Get Mystery Box with random crypto!

Alex Abreham በነገራችን - ላይ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alexabreham — Alex Abreham በነገራችን - ላይ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alexabreham — Alex Abreham በነገራችን - ላይ
የሰርጥ አድራሻ: @alexabreham
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.24K
የሰርጥ መግለጫ

በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር
1- ከዕለታት ግማሽ ቀን
2- ዙቤይዳ
3 - ዶክተር አሸብር
4 - እናት ሀገር ፍቅር
5 - አንፈርስም አንታደስም
💚💛❤️
አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው::
Not Official
@con_me_here

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-03 07:20:08 "ሳናብድ ያበደልን እብድ የተባረከ ይሁን"

ተራኪ- ቤቲ ሃበሻዊት

ከወደዳችኋት Comment
2.1K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 12:18:01 #ግጥም
ከዛስ እንዳትሉኝ!

አስታወሰኝ ረጋሳ
3.0K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 09:52:31 ኑ መርጠን እናልቅስ!
(አሌክስ አብርሃም)

የጨረባ ችሎት የክፉ ዘመን ክስ
"ለገደልኩት ሳይሆን ለሞተብኝ አልቅስ!"
ደም ባጠቀሰ ጣት ወደሰው አጠቁም
ከቻልክ ታጠብና ከሚስኪኖች ጎን ቁም
"መርጦ አልቃሽ " ባይ አንተ "መርጦ አራጅ" ወመኔ
አጨብጭብ ለገዳይ ላልቅስ ለወገኔ
መግደል እጣህ ሁኗል ማዘን እጣው ለ'ኔ!
ካፈራበት ማሳ የሰው ነፍስ ቀንጣሽ
"መርጦ አራጅ" ሳያፍር ለምን ይፈር አልቃሽ ?"
በደም እየዋኘህ አላግጥ አንጓጥጥ
ንፁህ ደም ልትሸፍን አኞ መግለጫ ስጥ
የግፍህ መሠረት አሸዋ ላይ ቢጣል
ፍትህ እንደዝናብ ዶፍ ሁኖ ይመጣል
የት'ቢት ባቢሎን በእንባ ጎርፍ ይናጣል
እስከዚያው ለሰዎች ሰው ሰው ለሚሸቱ
ሰው ከመሆን ኪዳን በግፍ ላልተፋቱ
((እጩ ሟቾች )) ስሙ ግፈኛን አንቀድስ
የፍጅት ኪዳኑን የደም ሱሱን ሲያድስ
"መርጦ ላረዳቸው" ኑ "መርጠን እናልቅስ!"


#Share
#AlexAbreham

JOIN
@AlexAbreham
3.9K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 09:08:07 በደንባራ በቅሎ ስልጣን ተጨምሮ !
(አሌክስ አብርሃም)

