነበር እሺ ከመጣሁ አይቀር ዛሬ ትርጉም አትነግረኝም ብዬ እየተቅለሰለስኩ አየሁት አዎ እሱ ሁል ግዜ ስመጣ ቁረአን እየተረጎመ ይነግረኛል እናም እሺ ብሎኝ ከቁዱስ ቁረአን ለማዉጣት አስቦ ሂድ ቁዱስ ቁረአን አምጣልኝ ብሎ ከመፅሀፍት መደርደሪያዉ ላይ አሳየኝና ሄጄ አመጣሁለት እሱም ድምፁን እያሳመረ ዛሬ እንኳን አጠር የሚለዉን ሱራ ነዉ የምነግርህ ብሎኝ ተስተካከለ እኔም በጉጉት እጠብቀዉ ጀመር
<አል ካፊሩን>
በላቸዉ❮❮❮እናንተ ከሓዲዎች ሆይ!
❮❮❮ያንን
የምትገዙትን (ጣዖት አሁን)
አልግገዛም።
<<<እናንተም እኔን የምግገዛዉን
(አምላክም አሁን)
ተገዢዎች አይደላቹሁም።
<<<እኔም ያንን የተገዛችሁትን
(ወደፊት)ተገዢ አይደለሁም።
<<<እናንተም እኔም የምገዛዉን
(ወደፊት)
ተገዢዎች አይደላችሁም።
<<<ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አለላችሁ።
ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ።
<ሃሚዬ ጨርሻለሁ አሁን እስቲ ስለዉሎህ ንገረኝ
<<ዉልዬ ደስ የሚል ነበር አሪፍ ወርክ ወርኬ ገና ከመከሰቴ ነዉ አንተ ጋር የመጣሁት
<እኔ ምለዉ ሃሚ ሰኢዲ አለንዴ
<<አዎ አለ
<እናቴ ቅድም ለአንዳንድ ነገር ብላኝ ገንዘብ ሰጥታኝ ነበር እና ልትሰጥልኝ ትችላለህ
<<አዎ ግን አንድ የምነግርህ ነገር አለ
<ምነዉ ሳሪ ሰላም አይደለችምንዴ
<<ቢሆን ነዋ ማታ ስራ ወጥታ የተመለሰችዉ
<ምን ሳሪ አታረገዉም ለኔኮ ቃል ገብታልኝ ነበር
<<ወንድሜ በቃ ተረጋጋ አሁን አሪፍ ስራ ከሶስት ቀን ቡሀላ ስለማገኝ መቼም አትወጣም
<ታዉቃለህ ግን ቃል ገብታልኝ ነበርኮ ብሎ ተንሰቅስቆ ማልቀስ ጀመረ የወንድሜ ነገር ስለማያስችለኝ እናቴን ጠርቼ እሷ ስታረጋጋዉ እኔ ወጣሁ ልክ ከበሩ ስደርስ ግን አባቴ ተቀምጦ አሁን ደሞ ወዴት ነዉ ሲለኝ ገላምጬዉ ወደ ሰኢድ ጋር ሄድኩኝ ልክ ከሰፈሩ ስደርስ ሳሪን አገኘዋት ምንም ሳልላት ከዛሬ ወዲህ ስራ ብለሽ ብትወጪ አለቅሽም እሺ ብያት ወደ መስጂድ ተመለስኩ......

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሶስት ❲➂❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
╭───────╯ ╰───────╮
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╰───────╮ ╭───────╯
የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል
. @Ayto_fkrshe
211 views✿Smart girl , 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 20:43:00 ┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አንድ ❲①❳
╰───── • ❊ • ─────╯

