Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 60.07K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-10 10:01:50 “ሶስት ጁምዓዎችን ያለ በቂ ምክንያት የተወ ከሙናፊቆች ተደርጎ ይመዘገባል።”

ረሱል ﷺ
11.5K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 18:27:37
Iyyaafannoo!

Dargaggoon asii gaditti argitan kun Kaashif Abbaaraayyaa Abbaaluleessaa jedhama. Dhalataa Godina Jimmaa Aanaa Saqqaa Coqorsaa Ganda Gurraa Ulaa'ukkee yoo tahu, dhibee sammuu isa mudateef qoricha fudhachuuf Magaalaa Adaamaa kutaa magaalaa Bokkuu shanan Aanaa Torban Oboo dhufee, gafa Guyyaa Sanbata Xiqqaa jechun 11/08/16 tti naannoo sa'aa 8:00 erga bahee hin deebine.

Yeroo manaa bahu kanas T-Shartii magariisaa fi marxoo kan uffate yoo ta'u, Namni nama kana argitan nuuf eeraa gatii dadhabbii keessanii ni kaffalla jedhu maatiin isaa

Lakkoofsa bilbilaa eeruun itti kennamu:
0911060786
0963455574
0985679812
0938531237
0917833073
15.4K views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 13:52:16
አፋልጉን
————
ይህ በፎቶ የምትመለከቱት ወንድማችን ስሙ ኸይሩ ሁሴን ይባላል። ትላንት ሰኞ 9:00 ከካራ ስልጤ ሰፈር ከሚኖርበት ቤት እንደወጣ አልተመለሰም። ትንሽ የአእምሮ ታካሚ የሆነ ነው። ይህ ወንድማችን ያየ ወይምH ያለበት የሚያውቅ
በ 0965593789 ወይም
በ 0921058046 ቢያሳውቁን ይላሉ
ቤተሰቦቹ
13.5K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 17:02:31 ባለፉት 29 ዓመታት የህገ-መንግስቱን ግልጽ ድንጋጌዎች ሆንብሎ ያለአግባብ በመተርጐም ሙስሊሙ ማህበረሰብ በልዩነት ሲጠቃባቸው የነበሩና ማህበረሰቡም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያቀርብባቸው የነበሩ መመሪያዎችና አሰራሮች መወገድ ሲገባቸው በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በድጋሚ ተካተው መገኘታቸው በህዝብ ዘንድ ከወዲሁ እየፈጠረ ያለው ከፍተኛ የስጋት ስሜት ለወደፊቱም ከሀገር ደህንነትና ሰላም አንፃር የሚያመጣውን ውጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣

አዋጁ በብስለትና በስክነት ታይቶ ተጨባጭ የሆኑ የጥናት ውጤቶች ተንፀባርቀውበት፣ ከገዳቢነት ይልቅ መብት ማስከበርን መርሁ ያደረገ አዋጅ እንዲሆን እንደገና እንዲከለስና ተጨማሪ ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት እንዲወጣ ያለንን አቋምና ስጋት እየገለፅን ም/ቤታችን ከዚህ አንፃር የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎትና መብት እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ ቢካተቱ የሚላቸውን ገንቢ ሀሳቦች በዝርዝር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚያቀርብ መሆኑን እያሳወቀ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ረቂቅ አዋጁ እንደ ተቋም በፅሁፍ እንዲደርሰን ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡
“ከሰላምታ ጋር”
13.8K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 17:02:31 የሃይማኖት ጉዳይን አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የም/ቤታችንን አቋም ስለማሳወቅ፤


ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሃይማኖት መገኛ ሆና ሳለ ለዘመናት የሃይማኖቶች እኩልነትና የሐገር ባለቤትነት ጉዳይ ከሙስሊሙ አንፃር ሳይረጋገጥ በመኖሩ እስልምና እንደ ሃይማኖት ሙስሊሙ ማህበረሰብም እንደ ዜጋ ከፍ ያለ ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝበ ሙስሊሙ ከንጉሳዊው የአስተዳደር ዘመን ጀምሮ መንግሰትና ሃይማኖት የተለያዩ እንዲሆኑና የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዲከበር መራር ትግል ሲያደርግ ቆይቷል።

