Get Mystery Box with random crypto!

ሳብ ሳብ አረጉ በኛ ላይ ሊነዱ እስኪ እናየዋለን ካስኬደ መንገዱ ምን ያለ እንዝርት ነው ወልቆ የ | Μ@ አል_ሪጃሉላህ_የሐድራ_ጀመአ

ሳብ ሳብ አረጉ በኛ ላይ ሊነዱ
እስኪ እናየዋለን ካስኬደ መንገዱ

ምን ያለ እንዝርት ነው ወልቆ የሌለው
ሁሉም ስብሰባ አለ ጠባቂው ማነው

ሀገሬ ላይ ሆኜ ናፈቀኝ ሀገሬ
ሰው ማን ጋር ይኖራል ሁሉም ሆኗል አውሬ

እኔ ለ እርሱ ብዬ ጧት ማታ ስለፋ
ታጥቆ ብድግ አለ ሊዶለኝ እፈፋ

ሳዳቶቹ መጀን ሁለት አይኑ ይጥፋ

እመንገዱ አጠገብ አንድ ቤት ነበረኝ
አላፊው አግዳሚው (የ አፈር ሰው) ያፈርሰው መሰለኝ

ይቅር ይቅር ያለው መጅሊስ እንዴት ይቅር
ሊቃው እንዴት ይቅር
የተለዩ ግዜ የሚለው ቅር ቅር

እኩሉም ጊንጥ ነው እኩሉም ሀየት
ሲገናኙ ትዝብት ሲለዩም ሀሜት

ተደባልቆበታል ሀቅ እና ባጢሉ
እብዱ ተወደደ ተጠልቶ አቂሉ

ወንዱ አውገረድ ሆኖ ሴቱ ሆኗል ባሉ

ያንድኛው ንግግር ላንድኛው መች ጣመ
ከቶም ያጠፋዋል እየቆለመመ

ሁሉም ሰው ነኝ ብሎ ጥምጣም ጠመጠመ
አፈኛው ዝም ብሎ ዲዳው አጣጣመ
ውሸቱን ሊናገር አፉን ቆረጠመ
ሁሉም ተጎዳ እንጅ መቼ ተጠቀመ

ያንበሳውን ግልገል ያዙት በሰንሰለት
አድኖ እንዳይበላ ያን ያባቱን ሀለት

ድንጋይ ተንከባሎ ያርፋል ከተመቸው
የሚመጣውን ቀን ጭራሹን አይቼው

የድንጋይ ስርባት በእጅ አይመዘዝም
የሚመጣን ወራት እንዲያው ዝም እንዲያው ዝም

ሸህ አደም ደርቃ