Get Mystery Box with random crypto!

በሰብርና በሰላት መታገዝ አልሐምዱሊላሂ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ #ሰው ሲፈጠር ደካማ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

በሰብርና በሰላት መታገዝ

አልሐምዱሊላሂ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ


#ሰው ሲፈጠር ደካማ ሆኖ ተፈጠረ ፣በስሜቶችና ፍላጎቶችም የተሞላ ሆኖ እንዲሁ።
ታዲያ ችግሮቹን ለመቋቋምና ከእዝነቱም በመቅረብ ለመቋደስ ያስችለው ዘንድ በኢማን ላይ የተመሰረተ  ሁለት መሳሪያዎች ተሰጡት።የችግር መላቀቂያ መድሀኒት ቀረበለት።
ሰብርና ሰላት
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱسْتَعِينُوا۟ بِٱلصَّبْرِ وَٱلصَّلَوٰةِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡ በቀራ 2 :153


ታላቁ ሰሐባ ዐብደላህ ኢብኑ አባስ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና በመንገድ እየሄዱ  የልጃቸውን  ሞት መርዶይረዳሉ።እርሳቸውም ከመጓጓዣቸው ወርደው ሁለት ረከዓ ሰላት ሰገዱና አላህ  አላህ  በመታገስና በሰላት ተረዱ  ብሏል በማለት በልጃቸው ሞት  የተከሰተባቸውን  ሀዘን ለመቋቋም የአላህን እገዛ ፍለጋ ወዲያውኑ ወደ ቀደሩ ባለቤት የሆነው ፈጣሪያቸው ለመጠጋት ትዕዛዙን ፈፀሙ
ምንኛ  የተወደደ በቀልብ የገባ፣ የረጋ፣ በተግባር የተረጋገጠ ኢማን ።
አላህ  ሆይ ሰብርና በሰላትና ከሚጠቀሙ የኢማን ባለቤቶች አድርገን።

http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