Get Mystery Box with random crypto!

ፈታዋ ላይ ደፋርና ችኩሎቹ በእውቀት ዝቅተኛ ክፍሎቹ ናቸው! ሳዕድ ከ ሀጃጅ ኢብኑ ዑመይር ይዞ | አል ሁዳ

ፈታዋ ላይ ደፋርና ችኩሎቹ በእውቀት ዝቅተኛ ክፍሎቹ ናቸው!

ሳዕድ ከ ሀጃጅ ኢብኑ ዑመይር ይዞ እንዳስተላለፈው እንዲህ ይላል

« በአንድ የዲን ጉዳይ ላይ ዐልቀማህን ጠየቅኩት ዐልቀማህም እኔን ሳይሆን ሂድና ዑበይዳህን ጠይቅ አለኝ ዑበይዳን ስጠይቀው እራሱን ዐልቀማን ጠይቅ ብሎ መለሰኝ ወደ ዐልቀማህ ተመልሼ ነገርኩት በቃ ወደ መስሩቅ ሂድና ጠይቅ አለኝ ወደ መስሩቅ ሄድኩኝ መስሩቅም መልሶ ወደ ዐልቀማህ መለሰኝ ዐልቀማህም ወደ ኢብኑ አቢ ለይላ ሂድና እርሱን ጠይቅ አለኝ አቢ ለይላን ስጠይቅም ፈታዋውን ሊሰጠኝ አልቻለው ዐልቀማህን ጠይቅ የእውት አባት እሱ ነው አለኝ በስተመጨረሻ ዐልቀማህ እንዲህ ይባላል አለኝ...

« ፈታዋ ላይ ደፋርና ችኩሎቹ በእውቀት ዝቅተኛ ክፍሎቹ ናቸው! »

( አኽላቀል ዑለማእ ሊል አጁሪይ ከገፅ 110–111)

ፈታዋ ላይ ደፋር ደፋር አይሰራራን ልዮ በሆነ መልኩ ደግሞ ይሄ ፌስቡክ ዐሊሙንም የኔ ቢጤው ጃሂሉንም እኩል ያደረገ መድረክ ነውና በማናቀው ጉዳይ አንዘባርቅ ይህ ዲን አባት አህል) አለው ለ አህሉ እንተወው አቅማችንን እንወቅ !