""አልሀምዱሊላህ ዛሬ ያገኘዉትማ በቃ ብዙ ነዉ ያዉ የሰረቀ ሁሉ ሌባ ነዉ ያለዉ ማነዉ ቆይ አዎ እዉነቴንኮ ነዉ እኔ አሁን ከዝርፊያ ባልተናነሰ ከሚሰሩት ባለሀብቶች ብዘርፍና ብሰርቅ ሌባ እባላለሁ ያዉ ብባልም ግን እኔ ከሌቦች ሁሉ ለየት የሚያረገኝ ሁሌ አላህን በማመስገኔ ነዉ ያዉ ከትርፋቸዉ በመካፈሌ እንጂ ሰርቄ ነዉ ብዬ አላምንም ስራ ሲጠፋና ሚዘረፍ ሲጠፋ ግን አልሀምዱሊላህ ብዬ ያገኘዉትን ልብስም ቢሆን ከሽቦ ላይ እሰርቅና እኖራለሁ ግን ለምንድ ነዉ የምትሰርቀዉ የሚለኝ ሰዉ ሳገኝ የምር ደሜን ነዉ የሚያፈሉት የሆኑ የዋህ ህዝቦች ዘርፌም ስሮጥኮ የሚመርቁኝ አሉ ያዉ አለ አይደል ሸበላ ዘራፊ ነገር ነኝ መሰለኝ አልሀምዱሊላህ ግን ለምን አልሀምዱሊላህ ትላለህም እንዳትሉኝ ምክንያቱም አሁን ስራ ስለጠፋ እያመሰገንኩ ከአንድ ጊቢ ዘዉ ብዬ ገባሁ ጊቢዉ የሀብታም ይመስላል ያዉ ደሰ እያለኝ ገብቼ ያገኘዉት የተሰጣ ጅልባብና ቀሚሶች ነበሩ አመል አይደል የያዘኝ አልሀምዱሊላህ ብዬ ይዤ ልወጣ ስል አንተ ብላ የሆነች ሴት ጠራችኝ እኔም ስራዬን አክባሪም አይደለሁ ወዬ ብዬ ዞርኩኝ
<ልብሶቼን ሰብስበህ ወዴት ነዉ
<<ልሸጠዉ ነዉ ያዉ ሳሙናሽን አይደል የሚጨርሰዉ
<ከዛንስ ምን ልታረግበት በብሩ
<<ሌላ ልብስ ገዝቼ ላመጣልሽ ነዉ
<እስቲ ወላሂ በል ብላኝ እየሳቀች ወደኔ መጣች ኢላሂዬ የዘንድሮ ሞኝ አንቺን አየሁ ስላት
<ተመኒ በዛ በከልኮ ብዙ ያሰጣችዉ አለ ብላኝ እጄን ይዛ ብዙ ልብስ የተሰጣበትን አሳየችኝ እኔም እያመሰገንኳት ግንባሯን ስሜ የቻልኩትን ይዤ ወጥቼ በር ስደርስ አባቱ አለችኝ
<<ወዬ
<በሚቀጥለዉ ስትመጣ ብዙ ልብስ አለ ቁም ሳጥን ዉስጥ አሳይሀለዉ እና ግን ቸኮሌት ይዘህልኝ ከመጣህ ነዉ የማሳይል አለችኝ
<<እሺ መቼ ነዉ ብዬ ስጠይቃት እሮብ አለችኝ ግራ ተጋብቼ ቀኑን ሳስበዉ ዛሬ ለካ ቅዳሜ ነዉ እሺ በቃ ማክሰኞ አምጥቼ እሮብ ወስዳለዉ ቤዬ ከአዲሷ የስራ ባልደረባዬ ጋር ሳልተዋወቅ ወጥቼ ሄድኩኝ ግን እየገረመችኝ ነበር ሆሆሆ ልብሶቹን ባገኘዉት ቸብችቤ ወደቤቴ ተመለስኩ አልሀምዱሊላህ ፈጣሪዬን ሳመሰግንኮ ብዙ ነዉ የሚሰጠኝ አላህዬ ቸኩል በኔ በኩል ብዬ ለምኜ ወደ መስጂድ ሄድኩኝ..............

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሁለት ❲➁❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
╭───────╯ ╰───────╮
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╰───────╮ ╭───────╯
የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል
. @Ayto_fkrshe
238 views✿Smart girl , 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 19:23:03 እንዴት ናቹልኝ ቤተሰቦቼ? በፈጣሪ ፊቃድ አዲስ ታሪክ ልንጀምርላቹ አስበናል ሁለት ታሪክ ስለሆነ ያዘጋጀነው አንዱን በመምረጥ ትተባበሩኛላቹ! 1,ተመኒ 2,ልጅነቴ
238 views✿Smart girl , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 07:24:17 እንዴት ናቹልኝ ቤተሰቦቼ?

በፈጣሪ ፊቃድ አዲስ ታሪክ ልንጀምርላቹ አስበናል ሁለት ታሪክ ስለሆነ ያዘጋጀነው አንዱን በመምረጥ ትተባበሩኛላቹ!

1,ተመኒ
2,ልጅነቴ
267 views✿Smart girl , 04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:09:44
548 views✿Smart girl , 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:09:44
490 views✿Smart girl , 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:09:44
445 views✿Smart girl , 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