Get Mystery Box with random crypto!

'ድካሜንና ውድቀቴን አውቃለሁ። በራሴ መንገድ ኃጢአትን ለመተው ሞክሬአለሁ። አሁን በሕይወቴ አንተ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

"ድካሜንና ውድቀቴን አውቃለሁ። በራሴ መንገድ ኃጢአትን ለመተው ሞክሬአለሁ። አሁን በሕይወቴ አንተ ጣልቃ ትገባ ዘንድ ያስፈልጋል። እኔ በራሴ ኃይል ኃጢአትን መተው አልቻልኩምና።"

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም" ያለን። ያለእርሱ ምንም ማድረግ ስለማንችል ነው። ንስሐ መግባት፣ መጸለይ፣ መጾም፣ ከቅዱሳት ምሥጢራት መሳተፍ በአጠቃለይ ከኃጢአትን ነጽተን በንጽሕና መኖርን እንፈልጋለን። ማሳካት የምንችለው ግን በእርሱ በእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የጸሎታችን ይዘት የእኛን አለመቻል የእግዚአብሔርን ከሀሌ ኩልነት የሚገልጥና በተሰበረ ልቡና በትሑት ቃል ሊኾን ይገባዋል። ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በእርሱ ሀሳብና ፈቃድ እንኖር ዘንድ ያድለናል።
"በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?" ዘፍ፲፰
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
ሐምሌ ፲ ፳፻፲፬ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
https://t.me/Amdehaymanotzeortodoxtewahdo