የመረረ ብሔረተኝነትን ያውም አዙሮ ከሚደፋ ጥላቻ ጋር ከኬጂ ጀምሮ እየተጋተ ያደገ ሀይል አሁን እየሆነ ያለው ነገር ያስደነግጠዋል ማለት ዘበት ነው! የበዙ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ የሚበዛው አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኝነት አቀንቃኝ ደጋፊ እንዲሁም የዘር ሀረግ ቆጥሮ ከጥቅማ ጥቅሙ ቅንጥጣቢ ለመለቃቀም ያሰፈሰፈው ሁሉ አሁን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያላቸው አመለካከት ስልጣን ይዞ አገር የመምራት ሳይሆን የነብርን ጅራት የመያዝ አይነት ነው! ከአገር እድገት... ከዜጎች ደህንነትና አለም አቀፉ ነባራዊ ሁኔታ በላይ የሚያሳስባቸው ...ራሳቸው አጋነው የሳሉት "ነብር" ነገር ነው! ብንለቀው ዙሮ ይበላናል በሚል ፍራቻ ላባቸው ጠብ እስኪል በፍርሃት ጅራቱን ይዘው እየጎተቱ ናቸው! ሲጎትቱ ግን ነብር ነው እያሉ አይደለም አህያ ነው እያሉ ነው!እንኳን ከሌላው አመለካከት ጋር ቀርቶ ራሳቸው አፍና ልባቸው አይተማመንም!
ከዚህ መጓተት የሚቀድም ዓላማም ሀሳብም የላቸውም! ይሄ መጓተት "ለነብሩም" ለነብር ጅራት ጎታቹም ፍፃሜ የሌለው ድካም ነው! የመጨረሻ አላማቸው እንደምንም እጃቸው የነብሩ አንገት ላይ ቢደርስ አንቀው መግደልና መገላገል ብቻ ነው! ቢያንስ ያንን ለማድረግ መጀመሪያ የነብሩን ጥፍሮች መቆራረጥ ጥርሶቹን መነቃቀል ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ! እያደረጉ ያሉት ግን "ነብር" ብለው ከፈረጁት አካል ላይ ፀጉር መንጨት ነው! ፀጉር ደግሞ ተነቅሎ አያልቅም! በየቀኑ የሚያድግ ተፈጥሯዊ ኡደት አለው! ለዛም ነው በምድራችን ላይ የተፈፀሙ ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋዎች ትዝብትና ፍርድ እንዲሁም የእርስ በርስ እልቂት አትርፈው ያለፉት! የመጨረሻው ጅል እንኳን ይሄን ያውቃል!
የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ፈፅሞ አልገባቸውም! ይሄ የምንጎትተው ነገር ሲሰበከን እንደኖረው ነብር ነው ወይስ በግ አልያም አያያዛችን ያስቆጣው ሰው ብለው ለማሰብ ፍርሃታቸው አፍታ የሚሰጥ አይደለም! ደንባራ ብሔረተኝነታቸው ላይ የስልጣን ቃጭል ተጨምሮ በተቅጨለጨለ ቁጥር ደንብረው አገርና ህዝብ እያጠፉ ነው! በዚች አገር ላይ የመረረው የኦሮሞ ብሔረተኝነት የፈጠረው ትርምስ መቸም አይፈወስም! እንደውም ከቀን ወደቀን እጅግ እየከፋና አድማሱንም እያሰፋ ነው የመጣው! ምክንያቱም አሁንም ስብከቱ ቀንድና ጅራት እየቀጠለ በስርዓት ደረጃ በባለስልጣናት የሐሰት ትርክት ቀጥሏልና!
በእነዚህ አራት ዓመታት የተፈፀመውን ቁጥር ስፍር የሌለው ጥላቻ አቆይተነው ...ለኦሮሞ ህዝብ መብት ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ፖለቲከኞች ዩቲዮበሮች ፌሰሰቡከሮች " የሐይማኖት" ሰዎች ጭምር ሌላው ህዝብ ላይ የሚሰነዘር ዘለፋ የጥላቻና እልቂት ቅስቀሳ እንዲሁም ፀያፍ ስድብና ማንቋሸሽ ለሰሚው ይዘገንናል! ተራውን ህዝብ ተውት ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ እንደፈለገ ጥላቻ የሚሰብከውን ለተመለከተ ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ አይነት ብልግና እንዲህም አይነት ባለጌና ጋጠዎጥ ስርዓት በአደባባይ ሰምታ ታውቃለች ወይ ያስብላል! ይሄ ተራ ዘለፋ ብቻ አይደለም ! ለነገም ከዛሬ የከፋ ነገር መሰነቁን ጠቋሚ ምልክት እንጅ! አሳዛኙ ነገር ደግሞ ለዘብተኛ የሚባሉት ሳይቀሩ ከዚች "ለውጥ" በኋላ እንደቀልድ ጭልጥ ወዳለ ጥላቻና የዚህ ቡድን ደጋፊነት እየተንሸራተቱ መግባታቸው ነው!
