Get Mystery Box with random crypto!

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ   'ከአቡበክር በስተቀር ማንኛውንም ሰው ወደ እስ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

  "ከአቡበክር በስተቀር ማንኛውንም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ያላመነታና ያላንገራገረ የለም።..." ረሱል ﷺ
   
                    ክፍል አምስት

   አቡበክርም (ረ.ዐ) “እሺ ስንት ልክፈልህና ነፃ ትለቀዋለህ?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ “በሰባት ወቄት ወርቅ እሸጥልሃለሁ” ይላል። አቡበክርም (ረ.ዐ) “እሺ እከፍላለሁ” በማለት ይስማማሉ።
ከዚህም ኡመያ ሳቅ ይልና እንዲህ ይላቸዋል፡፡ “ታውቃለህ አቡበክር
ስአራት ወቄት ካልሆነ አልወስድም ብትለኝ ኖሮ እንኳ እሽጥለህ ነበር።” አቡበክርም (ረ.ዐ) መልሰው “ወላሂ መቶ ወቄት ብትጠይቀኝ እንኳ ከፍዬህ እወስደው ነበር፡፡” ይላሉ፡፡ ከዚያ ክፍያውን ፈጸሙና ቢላልን በነፃ ለቀቁት። ከቢላል በኋላም ሕፃናትንና ሴቶችን በገንዘባቸው ነፃ አውጥተዋል።

      አባታቸው ከደካማዎች ይልቅ ይመሰገኑ ዘንድ ጠንከር ያሉትን
ነፃ ቢያስወጡት እንደሚሻል ደጋግመው ቢነግሯቸውም አቡበክር (ረ.ዐ) ግን "ይህን የማደርገው የአላህን (ሱ.ወ) ውዴታ ለማግኘት እንጂ ለሌላ ለምንም አይደለም፡፡” ብለው ይመልሱላቸው ነበር፡፡

   መልካም ድርጊታቸውን ጭቃ ሊቀቡ የተነሱ የመካ ሙሽሪኮች
የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎችን በአቡበክር (ረ.ዐ) ላይ ይነዙ ጀመር፡፡ “ቢላልን ነፃ እንዲወጣ ያደረገው እርሱ እንደሚለው የአላህን ውዴታ ለማግኘት ሳይሆን ከዚህ በፊት ቢላል የዋለለትን ዉለታ ለመመለስ ብሎ ነዉ።" እያሉ ሥራቸውን በማንኳሰስ አንጓጠጡ፡፡ በዚህ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) የሚከተለውን የቁርኣን አናቅጽ አወረደ

{ وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُۥ مِن نِّعۡمَةࣲ تُجۡزَىٰۤ (19) إِلَّا ٱبۡتِغَاۤءَ وَجۡهِ رَبِّهِ ٱلۡأَعۡلَىٰ (20) وَلَسَوۡفَ یَرۡضَىٰ (21) }

“ለአንድ ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ ግን የታላቅ
ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህን ሠራ)፡፡ ወደፊትም በእርግጥ
ይደሰታል፡፡” (አል-ለይል፡ 19-21)

    ሱረቱል ለይል በውስጧ ያካተተችው መልእክት በአቡበክር (ረ.ዐ) ላይ የተነዛው ሀሰት መሆኑን መግለጫ ነው፡፡ ሃያ አንድ አናቅፅን አካታለች፡፡

              ከሶሐቦች ሁሉ ጀግና
    አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ምንም እንኳ ጉልበታቸው ደካማና
ሰውነታቸው ለስለስ ያለ ቢሆንም በሐቅ ጉዳይ ግን መንፈሳቸው ጠንካራ ነበር። በአላህ(ሱ.ወ) ጉዳይ ማንንም አይፈሩም፡፡

   በአንድ ወቅት ስይድ ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ "ከሰዎች ሁሉ ጀግና
ማንነው? እርሶ ነዎት አሚረል ሙእሚኒን?” ተብለው ሲጠይቁ
የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ" የለም! ከሰው ሁሉ ጀግናው አቡበክር አስ-ሲዲቅ ናቸው። በአንድ ወቅት የቁረይሽ ከሃዲዎች ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከበው ሲያንገላቷቸው ተመለከትኩ፡፡ እኛ ራቅ ብለን ሁኔታውን እንመለከት ነበር፡፡ ለብቻቸው ሆነው ከሃዲዎቹን ገፈታተሯቸው፡፡ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዙሪያ ገለል አደረጉዋቸው፡፡ “አላህ ጌታዬ ነው የሚልን ሰው ልትገድሉ ነው እንዴ?” በማለት ተናገሯቸው፡፡ ከሐዲዎቹም ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ተወት አደረጉና አቡበክርን ያዟቸው፡፡ ዑቅበት ቢን አቢ ሙዐጥ የሚባል ከሐዲ መጣና የአቡበክርን (ረ.ዐ) ፊት ይመታ ጀመር፡፡ ፊታቸው እስኪያባብጥ ድረስ በጫማው ደበደባቸው፡፡ አፍንጫቸው
እስኪቀላ ድረስ ፊታቸው አበጠ፡፡ ከፊታቸው ላይም ደም ይፈስ ጀመር፡፡ አቡበክር ሲዲቅ ራሳቸውን ሳቱ፡፡

