2022-07-31 15:42:41
تلاحظ هذه الطَّوائف المختلفة تجد أنَّ كلاَّ منهم يدَّعي أنَّه على الكتاب والسنة وكما قال الشَّاعر
وكل يدعي وصلا بليلى وليلى لا تقر لهم بذاكا
ዑመር ኢብን ዓብዱልዓዚዝ ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል
"من جعل دينه غرضا للخصومات أكثر التنقل"
“ዲኑን ለክርክር ኢላማ ያደረገ መቀያየርን ያበዛል”
አል ኢባናህ ሊብን በጧህ 584
ዲኑን ለክርክር ኢላማ ያደረገ ሰው መዘዋወርን ያበዛል፡፡ ከዚህም ከዚያኛውም ጋር ይከራከራል ከዚህም ከዚያም ጋር ይሟገታል በመጨረሻም አሸናፊውን ይከተላል፡፡ ይህ የሰለፎች ባህሪና አካሄድ አይደለም፡፡ ይልቁንም አንድ ሰው ለክርክር ከመጣ በቅድሚያ አላማው ምን እንደሆነ ይገነዘቡታል፡፡ ከዚያም “እኛ በግልጽ መረጃ
ላይ ነን አንተ ግን ተጠራጣሪ ነህ፡፡ ስለዚህ አንተን ወደመሰለ ተጠራጣሪ ሂድ” ብለው ያሰናብቱት ነበር፡፡
ከእርሱ ዘንድ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃ ያለው ሙስሊም የክርክሩ አላማ
የማሸነፍና የመሸነፍ ከሆነ ከአንድም ሰው ጋር ሊከራከር አይገባውም፡፡
ምክንያቱም ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጅ ሌላ የለም፡፡ ቁርኣንና ሐዲስን አጥብቀህ
ያዝ፡፡ በእነርሱ ላይ ቋሚ ሁን፡፡ ዲኑን ለብልሽት ለቢድዓና ለስሜት ባለቤት
አያጋልጠው፡፡ ጥልቅ የእውቀት ባለቤቶች ወይም በዲኑ ላይ የተመቻቹ ዓሊሞች ከሆኑ ግን ቢከራከሩም ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የአህለል ቢድዓ ዓቂዳ የተበላሸና የተጣመመ ብሎም ባጢል መሆኑን የሚያብራሩበትና የሚከራከሩበት ራሱን የቻለ ስልትና ዘዴ አላቸው፡፡
ትልቁ የችግሮቻችን መፍትሄ የሚገኘው ቁርኣንና ሱናን ጠንቅቆ በማወቅ በእነርሱ ላይ በመደገፍ ብቻና ብቻ ነው፡፡
በደንብ ካስተዋልህ አንተን የሚሞግቱህ ቁርኣን እና ሐዲስን እንከተላለን የሚሉ
ቡድኖች ናቸው፡፡
ግጥም ገጣሚው የሚከተለውን ተናግሯል
ሁሉም ለይላ የኔ ናት ብሎ ይሞግታል ለይላ ግን ለማንም አላረጋገጠችም።
https://t.me/Amirposts/
217 viewsAbu Taymiyyah Amir Mohammed, edited 12:42