በነገራችን ላይ ... ብዙ ሰው እዚህና እዚያ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን ተራ የጫካ ቡድን ድርጊት አድርጎ በማየት ዝቅ ያለ ግምት ሊሰጥ ይችላል! ነገሩ ግን ሙሉ ወታደራዊ አደረጃጀትና ስምሪት ያላቸው የሰለጠኑ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ የከተማ ክንፍ ያላቸው ስልጣን ላይ ያለው ድርጅት ውስጥ የተሰገሰገ ደጋፊ ሞልቶ የተረፋቸው በወጉ እንኳ ጥፋታቸው እንዳይዘገብ እሹሩሩ የሚባሉ ጭካኔያቸውና እንስሳዊ ድርጊታቸው የሚድበሰበስላቸው ስማቸው በክፉ እንዳይጠራ የሚጨነቅላቸው አካል ያላቸው /በተዘዋዋሪ የሚዲያ ድጋፍ ያላቸው ድጋፉ አበጃችሁ በሚመስል ዝምታ/ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች ናቸው!
እነዚህ ብሔረተኞች ኦሮሚያ ጫካ እና ከተሞች ውስጥ የሚወሰኑ ከመሰለን የዋህነት ነው! (((ነገ አዲስ አበባም ይሁን ሌሎች ከተሞች ህንፃወችን በፈንጅ ከማንጎድና በየቦታው ተመሳሳይ ጥቃት ከመሰንዘር አይመለሱም! የቀራቸው ይሄ ነው በጣም በቅርቡ ደግሞ ያደርጉታል ...ይሄን ))) ዘመናዊ መሳሪያዎችን በገፍ የሚያገኙ ከመከላከያ ሰራዊቱ እኩል የሚታጠቁ ከሞላ ጎደል የክልሉ ህዝብና መንግስት ድጋፍ ያላቸው ሰዎች አሁንም የትና በማን ምን አይነት ስልጠና እየወሰዱ እንዳሉ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው!
መፍትሔው ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣት በተዋረድ እስከወረዳና ቀበሌ ድረስ ለዚህ እልቂት በአለም አቀፍ ደረጃ በለየለት የዘር ፍጅት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና በክልሉ ውስጥ ላሉና የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች የደህንነት ዋስትና እንዲሰጥ ሁላችንም መጣር! ሁሉም እንደሰው የሚያስብ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጉዳይ መስራት ! እንዲሁም በተለይ ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚዋሰኑ ክልሎች ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ከዚህ ክልል እንደሚመነጭ አውቀው እንዲሁም የክልሉ አመራሮች ይህን እልቂት የመከላከል ፍለጎቱም ብቃቱም እንደሌላቸው ተረድተው የየራሳቸውን የፀጥታ መዋቅር ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል! ከፓርላማ እስከ"የህዝብ" ሚዲያዎቻችን ጉዳዩ እንዳይወገዝ ለማፈን ያደረጉት ጥረት ታሪክ ይቅር የማይለው አስነዋሪ ተግባር ነው!
ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ ይህን ዘግናኝ ጭፍጨፋ "ጠላቶቻችን አገር ለማፍረሰሰ ምናምን" በሚል እንጩጭ ስብከት ትክክለኛ የአገር ጠላቶችን ከነአስተሳሰባቸው ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው! በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ዋና ቀዳሚ ጠላት አክራሪው የኦሮሞ ብሔረትኝነት የወለደው ፅንፍ የለሽ የጥላቻ ትርክት ነው ! በዚህ ትርክት የተጠመቀ ሁሉ አገርን እንደጋንግሪን ቀስ በቀስ እየበከለ ከመግደል ያለፈ ሚና አይኖረውም! ለዜጎቻችን የግፍ ጭፍጨፋ ተጠያቂው ይሄ አካል ነው! የትርክቱ አጥማቂና ተጠማቂ!!