ከዚህም በመነሳት ሙስሊሙ በታላቁ የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብዮት ዋነኛ ተሳታፊ ነበር። አብዮቱ ካስገኛቸው ድሎች አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግስትና የሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸው የተደነገገበት የደርግ ዘመን 1979 ህገ መንግሰት ተጠቃሽ ነው። ይሁን እንጂ መብቱ በህገመንግሰት ይካተት እንጂ በተግባር ስራ ላይ ሳይውል ጭቆናው ቀጥሎ ቆይቷል። በአንፃራዊነት በ1983 የነበረውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት በ1987 ፀድቆ እስከ አሁንም በስራ ላይ የሚገኘው የኢፊዴሪ ህገ-መንግስት በግልፅ በመቀመጡ ከቀድሞ የተሻለ ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ነገር ግን ህገ-መንግስቱ ውስጥ በመርህ ደረጃ የተቀመጡትን የመንግሰትና ሐይማኖት መለያየት እንዲሁም የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት መብቶችና መሰረታዊ መርሆዎችና ድንጋጌዎች ለማስፈፀም የሚውሉ ዝርዝር ህጎች ሳይወጡ በመቆየቱ ምክንያት መብቶቹን በምሉዕነት መጠቀም አልተቻለም። ይባስ ብሎም አንዳንድ ተቋማት ህገመንግሰታዊ የሆነውን የመንግሰትና ሃይማኖት መለያየት መርህ ያልተገባ ትርጉም በመስጠት ለአድሏዊ አሰራር ሲያዉሉት ተስተውለዋል። አንዳንድ ተቋማትም የህገ-መንግስቱን ግልፅ ድንጋጌዎች የሚቃረኑ፤እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ኢላማ ያደረጉ ደንቦች፤መመሪያዎችንና አሰራሮችን በመዘርጋት ህዝባችን ላይ ጥቃቶችና በደሎች ሲያደርሱበት በስፋት ተስተውለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብም በተለያዩ ጊዜያት እነዚህ በደሎችና ጥቃቶች በዘላቂነት ሊያስቆሙለት የሚያስችሉና ህገ መንግስተዊ መብቱን በምሉዕነት እንዲገለገልባቸው የሚያስችሉ ዝርዝር ህጎች በአግባቡ እንዲወጡና ስርዓት ያለው ወጥ አሰራር እንዲኖር ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

ከዚህም በመነሳት የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህገመንግስታዊውን የመንግስትና ሃይማኖት መለያየት መርህን እንዲሁም የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነትን በዝርዝር ለማስፈፀም አዋጅ መውጣቱን በመርህ ደረጃ ይደግፈዋል። ይሁን እንጂ ከአዋጁ ረቂቅ ዝግጅት ጀምሮ ህጉን ለማውጣት እየተኬደበት ያለው ሂደትና ፤የረቂቅ አዋጁ ይዘትን አስመልክቶ ከሰሞኑ እየተስተዋለ ያለውን የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎትና ስጋት በእጅጉ ይጋራል።