     ትንሽ ቆይቶም የአቡበክር (ረ.ዐ) ጎሳዎች የሆኑ በኒ ተሚሞች
መጡና ወደ ቤታቸው ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ ከመጎዳታቸው ብዛት ከሞት እንደማይተርፉ እርግጠኛ ነበሩ፡፡ ለእናታቸውም 'በሕይወት ከቆየ መግቢው፣ አጠጭውም' ብለዋቸው ሄዱ፡፡ ከዚያም ወደ ዑቅበት ተመልሰው ሄዱና አቡበክር (ረ.ዐ) ከሞት ሊበቀሉት እንደሚችሉ ዝተው ተመለሱ፡፡

    አቡበክር (ረ.ዐ) ከጉዳታቸው ትንሽ መለስ በማለት ዓይናቸውን
እንደከፈቱ ወዲያው የጠየቁት ጥያቄ «ረሱል እንዴት ናቸው?” የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ያልሰለመችው እናታቸው አጠገባቸው ነበረችና አሁንም ታስታውሰዋለህ እንዴ! አለቻቸው... እርሳቸውም "ወላሂ ያሉበትን ሁኔታ አውቄ ነፍሴ እስክትረጋጋ ድረስ እህልም ሆነ ውሃ አልቀምስም” ይላሉ፡፡

    በመቀጠልም "ወደ ኡሙ ጀሚል ፋጢማ ቢንት አል-ኸጣብ
(የሰይድ ዑመር እህት) ዘንድ ሂጅና ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያሉበትን ሁኔታ
ጠይቂያት፡፡” አሏቸው፡፡ የአቡበክር (ረ.ዐ) እናት ወደ ተባሉበት ቦታ
ይሄዳሉ፡፡ ያኔ ቢንት አል-ኸጣብ መስለሟን ደብቃ ትኖር ነበር፡፡
የአቡበክር (ረ.ዐ) እናት ስለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሁኔታ ይጠይቋታል።
እርሷም እንዲህ ትላለች "ወላሂ! ልጅሽንም ሆነ መሐመድን አላውቅም፡፡ ነገር ግን ደስ ካለሽ ልጅሽን ለመጠየቅ አብሬሽ ልመጣ እችላለሁ፡፡”

     ከዚያም ተከታትለው ወደ አቡበክር (ረ.ዐ) ዘንድ ይሄዳሉ፡፡
አቡበክርም "ፋጢማ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዴት ናቸው?” ሲሉ
ይጠይቋታል፡፡ እርሷም "እኔ ሙሐመድ ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡”
ስትል ትመልሳለች፡፡ አቡበክርም ነገሩ ገብቷቸው "አትፍሪ እርሷ እናቴ ነች።” ይሏታል፡፡ ከዚያም “ደህና ናቸው ምንም አልሆኑ፡፡” ትላለች አቡበክርም "ወላሂ! በዓይኔ እስካላየኋቸው ድረስ እህልም ሆነ ውሃ አልቀምስም” ይላሉ፡፡ እናትየውም "እግርህ እስኪሻልህ ድረስ ትንሽ ጠብቅ” ይሏቸዋል፡፡

    እርሳቸውም እግራቸው መራመድ እያቃተውም ቢሆን ብድግ
ብለው በመነሳት ሁለቱም ሴቶች ደግፈዋቸው የአል-አርቀም ቢን አቢ አል-አርቀም ቤት ይደርሳሉ፡፡ በር ሲያንኳኩ ይከፍትላቸዋል፡፡ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አቡበክርን ሲያዩዋቸው በጣም ያዝኑላችዋል። እቅፍ ያደርጓቸዋል፡፡ አቡበክር የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ማዘን ሲመለከቱ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ወላሂ ከፊቴ በስተቀር ደህና ነኝ ምንም አልሆንኩም» ይላሉ። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) በጣም አዝነው ዱዓ ያደርጉላቸዋል፡፡

    አቡበክርም እንዲህ ይሏቸዋል፡፡ "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ!
እናቴን አላህ ሙስሊም እንዲያደርጋት ዱዓ አድርጉላት፡፡” ነብዩም
(ሰ.ዐ.ወ) "አላህ ሆይ! የአቡበክርን እናት ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ምራት” ብለው ዱዓ ያደረጋሉ። የአቡበክር እናትም እዚያው እንደቆሙ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ፡፡

       አስ-ሲዲቅ ስለ እስልምና የነበራቸው ድንቅ አቋሞች

   ሰይድ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) በእስልምና ዙሪያ የነበራቸውን
አቋሞች ስናይ ለዲን የነበራቸውን ፍቅር ከፍተኛነት መረዳት እንችላለን፡፡ አስ-ሲዲቅ ሁሉ ነገራቸውን ለዲን የበላይነት ሲሉ
ገብረዋል። ነፍሳቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ቤተሰባቸውን ደማቸውን ይህን ሃይማኖት ለማገልገል ሲሉ ሰጥተዋል፡፡ ለእስልምና የበላይነት ሲሉ ሁለመናቸውን ከፍለዋል፡፡

   ስለ አስ-ሲዲቅ አቋሞች ስንነጋገር ዋነኛው ዓላማችን ሁሉም
ሙእሚን በዓርአያነት እንዲከተላቸው ነው፡፡ አቡበክርን (ረ.ዐ) ተምሳሌት አድርገን ከእስልምና ረገድ ያለብንን ኃላፊነቶች ሁሉ በአግባቡ እንድንወጣ ያግዘናል።

            ዕለተ-አል ኢስራእ ወል ሚዕራጅ

   ምንም ዓይነት ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት ባልነበረበትና
በማይታወቅበት ዘመን አንድ ሰው አንድ ሙሉ ሌሊት ባልሞላ ጊዜ
ዉስጥ ከመካ ተነስቶ ቁድስ ደርሶ ተመለሰ ተብሎ ቢነገር የሚታመን ነገር አልነበረም ::