Get Mystery Box with random crypto!

ለአፍሪካ ወጣቶች የቀረበ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እውቀትና ክህሎት ማዳበሪያ መርሓ ግብር ለ | ᴀᴍᴇsɪ ᴛᴇᴄʜ ✅

ለአፍሪካ ወጣቶች የቀረበ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እውቀትና ክህሎት ማዳበሪያ መርሓ ግብር

ለአስር ሳምንታት በሚቆየው መርሓ ግብር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የበይነ መረብ አጋዥ ሥልጠናዎች እና የዘርፉ ምሁራን ልምድ ይቀርብበታል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በመርሓ ግብሩ ማጠናቀቂያ በዳታ ሳይንስ፣ ዳታ ምህንድስና እና ፕሮግራሚንግ ዙሪያ መሠረታዊ እውቀት እንደሚጨብጡ ይጠበቃል፡፡ በዚህም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ወደፊት ስኬታማ የሙያ መሰላል ለመገንባት የሚያስችላቸውን አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተመላክቷል፡፡

ሥልጠናው ወጣቱን የአህጉሪቱ ትውልድ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እውቀትና ክህሎት ለማብቃት ያለመ መሆኑን የብላክ ኤንድ ብሪሊየንት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተሳታፊዎቹ ከሥልጠናው በተጨማሪ ከጉግል፣ ሾፒፋይ እና ፉጂትሱ ከመጡ አሰልጣኞች ጋር በመሆን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሥነ-ምግባር መርሕዎች፣ መድልዎች እና ሌሎች የዘርፉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፡፡

የተሰናዳውም የተለያዩ ትምህርቶችን በበይነመረብ በነጻ በማቅረብ በሚታወቀው ኮድአካዳሚ እና ብላክ ኤንድ ብሪሊየንት በተባለ ጥቁር ባለሞያዎች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት በሚሰራ ቡድን ትብብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

EAII

@Amesi_Tech
@Amesi_Apps
@Amesi_Tech_Group
@Amesi_Tech_Bot


▬▬▬▬▬▬ sʜᴀʀᴇ ▬▬▬▬▬▬