#Share
#AlexAbreham

JOIN
@AlexAbreham
4.1K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 16:18:34 ናዕት
ቴዲ አፍሮ
ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌው ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ
ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት
እያመመው መጣ
ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ….እያለ ማሲንቆ
ኡ….ኡ…..
እያመመው መጣ
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
እያመመው መጣ
ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዳር አለው እንዴ ድንበር
ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
የዘር ሐይማኖት ድንበር
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
በዚህ ለፀና እውነት
የፍቅር ሐገር ከጥንት
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከሞት
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት
ዶፍ ዶፍ ብዘንብ እሳት
አገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ናዕት



3.0K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 12:27:02 ለሞት ህይወት መስጠት!
(አሌክስ አብርሃም)

በብራቅ ጠመንጃ ለሚረግፍ ' መንደር'
ይሰማል ብለህ ነው ጯሂ ቃል መሰደር?
መልህቅ አይጥልም ቢገፋን ቢከፋን
ደም ላይ ይንሳፈፋል ያ ወላዋይ ዙፋን
ህይወትን ገንዞ ለሞት ህይወት መስጠት
ህዝብ ልብ ውስጥ ከስሞ ስልጣን ላይ መሠንበት !
ሰምቶ ማደባበስ ቅርሱ በሆነ አገር ...
ከባሩድ አይጮህም ሰው ምንም ቢናገር!
ደንቆሮ ነው ምድሩ ...ጋራ ሸንተረሩ
ሰልቅጦ ዝም ነው ሰው ሲረግፍ ከስሩ!
ተኳሹ ደንቆሮ ነፍስ መቀለጃ
ጆሮውን ሸጦ ነው የገዛው ጠመንጃ?!
ተንታኙ ይተንትን የሚገጥም ይግጠም
ፎቶ አንሽው ይለጥፍ አስከሬንና ደም
ድምፅ እያሳመረ ሌላው ያውርድ ሙሾ
በቃል ዘነዘና ይወቀጥ ስርዓቱ ይላም እንደጌሾ!
ላንድ ሰሞን ንዴት እንዳንበሳ እናግሳ
እንኳን የገዳይ ፍርድ ሟቹ እስከሚረሳ
እለት እንክሰሰው በየቀኑ እንማው
እኛ የፈራነውን "ፈረንጅ" እንዲሰማው¡
ዙፋኑ እስኪረጋ ምናል ብንከፋ
ሰው ሞተብን እንጅ "ኢንተርኔት" አልጠፋ¡
ሞት ማለት ዜና ነው እልቂት ማለት ቁጥር
ተስፋ መዘናጋት ፍትህ ማለት ሚስጥር
ገንፎ ሲቀርብ ነበር ማሰብ ስለስንጥር !
እስከዛው ...
ገዳይ ጥቂት ገድሎ አያገኝም ዝና
እልፎች ካልታረዱ ዜና አይደምቅምና?
መርዶ ሸጦ አዳሪ በሟች ደም ይጠቀም
ጥግጋት ያጣ ህዝብ ሬሳውን ይልቀም !

#Share
#AlexAbreham

JOIN
@AlexAbreham
2.6K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 21:01:18 Alex Abreham በነገራችን - ላይ, [6/20/2022 12:02 PM]
አቸ ብረቱ !
(አሌክስ አብርሃም)

