Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊሞች ይህን ሲባሉ ከቁርአን በመጥቀስ ነቢያትና ሐዋርያት ሙስሊም መሆናቸውን መስክረዋል ይላሉ | Obadiah Apologetics

ሙስሊሞች ይህን ሲባሉ ከቁርአን በመጥቀስ ነቢያትና ሐዋርያት ሙስሊም መሆናቸውን መስክረዋል ይላሉ

ይህ ግን አሁንም ተቀባይነት የሌለው circular reasoning ነው። ቁርአን የአላህ ቃል ነው። በቁርአኑ እከሌ የሚባለው ነቢይ፥ እከሌ የሚባለው ሐዋሪያ ሙስሊም ነኝ ብሏል ያለው አላህ ነው። እነርሱ ብለዋል ብሎ ተናገረ እንጂ፥ እነርሱ ራሳቸው አይደሉም ሙስሊም ነን ያሉት

ከላይ ባየነው ምሳሌ መሠረት፥ አቶ አማረ "አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አቶ አማረ ምሩቄ ነው ብሏል" ቢል፥ ነገር ግን ከራሱ ከዮኒቨርሲቲው የመጣ ቀዳማዊ ማስረጃ ከሌለው፥ የተናገረው ነገር ተቀባይነት እንደማይኖረው ሁሉ፥ ነቢያትና ሐዋርያት አላህን ማምለካቸውን የሚያሳይ ከራሳቸው ዘንድ የመጣ ቀዳማዊ ማስረጃ ከሌለው ተቀባይነት የለውም።

ሙስሊም መሆናቸው ሊረጋገጥ ካስፈለገ primary source ያስፈልጋል። ራሳቸው ሙስሊም መሆናቸውን መመስከር አለባቸው። እንጂ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባው አላህ ለራሱ ምስክርነት ሊሰጥ አይችልም። ሙስሊም ለመሆናቸው ከራሳቸው ዘንድ የመጣ ማስረጃ መምጣት አለበት

ታዲያ ነቢያትና ሐዋርያት ያወቁት የእስራኤል አምላክ ማነው?

ነቢያትና ሐዋርያት ያወቁት አንዱ የእስራኤል አምላክ ሥላሴ ነው። አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ። ይህ የነቢያቱና የሐዋርያቱ ጽሑፎች ከሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ሊረጋገጥ የሚችል ነገር ነው። ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ድረስ የተመሰከረለት ሀቅ ነው

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት ነቢያት አምላካቸው አብ፥ ልጁ/መልአኩ እና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን መስክረዋል። አምላካቸው የነበረው አንዱ አምላክ እርሱ ነው። በአዲስ ኪዳንም ሐዋርያት፥ ይህንኑ አምላክ በመከተል አምላካቸው አብ፥ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን መስክረዋል። የነቢያቱ አንዱ አምላክ የነርሱም አምላክ ነበርና። (ልጁ በስጋ ስለመጣ ኢየሱስ ክርስቶስ ተባለ)

የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ ሥላሴ ነው። አላህ አይደለም። ይህ ማለት አላህ ጣዖት ነው ማለት ነው። እስራኤል ያላወቀው ባዕድ አምላክ ተብዬ

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያዘን አንከተለውም። አናመልከውም። አንገዛለትም። አናምንበትም። አንፈራውም። ምንም አይነት ቦታም አንሰጠውም። ይልቁንም እንደ ጣዖት እንርቀዋለን። ሰዎችም እርሱን በማምለክ በጣዖት አምልኮ እንዳይተበተቡ እንጣራለን። የማይታወቅ የአሕዛብ አምላክ ነውና። አይን እያላቸው ከማያዩት፥ ጆሮ እያላቸው ከማይሰሙት ጣዖታት ምድብ የሚመደብ ነው።

እስራኤል ያላወቀውን አምላክ ከመከተል እንጠበቅ!

say #No! to allah!