Get Mystery Box with random crypto!

#ኸሚስ #ኸሚስ ላይ ስራቹ ወደ አላህ ይቀርባል ስባል የሳምንት reporቴ በአመፅ መንጋጋቱ ያ | አል- በረካህ የሐድራ ጀመዓ (ቡታጂራ)ቻናል❤💚❤

#ኸሚስ

#ኸሚስ ላይ ስራቹ ወደ አላህ ይቀርባል ስባል የሳምንት reporቴ በአመፅ መንጋጋቱ ያሳፍረኛል። ከመማማር አልፎ ኸሚስ ላይ የነፍስያዬን ሂሳብ ማወራረድ ይቀናኛል ፤ ደስታ የማያምርባት ነፍሴ ደግሞ ዘወትር ትዋትታለች። ብዙ ሀዘን ከመሸከሟም ጋር ሀሴት ግን ያስፈራታል። የሀሴት ሸክሙ ከባድ ነው ስል እመኑኝ። የፌሽታ ጭነቱን ይዞ ሲግተለተል ያሸማቅቃል።
*

ብኩን ነን። ሁሌ ጌታችንን በማስቀየም ላይ ምንታትር። ጀምበር ወጥታ እስክትገባ ከኩነኔ ማንርቅ። ራሱ በሞላልን ፀጋ ራሱን ምናምፅ በልቶ ካጆች። ታዲያ በምን መስፈርት ደስታ ለኛ ተገባች?! እያመፅኩት ሚውልልኝ ጌታዬን ለምን አላፍረው?!
*

ብዙ ግዜ መጠየቅ አልወድም ከጠየኩኝ ግን ሁሌም "ለምን?" ብዬ ነው የምጠይቀው። ጌታዬ ለምን?! አላህዋዬ ለምን ታሞላቅቀኛለህ?! የራሴን ጉድፍ እንዳልሸሽግ ለምን በክብር ከፍ አድርገህ ፀፀቴን ታገዝፍብኛለህ?! ለምን?!
***

ህይወቴ ላይ ምንም ነገርን እንደ ወታደር ዝግጁ ሆኜ ነው የምጠብቀው። የመከራ ዶፍ ቢወርድ እንኳ ጌታዬ ያበረታኛል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። ሀሴትን ግን የሚሸከም ትከሻ አላዳበርኩም ፤ የአላህዬን ውለታ እፈራለሁ። ነገ " ይሄ ሁሉ አድርጌልሽ ለኔ ይሄ ይገባኛል? " ብሎ ወደ ወንጀሎቼ ሲያመላክተኝ ምን ይውጠኛል?! ዋ ነፍሴ ተይ ተመከሪ ተይ...