Get Mystery Box with random crypto!

የArabsat/Badr 26°E አሰራር ውድ ተከታታይዎቻችን ሰላም ለናንተ ይሁን! እስቲ ስለ A | AGARO DISH📡AND TECH.INFO/አጋሮ ዲሽና ቴክ መረጃ

የArabsat/Badr 26°E አሰራር
ውድ ተከታታይዎቻችን ሰላም ለናንተ ይሁን!
እስቲ ስለ Arabsat26°E/Bein Sport ያለበትን/ ሳተላይት እንዴት መስራት እንዳለብን ትንሽ ልበላችሁ።
ይህ ሳተላይት የBein Sport እንጂ ሌሎች ብዙም ለኛ የሚያስፈልጉን ቻናሎች አለበት ብዬ አላስብም።
ለማንኛውም ወደ አሰራሩ ስንገባ
ከዚህ በፊት እንዳልነው የትኛውንም ሳተላይት ስንሰራ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ሳተላይቱ የለበትን ዲግሪ(°) መሆኑን አትዘንጉ።
ለምሳሌ ናይልሳት በ7°ምዕራብ/West ላይ ነው የሚገኘው። የየትኛውም ሳተላይት መነሻ ደግሞ ምዕራብ/West ነው። ለምሳሌ Eutelsat 7°E ስንሰራ ሰሀናችንን ከናይልሳት ትንሽ ብቻ ነው ወደግራ አርገን ከፍ የምናረገው።
ይህ የሚያሳየን  የምንሰራው ሳተላይት በEast Direction ከሆነ ዲግሪው ሲጨምር ሰሀናችንን ወደግራ እያረግን ከፍ እንደምናደርገው ነው።
ወደ ርዕሳችን ስንመጣ፦
Arabsatን ለመስራት የሚያስፈልጉንን ማቴሪያሎች እናዘጋጃለን፤ ማለትም አንድ ሰሀን(ከናይልሳት ሌላ)፣ አንድ ተጨማሪ LNB እና አንድ HD ዲኮደር(ረሲቨር) ናቸው።
በመጀመሪያ ስራችንን ለማቃለል ናይልሳት እንሰራለን(11512V27500) በመቀጠል የናይልሳትን Q. ካገኘን በኋላ እዛው ሰሀኑን በማሰር ረሲቨራችን/ፋይንደራችን ላይ 11919H27500 እንሞላና ከሰሀኑ ኋላ በመሆን ሰሀናችንን 15°ዲግሪ አካባቢ ወደ ግራ እናረጋለን ከዛ ትንሽ ከፍ ማድረግ ነው Quality ወዲያውኑ ከች ይላል።
@agarodishinfo