Get Mystery Box with random crypto!

አል- በረካህ የሐድራ ጀመዓ (ቡታጂራ)ቻናል❤💚❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ al_berekah_jema_channel — አል- በረካህ የሐድራ ጀመዓ (ቡታጂራ)ቻናል❤💚❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ al_berekah_jema_channel — አል- በረካህ የሐድራ ጀመዓ (ቡታጂራ)ቻናል❤💚❤
የሰርጥ አድራሻ: @al_berekah_jema_channel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 483
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኢስላማዊ ስነ ፅሁፎች - ግጥሞች ወጎች አነቃቂ መልዕክቶች ታሪኮችን ያገኛሉ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ ለአስተያየት እና ለጥቆማ @BI_JAHIL_MURSELA
@Al_Berekah_jema_channel👈👈👈👈👈

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-14 17:22:28 #ኸሚስ

#ኸሚስ ላይ ስራቹ ወደ አላህ ይቀርባል ስባል የሳምንት reporቴ በአመፅ መንጋጋቱ ያሳፍረኛል። ከመማማር አልፎ ኸሚስ ላይ የነፍስያዬን ሂሳብ ማወራረድ ይቀናኛል ፤ ደስታ የማያምርባት ነፍሴ ደግሞ ዘወትር ትዋትታለች። ብዙ ሀዘን ከመሸከሟም ጋር ሀሴት ግን ያስፈራታል። የሀሴት ሸክሙ ከባድ ነው ስል እመኑኝ። የፌሽታ ጭነቱን ይዞ ሲግተለተል ያሸማቅቃል።
*

ብኩን ነን። ሁሌ ጌታችንን በማስቀየም ላይ ምንታትር። ጀምበር ወጥታ እስክትገባ ከኩነኔ ማንርቅ። ራሱ በሞላልን ፀጋ ራሱን ምናምፅ በልቶ ካጆች። ታዲያ በምን መስፈርት ደስታ ለኛ ተገባች?! እያመፅኩት ሚውልልኝ ጌታዬን ለምን አላፍረው?!
*

ብዙ ግዜ መጠየቅ አልወድም ከጠየኩኝ ግን ሁሌም "ለምን?" ብዬ ነው የምጠይቀው። ጌታዬ ለምን?! አላህዋዬ ለምን ታሞላቅቀኛለህ?! የራሴን ጉድፍ እንዳልሸሽግ ለምን በክብር ከፍ አድርገህ ፀፀቴን ታገዝፍብኛለህ?! ለምን?!
***

ህይወቴ ላይ ምንም ነገርን እንደ ወታደር ዝግጁ ሆኜ ነው የምጠብቀው። የመከራ ዶፍ ቢወርድ እንኳ ጌታዬ ያበረታኛል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። ሀሴትን ግን የሚሸከም ትከሻ አላዳበርኩም ፤ የአላህዬን ውለታ እፈራለሁ። ነገ " ይሄ ሁሉ አድርጌልሽ ለኔ ይሄ ይገባኛል? " ብሎ ወደ ወንጀሎቼ ሲያመላክተኝ ምን ይውጠኛል?! ዋ ነፍሴ ተይ ተመከሪ ተይ...
47 views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:52:13 ።።።። ሙሐመድ የላቀው።።።።

ሙስጦፋየ ብየ በስሙ ላውጣጣው
ያንን የከውኑን ኑር ያን ያዘል ባለ እጣው
ሚሳሉ ያልተመጣ ከፊትም ማይመጣው
ጀሊል በረህመቱ ለረህመት አወጣው
ጀማሉ ሚቃጣው ሩሃችን ሊሰርቀው

።።።።።።ሙሐመድ የላቀው።።።።።።።።።

ከመቅለል አይደለም የኔ መቅለብለቤ
የማይቻልን ስም ላልችለው መሳቤ
ሰይዲ ባንቱ አይደል ያማረልኝ ክትቤ
ባንቱው ሾለ ብዕሬ ባንቱው ሻረ ልቤ
አዟሪቱን ላንቱ አዙሬ ብለቀው

።።።።።።። ሙሐመድ የላቀው።።።።።።።።


☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
74 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:59:29 ከተውበት የበለጠ ምልጃ የለም ።

ከጤንነት የበለጠ ያማረ ልብስ የለም ።

ከተቅዋ በላጭ ተግባር የለም ።

ከኢስላም የበለጠ ክብር የለም ።

የድህነት ጌጥ ትዕግስት ሲሆን የሀብት ደሞ ምስጋና ነው ።

@Al_Berekah_jema_channel
@Al_Berekah_jema_channel
71 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:36:52 ጤንነት አስር ክፍሎች ሲኖሩት ......

-ዘጠኙን ዝምታ ዉስጥ ታገኘዋለህ (አሏህን ማውሳት ሲቀር )።

- አንዷን ደሞ ከቂላቂሎች ስብስብ በመራቅ ታገኘዋለህ ።
65 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:29:44
64 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:21:13 <<<ከዓሊሞች ጋር ከሆንክ >>>

-ከጥርጣሬ ወደ እርግጠኝነት

- ከእዩልኝ ወደ ፍፁምነት

- ከዝንጉነት ወደ ማስታወስ

- ከዱንያ ክጃሎት ወደ አኼራ ፍላጎት

-ከኩራት ወደ መተናነስ

- ከመጥፎ አስተሳሰብ ወደ ቅንነት ትሸጋገራለህ ።
63 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:14:43 ስንቅ የፈለገ ፦ አሏህን መፍራት ይበቃዋል ፣

ልዕልና የፈለገ ፦ እስልምና ይበቃዋል ፣

ፍትህን የፈለገ ፦ የአሏህ ፍርድ ይበቃዋል ፣

አጫዋች የፈለገ ፦ አሏህን ማስታወስ ይበቃዋል ፣

አቀማማጭ የፈለገ ፦ ቁርዓን ይበቃዋል ፣

መካሪን የፈለገ ፦ ሞት ይበቃዋል ፣

ሀብትን የፈለገ ፦ መተናነስ ይበቃዋል ፣

ጌጥን የፈለገ ፦ እውቀት ይበቃዋል ፣

ቁንጅናን የፈለገ ፦ ጥሩ ፀባይ ይበቃዋል ፣

እረፍትን የፈለገ ፦ አኺራ ይበቃዋል ፤

ይህ ሁሉ ያልበቃው እሳት ይበቃዋል

አሏህ ከእሳት ይበቃዋል ።

@Al_Berekah_jema_channel
@Al_Berekah_jema_channel
61 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:33:36 pp የሚሆኑ ኢስላማዊ ጥቅሶች ፣ ግራፊክሶች እና ፒክችሮች አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት ኢስላማዊ የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ?
ሓዲሶችስ ይፈልጋሉ
63 views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:39:02 በእኔነቴ ፀንቶ ጀሠዴን ሠንጥቆ ሊገለኝ የዳዳ ፣
አንድ ሙሀባ አለ የናፍቆቱ ፍሙ አካል ሚያፈነዳ ።
58 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