Get Mystery Box with random crypto!

የህይወት ምልከታ በአንድ ቀዝቃዛና ብርዳማ የክረምት ወቅት ሙቀት ለጋሽ ልብሶችን ደራርቦ በመልበ | አርጋኖን ስነ-ግጥም ና ጭውውት ..On.Tg

የህይወት ምልከታ

በአንድ ቀዝቃዛና ብርዳማ የክረምት ወቅት ሙቀት ለጋሽ ልብሶችን ደራርቦ በመልበስ በመንገድ ላይ የሚሄድ ሰው #ሙላህ ነስሩዲን አንዲት ሸሚዝ ብቻ ለብሶ ሲሄድ ተመልክቶ በሁኔታው ስለተደነቀ እንዲህ ሲል ጠየቀው ፦

<<ሙላህ! እኔ ይሄን ሁሉ ልብስ ደራርቤ ለብሼ እንኳን ብርዱን አልቻልኩም ፡፡አንተ ግን በዚህች ሸሚዝ ብቻ ጎዳናው ላይ ስትሄድ ትንሽ እንኳን የመብረድ ስሜት አይታይብህም ? >> ሲል ጠየቀው

ናስሩዲንም ፦ <<አየህ! አንተ ብዙ ልብሶች አሉህ ። እናም ብርድን የመቋቋም ብቃትህ ተወስዷል ። እኔ ደግሞ ከዚህች ሸሚዝ ሌላ የምለብሰው የለኝምና የብርድ ስሜት ቅንጦት ሆኖ ከውስጤ ጠፍቷል >> በማለት መንገዱን ቀጠለ ።
ለዚህ ነው እውነት ለሁላችንም አንድ መስላ ብትታየንም እንደ ሕይወት ምልከታችን እና እምነታች ትርጉሟ የተለያየ ሆኗል ።
#ከጲላጦስ