Get Mystery Box with random crypto!

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓ '. #ተመኒ '. ✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ ┗◛◛ | Ayto fikrsh

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስር ❲➉❳
╰───── • ❊ • ─────╯

"""ልበለዉ እያልኩ እያሰብኩ በመሀል ሃሚ ተመኒ ምን እንደሆንሽኮ አዉቃለሁ
<በምን አወክ
<<ነግሮኝ
<ማን ነዉ የነገረህ
<<ፊትሽ ነዋ ከፍቶኛል ብሎ ተጨንቆ አባብጧል ካላመንሽ በመስታወት መመልከት ትችያለሽ
<ሃሚዬ አትቀልድ
<<እሺ ምን እንደሆንሽ ንገሪኝ
<ደወለልኝ
<<ማነዉ የደወለዉ
<የበፊቱ ፍቅረኛዬ ደዉሎ አስፈራራኝ
<<አብሽሪ አትፍሪ እኔና አንቺኮ አንድ ለመሆን የሚቀሩን ሶስት ቀናት ናቸዉ እናም በቃ እስክንጋባ እኔ እጠብቅሻለሁ ያዉ ሰበብ ሆኜ ልልሽ ፈልጌ ነዉ ጠባቂዉ አንድ አላህ ቢሆንም እናም አሁን በይ ገብተሽ ተኚ ብያት አጠገቧ ተቀመጥኩ እሷም ገብታ ተኛች ቀናቶች ሄዱ ነጎዱ አባቷም መጥተተዉ ኒካህ አስረን አብረን ቤት አባቴ ገዝቶልን መኖር ጀመርን ሀኒም ከኛ ጋር ደስ የሚል ሂወት መኖር ጀመረች ብቻ አልሀምዱሊላህ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ቀናቶች አልፈዉ የተመኒ አባት ደዉለዉ መልስ ጠሩን አልሀምዱሊላህ ትዳራችን ደስ ከማለቱ የተነሳ የዉጪ ሰዉ ሲያየን እራሱ ይቀናብናል በነገራችን ላይ ወንድሜ ለኒካዬም አልተገኘም ደዉሎ ግን ያወራኛል አልሀምዱሊላህ ሁሌ ሲያወራኝ በቅርቡ እቀላቀልሀለዉ ይለኛል።

""መልስ ተጠርተን ከተነመኒ ቤት ከገባን ከሳምንት ቡሀላ ወደቤታችን ሳንመለስ አባቴም ጠራን አሁን አልሀምዱሊላህ ወንድሜን ተመኒም ለመተዋወቅ ጓግታ ስለነበር በመልሱ ሰበብ አስተዋዉቃታለሁ ብዬ ስንሄድ አልመጣም አሉኝ ሳሪና አሊም አብረዉ ሆነዋል ሰኢድ ደሞ የኔ ሚዜ ነበር አልሀምዱሊላህ ሁሉም ነገር ደስ ይል ነበር ወንድሜም ደዉሎ ባለመኖሩ ከባድ ይቅርታ ጠየቀንና በቃ ሲመጣ እንደሚተዋወቃት ነግሮኝ ቀናቶች አለፉ እኛም ወደቤታችን ተመልሰን መኖራችንን ቀጠልን ተመኒም አረገዘች አልሀምዱሊላህ በቃ እኔም በጣም ተደሰትኩኝ ሀኒም ትምርት ለመጀመር መዘጋጀት ጀመረች አልሀምዱሊላህ አንድ ቀን ግን አምሽቼ ወደቤት ገባሁ ሚስቴም የሶስት ወር እርጉዝ ስለነበረች ኬክ አምሮኛል ብላ ስትለኝ እኔም በቃ ገዝቼ መጣሁ ብዬ ወደ ዉጪ ወጣሁ ከዋላዬ የሆነ የሚከብደኝ ነገር አለ።

"""ሃሚ አቶ ሃሚ ተነስ የሚል ድምፅ ይሰማኛል አይኔን በደንብ ስገልጥ ነጭ ጋወን የለበሰ ሰዉዬ ነዉ ትልቅ ሰዉ ነዉ ሃሚ አለኝና አቤት ስለዉ ወደዉጪ ወጣ በቀጥታ አባቴ ወደ ተኛሁበት ገባና መጥቶ አልሀምዱሊላህ ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ያለቅስ ጀመር ምን ሆኜ ነዉ እዚ የመጣሁት ስለዉ ጥሎኝ ወጣ ሁሉም ለምጠይቃቸዉ ጥያቄ መልስ ሳይሰጡኝ እያለቀሱ ይወጣሉ በስተመጨረሻም ሰኢዲ መጣ እሱም እያየኝ ካለቀሰ ቡሀላ ሰኢዲ ተመኒና ሀኒ የት ሄደዉ ነዉ ያልመጡት ኬክ ብላኝኮ እንደወጣሁ ወደሷ አልተመለስኩም ብዬስጠይቀዉ የባሰ እያለቀሰ ወጣ ያረቢ ሰዎቹ ያማቸዋልንዴ ብዬ ምንም ነገር መጠየቅ ተዉኩኝ ቀስ በቀስ እያገገምኩ ስመጣ መጀመሪያ በዊልቸር ከዛም መንቀሳቀስ ስጀምር በእግሬ ወክ አረግ ጀመርኩ እናም ግን ተመኒ አለመምጣቷ አናደደኝ እንዴት አንድ ቀን ሙሉ ወጥቼ ስቆይ ፍለጋ እንኳን አትወጣምእንዴ ብዬ ፍለጋ ተነሳሁ አዎ ሄጄ መፈለግ አለብኝ ብዬ ወደ ቤታችን ሄጄ አንኳኳሁ የከፈተልኝ ግኖ ወንድ ነበር ተመኒ ብዬ ስጠይቀዉ እንደማያዉቃትና
አንዲት ሴት እንደሸጠችለት ነግሮኝ በሩን ዘጋዉ እንዴ በቃ ተመኒ ከነ ልጄ በአንድ ቀን ካደችኝ ማለት ነዉ ቆይ ያያለችኝ ፍቅረኛዋ ሲመጣ ወደሱ ሄዳ ነዋ

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስራ_አንድ ❲⓫❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