ምክር ቤታችን መንግስት ሊያወጣው ያሰበው ረቂቅ አዋጅ እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ወኪልነቱ እንደዚ ያሉ መመሪያዎች ባለመኖራቸው የተነሳ በሙስሊሙ ላይ ይደርሱ የነበሩትን ያልተማከሉ ነገር ግን የተቀናጁ የሚመስሉ ጥቃቶችን በወጥነት ያስቆማል ብሎ ስለሚያምን ለአዋጁ ያለውን ድጋፍ ከወዲሁ መግለፅ ይፈልጋል። በአዋጁ ላይ ያሉንን አስተያየቶችና ስጋቶች የምንገልፀውም የመንግስትን ፍላጎት ወይም አላማ በመጥፎ በመረዳት ሳይሆን በሀገራችን የህግና የአዋጆች መውጣት ታሪክ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎችና ጥቅሞች የማይገናዘቡበት የቆየ አሰራር በመኖሩ አንዳንድ ለኛ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን አንድም ባለማወቅ ወይን ደግሞ በግለሰቦች የተለየ ፍላጎት የተነሳ ቸል ሲባሉ እና ሙስሊሙን ተጎጂ ሲያደርጉ በመኖራችን ስጋት ስላለን መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ይህ የአማኞች ሀገር በምትባለው ሀገራችን ሊወጣ እየተዘጋጀ የሚገኘው አዋጅም የሃይማኖትን እኩልነት፣ የመንግስትና የሃይማኖትን መለያየት በተለያዩ ጊዜያት በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተለይም ደግሞ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ ሙስሊም ሰራተኞችና ባለስልጣናት ላይ ይደርስ የነበረውን ግልጽ የሆነ ተቋማዊና ግለሰባዊ የሆነ የበደልና የጥቃት ተግባራትን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍ መሆን እንዳለበት ም/ቤታችን ያምናል፡፡

ከዚህ አንፃር በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ እየተነሱ ካሉ የህዝባችን ሃሳቦች በመነሳት ምክር ቤታችን በተወሰነ መልኩ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ረቂቅ አዋጁ እነዚህን ነባር ችግሮች ከመቅረፍ ይልቅ የሚያባብሱና ተጨማሪ ችግሮችን የሚያስከትሉ አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዳሉበት ለመገንዘብ ችሏል።

በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በተደረገው ውይይት መሠረት ሰፋ ያለ የሙስሊሙን መብት የሚመለከቱ ጉዳዮችን በዝርዝር የሚያቀርብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ጠቅላይ ምክር ቤታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጉዳዮች ላይ ያለውን ጥብቅ አቋምና ስጋት ለማቅረብ ይወዳል፡-

1. ምንም እንኳን ህግ መውጣቱ የምንፈልገውና የቆየ የህዝባችን ጥያቄ ቢሆንም የእምነታችንን የተለዩ የአምልኮ ባህሪያት ግምት ውስጥ ሳያስገባ በስመ እኩልነት ብቻ ከሌሎች ሃይማኖቶች የአምልኮ ስርዓት ጋር በማነፃፀር እዚህም እዚያም ከልክለናል በሚል የተሳሳተ መነሻ የተቀረፀው እንዲሁም በእምነታችን የአምልኮ ስርዓት ውስጥ በመግባት አንድ ሙስሊም በእምነቱ የታዘዘውን የአምልኮ ተግባር እንዴት ማከናወን እንዳለበት እሰከመምረጥ ድረስ ገደብ ለመጣል በሚሞክሩ አናቅፅ የተሞላ ረቂቅ አዋጅ መሆኑ ተገቢ ስላልሆነ ፣

2. የሃይማኖትና የአማኞች ሃገር ናት የምትባለውን ሃገራችንን ሃይማኖታዊ እሴቶች ከማጎልበትና ሃይማኖቶችን ለሃገራዊ አንድነትና እድገት በአዎንታዊነት ከመጠቀም ይልቅ የሀገራችንን ተጨባጭ ባለማገናዘብና ወደጐን በመተው እምነቶችን በበማዳከም ለሃገር ከሚያበረክቱት ገንቢ አስተዋፅኦ የማግለል ባህሪ ያለው በመሆኑ ፣

3. ሃገራችን ህብረ ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት የምትከተል እንደመሆንዋ በተለያዩ ክልሎች በመሬት ላይ ያለውን እውነታ በፍፁም ከግምት ውስጥ ያልከተተና ተፈፃሚነት የሌለው ህግ እንዳይሆን የሚያሰጋ በመሆኑ፣

