Get Mystery Box with random crypto!

አሚጎስ በኅብረት ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ 52% ለአባላቶቹ ትርፍ አከፋፈለ። (አሚጎስ፣ ሚያዚያ 15 | AMIGOS SAVING AND CREDIT COOP.

አሚጎስ በኅብረት ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ 52% ለአባላቶቹ ትርፍ አከፋፈለ።

(አሚጎስ፣ ሚያዚያ 15 ቀን 2016ዓ.ም)

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር በዛሬው 10ኛ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤው የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2015 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ አባላት የፀደቀ ሲሆን የኦዲት ሪፖርቱም  ነጻ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ መከናወኑን እንዲሁም በባለፈው በጀት ዓመት (ከሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም) የስራ አፈጻጸም በአጠቃላይ 68.3 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ትርፍ ማስመዘገቡን የአዲስ አበባ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ፅህፈት ቤት የማህበራት የኦዲት ቡድን ኦዲተሮች ለጉባዔው ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል 51.84 ⁒ መሆኑ ተገልጾ ለአባላቱ እንዲከፋፈል በህብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ፀድቋል፡፡ በተጨማሪም አሚጎስ  ካተረፈው ዓመታዊ ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆነው ለህብረት ስራ ማህበሩ መጠባበቂያ ተቀማጭ የሚሆን ሲሆን ከመጠባበቂያ ተቀማጭ ውጪ የሆነው 70 በመቶ ትርፍ ለአባላት ባላቸው የሼር መጠን እንደሚከፋፈል ጉባኤው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

አባላት ኅብረት ሥራ ማህበራቸው ከተለያዩ የመኪና አስመጪና መኪና መገጣጠሚያ ተቋማት ጋር  በሚያደርጋቸው ስምምንቶች በቀላሉ መኪናዎችን እንዲያገኙ በማስቻል ላይ መገኙቱና  በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት  በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