የአቸ ብረቱ ጥንካሬ የሰው አይመስልም! የሰራውን ሁሉ ብዘረዝር ስለማታምኑኝ …ሊታመን የሚችለውን ገድሉን እንደሚከተለው እዘረዝራለሁ ! እኛ ሰፈር ስትመጡ፣ ልክ ከዋናው መንገድ ተገንጥላችሁ ወደአፈርማዋ መንገድ እጥፍ ስትሉ ያለችው የቆርቆሮ ኪወስክ በር ላይ ኒያላ ሲጋራ እያጨሰ ጫት የሚቅም ቀጫጫ ልጅ ካያችሁ እሱ አቸ ብረቱ ነው! ቅጥነቱ ሱቁ በር ላይ ከሚቆሙት የሚሸጡ መጥረጊያወች እንደአንዱ ነው … በዚያ ቅጥነት ከአፉ የሚትሎገለገውን የሲጃራ ጭስ ላየ ሰው የሆነ ቀጭን የመኪና ጭስ ማውጫ እንጅ ሰው አይመስልም!
ታዲያ እዚህ ልጅ ጋር በሆነ አጋጣሚ ብትጋጩ(እንድትጋጩ አልመኝም) ቅጥነቱን በማየት አካላዊ ሳፋጣ ውስጥ እንዳትገቡ! አንዳንዶች እንደሚሉት አንዳች የሚያግዘው መንፈስ አለ እንጅ በዚህ ሰውነት ይህን ያህል ጥንካሬ እንግዳ ነገር ነው! ስራ የለውም …ድሮ አሰብ የሚባል አገር ነበርኩ ይላል …እና ስራየ መርከብ ሲበላሽ እና መንገድ ሲዘጋ ጎትቸ ዳር ማስያዝ ነበር ሲል ቀልዱ ቢያስቅም ግን ቢሆንስ የሚያስብል ነገር ደግሞ አለው ….የተበላሸ ሲኖትራክ ብቻውን መጎተቱን ድፍን የሰፈሩ ሰው ያውቃል ….
ሽብሬ ስታገባ ባሏ አቅፏት ፎቶ መነሳት ፈለገች (ሽብሬ እንዲህ ማሰቧ የሰማውን ሁሉ አሳቀው ) ሽብሬኮ ከታክስ በፊት መቶ አስራ አንድ ኪሎግራም የምትገመት እመቤት ናት! አቸ ግን አልሳቀም ‹‹ሰርጓ ነው …ሴት ልጅ ለሰርጓ ልዕልት ናት… የባሏን ሱፍ ለብሸ እኔ አቅፋታለሁ ባይሆን ፎቶውን ከኋላየ አንሱኝ›› አለ …አለና ተነሳ! ይህን ሚስጥር ብዙ ሰው አያውቅም ... የመጀመሪያው የሰፈራችን ‹‹ስታንት ማን›› ነው አቸ! ምንም እንኳን ባሏ ጋር አንድ ልጅ ወልደው ቢፋቱም ያ ፎቶ እስካሁን ሽብሬ ቤት ሳሎን ተሰቅሏል !አቸም አንዳንዴ ሽ ብሬ ቤት ጎራ ይላል እየተባለ ይታማ ነበር! ባሏ ሲፋቱ ሰሞን ሲቆይ የሱ መስሎት ‹‹ፎቶየን አውርጅ ›› ቢላት ሽ ብሬ ‹‹የፎቶና የልጅን ነገር እንኳን ተወው …ሁለቱም የውክልና ነው !›› ብላ በሳቅ ፍርስ አለች አሉ!
የአቸ ዋናው ገድል ይሄ ነው! ሰፈራችን ከመሸ መንቀሳቀስ በጣም አደገኛ ሁኖ ቆይቶ ነበር ! ስሙም መልኩም የማይታወቅ ማጅራት መች በቃ እድል የጠመመበትን ጓ ነው ! የተመቱት ሰዎች እንደሚሉት ይሄ ማጅራት መች ጥላው ብቻ እንደዝሆን ይከብዳል …በዛ ላይ ጋን ጋን የሚሸት ሰው ነው …አንዴ ማጅራታቸውን ሲላቸው ብዙ አይነት ብርሃን እንደሚታያቸው ነው የሚናገሩት! በክንዱ አንቆ እንደደህና ፍቅረኛ ደረቱ ላይ አስደግፎ ነው የሚፈትሸው !አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ማጅራት መች ጨለማ ውስጥ ቁሞ ጥሎሹን ሲያማትር እንደመርፌ ጥላ የቀጠነ ሰው በጨለማው ውስጥ እያፏጨ ሲመጣ ተመለከተ ….ኧረ ድፍረት ብሎ ተዘጋጀ ….
አጠገቡ ሲደርስ …ድንገት ዘሎ የቀጭኑን ሰው ማጅራት ለቅጥነቱ በሚመጥን ‹‹ዶዝ›› …ጓ አደረገው… ተዝለፍልፎ ይወድቃል ብሎ ያሰበው ቀጫጫ ግን ወይ ፍንክች ….ስቸው ይሆን እንዴ ብሎ አሰበ ወጠምሻው ! እና ጠንከር አድርጎ ደገመው …ንቅንቅ አላለም ! በመጨረሻ ከኋላው በክንዱ አጥብቆ አነቀው… ቀጭኑ ሰው ድንገት ወደፊቱ ጎንበስ አለ… ያንን ዝሆን የሚያክል ሰው አንደህፃን አነሳውና አዝሎት ሮጠ …ማጅራት መችው እልህና ግርምት ይዞት ቀጭኑ አቸም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት እየበረረ ለዓመታት አልያዝ አልጨበጥ ያለውን የጨለማ ንጉስ አንከብክቦ ብርሃን ላይ አሰጣው …የሰፈሩ ሰው ያንን ወጠምሻ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ከመቀርቀሪያ እስከወጥማማሰያ ይዞ በመውጣት ‹‹ከቦ አናገረው›› !
አቸም ድንጋጤው በረድ ሲልለት አለ ‹‹ የጨለማውን ስራ እገልጥ ዘንድ መንፈስ በእኔ አደረ… እኔ ተራ ዜጋ ነኝ በመንገዴ አንገቴን ደፍቸ የማልፍ... የማይታዩት ሲበድሉ …ሲዘርፉና ሲያስፈራሩ በትእግስት ያለፍኩ …እነሆ ታናሽነቴን ናቋት …ጎስቋላነቴንም በመዳፋቸው ልክ ገምተው ሊጥሏት ሰነዘሩ … የኑሮን ጅራፍ የቻለ ጀርባየ የመረረው ቀን በዳይን ተሸክሞ ወደብርሃን ያወጣ ዘንድ …የሚስኪኖች መንፈስ እንዳደነደነው አምባገነኖች አያውቁም!›› እፎይ አለ መንደሩ ለዓመት …ከአመት በኋላ ግን … ሌላ ማጅራት መች ተነሳ …ጨለማውን የለበሰ …ሰዎችም አሉ …((አንገታችንን ሲያንቀን የቀጭን እጁ አጥንት ይወጋን ነበር …ደግሞም ኒያላ ኒያላ ይሸት ነበር !))