4. ረቂቅ አዋጁ በመሠረቱ አንድ ህግ ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚወጣበትን መርህ በመጣስ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን የእምነት መብትና ነፃነትን ከማስፈፀም ይልቅ መገደብ ላይ በማተኮር የአለም አቀፍ ህጐችንና ህገ መንግስታችንን የሚቃንኑ ሀሳቦች ያሉበት በመሆኑ ፣

5. የመንግሰትና ሃይማኖት መለያየት መርህ ዋና አስኳል የሆነውን የመንግስትን በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ሁኔታ ከመገደብ ይልቅ፤ያለአግባብ መንግሰት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ መግባትን የሚያበረታታና መንግስት የሀይማኖቶች ተቆጣጠሪ የማድረግ ባህሪ ያለው በመሆኑ ፣

6. ሕገመንግስታዊውን የሃይማኖት ነፃነትን ከማስከበር አንፃር የእምነታችንን ልዩ የአምልኮ ባህሪያት በመረዳት ለዚያ የሚመች ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ አምልኮዎችን መከልከል ላይ ማተኮሩ፣

ለምሳሌ፡- በት/ት ቤቶች እና በመንግስት ተቋማት አካባቢ ሙስሊሙ ግዴታ የሆነበትን ሰላትና የሴቶች አለባበስ ሁኔታ የመከልከልን ባህሪያት የተሞላ መሆኑ ፣

7. የመንግስትና የሃይማኖትን መለያየት አስመልክቶ ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት ተደርገው የነበሩ ጥናቶችን ውጤትና ምክረ ሃሳቦች ወደጐን በመተው ህግ አርቃቂዎቹ አካላት በተቃራኒው ለመሄድ የመረጡበት አግባብ ትክክል አለመሆኑ ፣
13.0K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 18:52:23 ሑጃጆች በያዙት የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን መጅሊስ አስታወቀ

ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 28 - 2016 | ሸዋል 27 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች በያዙት ስልክ ቁጥር የ“ሮሚንግ” አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን በዛሬው እለት አስታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች እንደሰማው አገልግሎቱን የሚያገኙ ሑጃጆች በኢትዮ ቴሌኮም መስመር የሚጠቀሙ ደንበኞች ናቸው።

ለዘንድሮው 1445ኛ ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን 12 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ወደ መካ እንደሚጓዙ “ሚንበር ቲቪ” መዘገቡ ይታወሳል። መጅሊስ እነዚህ ተጓዦች በያዙት የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር መደወል እና ጥሪ መቀበል እንደሚችሉ ገልጿል።

ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ሲጓዝ 100 ደቂቃ መደወል የሚያስችላቸው የአየር ሰዓት እንደተዘጋጀላቸው ታውቋል።

መጅሊስ ለኢትዮጵያውያን ሑጃጆች አገልግሎቱን ለመስጠት ስምምነት የፈፀመው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር መሆኑንም የመጅሊስ ኃላፊዎች ገልፀዋል። መንግሥታዊው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ በሚያቀርበው የ“ሮሚንግ”  አገልግሎት ደንበኞች ከኢትዮጵያ ውጭ ሆነው በያዙት የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ የድምጽና የአጭር ጽሑፍ መልእክትን መቀበልና መላክ ያስችላቸዋል።
12.9K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 20:46:41 “በድብቅ የሚሰጥ ሰደቃ ‘ምፅዋት’ የጌታን ቁጣ ታበርዳለች።”

ረሱል ﷺ
13.7K viewsedited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 21:28:25 “በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። አስር ሀጢያቱን ይሰርዝለታል። ደረጃውን በአስር ከፍ ያደርግለታል።”

ረሱል (ﷺ)
18.1K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 22:13:34 “ከናንተ አንዳችሁ ለግብዣ ከተጠራ እሺ ይበል (ይሂድ)።”

ረሱል ﷺ

ቡኻሪ ዘግበውታል: 5173
17.2K viewsedited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 12:09:45
ስለ ወለጋ 100 ጊዜ ብፅፍም ውንጀላው የሚቆም አይደለም
17.7K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