Get Mystery Box with random crypto!

የዘመሪት አዲስ አለም አሰፋ መልእክት ----- 'ወንጌል ንፁህ ነው' ደግሞም ቅዱስ ነዉ። በእርሱ | ፋሬስ Fєℓℓσωσѕнιρ

የዘመሪት አዲስ አለም አሰፋ መልእክት
-----
"ወንጌል ንፁህ ነው" ደግሞም ቅዱስ ነዉ። በእርሱ ወደ ንፅህናውና ወደ ቅድስናው እለት እለት የሚያድጉ ሰዎች.... ንፅህናውን እየነፁበት.... ቅድስናውን ደግሞ እየተቀደሱበት.... እየሱስ እስኪመጣ ወይ ደግሞ እነሱ ወደ ጌታ እስኪሄዱ ድረስ በፅድቅና እራስን በማስገዛት ቀን በቀን የመስቀሉን ሸክም የሚሸከሙበት ከራስ ተኮር የሂወት አዙሪት ተላቀው የኢየሱስን የህይወት መንገድ በኑሮአቸው የሚለማመዱበት ቀጭን መንገድ ነው። ማንም እየተነሳ በፈለገው መንገድ ሲሳካለት የሚከተለው ሳይሆንለት የሚተወዉ የሚለዋውጠው አይደለም ይልቁንስ እየሱስ ሞትን በመስቀል ላይ የቀጣበት በመስቀሉ ደም ሰላም ያደረገበት ሀጢያታችንን በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ ያስወገደበት ዉድና ውድ ደሙን ያፈሰሰበት "የክቡር ክቡር" አጀንዳ ነው ወገኖቼ....እንግዲ እርኩሱም ይርከስ አመፀኛውም ያምፅ። ለበጉ እራት የግብዣ ጥሪ የደረሰው አንድ አማኝ ካለ ግን እራሱን በዚህ ንፁህ ወንጌል ይፈትሽ!!! በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድገህ ከኔ የሰማኸውን "ጤናማ ቃል" ምሳሌ ያዝ መልካሙን አደራ በኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። 2ኛ ጢሞ 1-13-14 ተባረኩልኝ !!!
@Asasafaresfellow