Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሰችን? የድሮዋ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ሃይማኖተኛ የነበረች | ፋሬስ Fєℓℓσωσѕнιρ

ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሰችን?

የድሮዋ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ሃይማኖተኛ የነበረች በሕይወቷ ከሞተላት ጌታ ጋር የግል ትውውቅ ያልነበራት አህት ነበረች። አሁን የድሮዋ ሃይማኖተኛ የነበረችው ዘርፌ ከክርሰቶስ ጋር ሞታ አሁን ክርስቶስ በእርሷ ውስጥ የሆነላት እርሷም በክርስቶስ ውስጥ የሆነች ዘርፌ ናት ያለችው።
እኔ አሁን ካለሁበት ከፍታ መሬት ወርጄ ስለሃይማኖት ሊያወራ የሚያስችል ማንነት የለኝም። እኔ የተጠራሁት ስለተገለጠው ሕይወት ልናገር ላወራ እንጂ ሕይወት ሰለሌለበት ተቋም በመናገር ጊዜ ጊዜ እንዳባክን አይደለም። እኔ አሁንም ላሳውቅ የምወደው የጠራኝና የመረጠኝ ጌታ ኢየሱስ ነው። ምንም እንኳ በቅዱሳን ሕበረት ውስጥ በስጋ ብታዩኝም አሁን ያለሁት በመንፈሴ መድኅኔ በሆነው በክርስቶስ ውስጥ ነኝ ስለማይረባ ስለማይጠቅም ነገር እያወራሁ አልኖርም ወደ ሕይወት ራስ ወደ ታላቁ ልዑል ነው የተጠራሁት። በሕይወቴ ግን የጠተካፈልኩትን ሕይወት በመግለጥ መኖር የእኔ ሃላፊነት ነው።

ተጻፈ በዘርፌ ከበደ
@Asasafaresfellow
@Asasafaresfellow