Get Mystery Box with random crypto!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አቅጣጫው ወዴት ነው 'የዘፈን ዳር ዳርታው ለእስክታ ነው' ይላሉ አንዳንድ | 💠 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አቅጣጫው ወዴት ነው

"የዘፈን ዳር ዳርታው ለእስክታ ነው" ይላሉ አንዳንድ ሰዎች ሲተርቱ እውነት ነው፣ በሃይማኖት ስም የሚነግዱ ሰዎች አሉ። ሰዎች እንጅ የሃይማኖት ተቋማቱ ግን ሌብነት ፅዩፍ እንደሆነ በፈጣሪም ዘንድ ኃጢአት መሆኑን ነው የሚያስተምሩት። ምን ዓይነት የኦዲት ህግ ልታወጡ ነው? እንደ እኛ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ሌቦች ቢኖሩም ቤተክርስቲያን ግን የምትተዳደረው በአስራት በኩራትና ምዕመናን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚለግሱት ገንዘብ ነው። መንግስት ለሃይማኖት ተቋማት በጀት ለመመደብ አስቦ ነው? ወይስ ከአስራት በኩራትም ከሚሰበሰብ ገንዘብ ታክስ ለማስከፈል ታስቦ ነው? ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዛሬ በዋለው ፓርላማ ይህንን ተናግረዋል።

"የሃይማኖት ተቋማት የሌብነት ወንጀል እየተስፋፋባቸው ከመጡ ተቋማት መካከል ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በኋላ የህግ ማዕቀፍ ተበጅቶ እያንዳንዱ የህዝብ ሃብት በትክክል መዋሉን ለማረገጋገጥ የሚያስችል የኦዲት ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሁሉም ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ መሰል የሌብነት ወንጀሎች በማጋለጥ እና ኃላፊነትን በንፁህነት በመወጣት ኢትዮጵያን መድረስ ከሚገባት የልእልና ደረጃ ላይ ማድረስ አንደሚገባም ተናግረዋል"

እኛም እንደ አንድ የቤተክርስቲያን ልጆች ትናንትም ዛሬም ነገም በእኛ ቤተክርስቲያን በኩል በራሱ በጠቅላይ ቤተክህነቱ የሚመራ ጠንካራ የኦዲት ክፍል መኖር አለበት የሚል ጠንካራ አቋም አለን። መንግስት ግን በቤተክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት ላይ እጁን ማስገባት የለበትም።

ለበለጠ join
@ETHIOPIA_Hagerie

@Afe_Werk