#Share
#AlexAbreham

JOIN
@AlexAbreham
2.5K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 18:12:59 Forgot password is my password!
(አሌክስ አብርሃም)

አሜሪካ ኑሮው ከባድ ነው፣ብቸኝነቱ ከባድ ነው፣ አየሩ ከባድ ነው ፣ ይሄ ከባድ ነው …ያ ከባድ ነው ይላሉ እንጅ እኔ እስከአሁን የከበደኝ ሁለት ነገር ብቻ ነው! አንዱ ፓስወርድ ማስታወስ ! ፓስወርድ የሌለውን ነገር ጠይቁኝ …. ፓስወርድ በጣም ከመብዛቱ የተነሳ ዝም ብሎ በተራ ቁልፍ የሚከፈት ነገር ላይ ሁሉ ጣቴን አሾላለሁ! ዋሌቴን የሞላውን ካርድ አውጥቸ ብበውዘው …. በየመንገዱ እየዞርኩ በመጫዎቻ ካርድ ማጅክ ምናምን የምሰራ ሰው ያስመስለኛል !እዚች አገር ትንሽ ከቆየሁ እንደጋሽ ስብሃት ካርዴን በፌስታል መያዜ የማይቀር ነው! እንግዲህ ይሄ ሁሉ ካርድ ፓስወርድ አለው! እንዴት እንደሚሰለች የደረሰበት ያውቀዋል! እና አንድ ወዳጀ forgot password is your password ይለኛል !
ሁለተኛው ችግሬ … በጣም የሚበዙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ስቀላቀል ልክ እንደቻይና ኮሪያ ምናምን አንድ አይነት ይሆኑብኛል ! መለየት በጣም ነው የሚከብደኝ ! በምሳሌ ላስረዳ! አሁን በቅርቡ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሳ ጠሩኝ …ምክንያት? ከኢትዮጵያ እህታቸው ስለመጣች! ....ስደርስ ያለምንም ግነት ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ አንድ አይነት ሴቶች ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይላሉ …የሌላውን እንግዳ ብዛት ደግሞ ተውት …ሁሉም አንድ አይነት የባህል ልብስ ለብሰዋል …ሁሉም ሹሩባ ተሰርተዋል …ሁሉም በሜካፕ አብደዋል …ሁሉም አይፎን ስልክ ይዘዋል … እና ሁሉም ጥርሳቸው ብሬስ …በእርግጥ ሁሉም ቆንጆዎች ነበሩ ! እና ምሳ የጠራችኝ አክስታቸው እያስተዋወቀችኝ ነው …
እሷ ቲጅ ናት ባለፈው ዳኒን አግብታ የመጣችው …ያው ዳኒ ግን የአጎቷ ልጅ ነው …ለፕሮሰስ ነው እንጅ እሷ አላገባችም ሲንግል ነች ሂሂሂ(ምን ሂሂሂ ያስብላል) !ትክ ብየ አየኋት በስማም ቁንጅና ….ሌሎቹ ጋር አንድ አይነት !ይሄ የተረገመ ሹርባ እንዴት ነው ሰው የሚያመሳስለው! …ይችኛዋ ኪያ ነች ….የዛሬ አመት አሴን አግብታ የመጣችው …አሴን ታውቀው የለ የኔ ትልቁ ልጅ የሩታ ባል …ለፕሮሰስ ነው እንጅ ትክክለኛ ባሏ ዳጊ ነው ! ያች (ነይ አንች ሰላም በይው ) ፍልቅልቅ እያለች መጣች ! ይች ሩሃማ ነች … ለቫኬሽን መጥታ በአሳይለም የቀረችው …
ፖለቲከኛ ነች ጋዜጠኛ?…አልኩ …..
ማን እሷ? አሁን ያለው ጠቅላይ ሚንስትር ማነው ብትላት አታውቀውም …ለፕሮሰስ ነው ! ያችኛዋ ናኒ ነች የፍሬው ሚስት …እና ደግሞ ይች ፊኖ የሽሜ ሚስት …ያች ….ኪራ ለፕሮሰስ ፍፄን አግብታ የመጣችው ናት …ፍፄን ታውቀው የለ የሲቲና ባል ….
ዘወርወር ስላለብኝ …ከምግብ ቡፌው ላይ ሁለት ናብኪን አንስቸ ሰሃኑ ላይ ካነጠፍኩ በኋላ ቀይ ወጥ ጨመርኩበት …አልጫ ልጨምርበት ስል ነው እንጀራውን እንደረሳሁ ትዝ ያለኝ ! ወደውስጥ ገብተው በተመለሱ ቁጥር አንዷ ከሌላኛዋ ይምታቱብኛል …ዋናው ነጥብ ሲንግል የተባለችውን ላለመርሳት መሞከር ነው እላለሁ ለራሴ…ለምልክት ቀሚሷን ቀይ ወጥ ላስነካው ይሆን ….! ግን ነገሩ ቀይዋን ያየ የሚሉት አይነት የካርታ ጨዋታ ነበር …ተበወዙብኝ …ውር ውር ውር ያገባች ያላገባች ፕሮሰስ አሳይለም! የቷ ናት ሲንግል ይለኛል አእምሮየ …ይች ነቻ እላለሁ …ተሳሳትክ ይች የፍሬው ሚስት ናት!
ሲንግሏ ናት ብየ ያሰብኳትን ፈገግ አልኩላት ፈገግ አለች …ብሬስ ! እንዴት ነው ታዲያ አገሩን ለመድሽው … ኦ እኔ አይደለሁምኮ የመጣሁት …የት ሄደች ቲጅ ናት … ተሳሳቅን! ቆይቸ ቲጅን አገኘኋት ብየ ወሬ ስጀምር ቶማስ መጥቶ አብርሽ ተጫዎት ተዋወቃችሁ?…ናኒ ባለቤቴ ነች ! እንዲቹ እንደተምታታብኝ ‹‹የታለች ሲንግሏ ቲጅ ? መልሳችሁ.... ወደአገር ቤት ላካችኋት እንዴ ? ….›› ብየ ልጮህ ምንም አልቀረኝም በሰው አገር ሰንደል ፀጉሬ ላይ ሰክቸ ከመዞሬ በፊት ማሰቡትን ትቸ ሰሀኔ ላይ አቀረቀርኩ! ምናይነት ፊዚክስ የሆነ ቤተሰብ ነው?! ተሰናብቸ ስወጣ አክስታቸው …ከተል ብላኝ በቁም ነገር …
‹‹እኔ የምልህ አብርሽ …. ትንሽ አትጫዎትም ነበር? ….
‹‹ሌላ ቀን እመጣለሁ ››
‹‹ መምጣትማ አለብህ ! አንግዳዋን እናተ ካላላመዳችኋት ማን ያላምዳታል?! …ካለች በኋላ ወደዋናው ነጥቧ ገባች! እየውልህ …ሰው በቁሙ ካልተጠቃቀመ መቸም በኋላ እየየ ምን ያደርጋል …አንድ ነገር አስቤኮ …አንድ እህታቸው ብቻ አገር ቤት ቀርታለች … ለፕሮሰስ ለማን ልዳራት ብየ ሳስብ አንተ ትዝ አልከኝ … ባይሆን ያንተን እህት ደግሞ አንዱ የኔ ልጅ አግብቶ ያመጣታል !
ሲንግል ናት …? አልኩ (እስቲምናገባኝ)
ኧረ አግብታ ሁለት ወልዳለች …ባሏ በካቦ ቢጎትቱት ከዛ አገር የሚንቀሳቀስ አይነት አይደለም እንጅ ! እንዴት ያለች ቆንጆ መሰለችህ …መዓዚየ! ይች ሴትዮማ በአሳይሎም ቀርታ እንጅ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሳትሆን አትቀርም ! …ወደቤት ስመለስ መንገድ ላይ የትኛው መስመር የኔ የትኛው በተቃራኒ መስመር የሚመጣው መኪና እንደሆነ ብዥዥዥዥዥዥዥዥ …ጭራሽ የተሳሳተ ሰፈር ገብቸ አረፍኩ! ጂፒኤስ ለመጠቀም ስልኬን አወጣሁ…. ስልኬ በፓስወርድ ጥርቅም ተደርጎ ተዘግቷል ….ፓስወርዱን ምን ነበር ? ….አዎ forgot password is my password!

#Share
#AlexAbreham

JOIN
@AlexAbreham
2.2K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