Get Mystery Box with random crypto!

አይነጣጠሉም በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብዩ ሙሐ | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

አይነጣጠሉም

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ይሁን።

1) ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣
2) አላህ ቁርአንን በታማኙ የመላእክቶች አለቃ ጂብሪል አማካኝነት ነብዩ ሙሐመድ ላይ አወረደው፣
3) ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለሰሀባዎቻቸው ይህንን መልክት አላህ በሚፈልገው መንገድ በደንም አብራሩላቸው። ይህም ሱና ነበውያ (የነብዩ ሱና) ይባላል።
4) ሙስሊሞች የመተዳደሪያቸው ምንጭ የትም አለም ላይ ይኑሩ ከነዚህ ከሁለቱ አይወጡም።
ከአላህ ቃል ቁርአን እና ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና።
5) ቁርአንን ተቀብሎ ሀዲስ ያልተቀበለ ከኢስላም ይወጣል። ምክንያቱም አላህ ቁርአን ላይ እንዲህ ስለሚል
{وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ }
[Surah An-Nahl: 44]
ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና (ልታብራራላቸው) ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡
ሀዲስ አልቀበልም ያለውን ግለሰብ ከሀዲ ያደረገው አላህ አብራራላቸው ብሎ ያዘዛቸው ነብይ ማብራሪያ አልቀበልም በማለቱ ነው።

አላህ ቁርአን ላይ ያዘዘን ትእዛዛት አፈፃፀማቸውን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነው ያብራሩት።

በየቀኑ የምንሰግደው 5 ወቅት ሶላት አላህ እንድንሰግድ ሲያዘን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አላህ የሚቀበላት ስግድት እያንዳንዱ ሶላት ስንት ረከአ እንዳለው፣ በውስጡ ምን እንደሚባል፣ ከሶላት በኀላ ምን እንደሚባል ያስተማሩት እኝህ መልክተኛ ናቸው።

6) ይህ ቁርአን ሲወርድ ቦታው ላይ የነበሩት ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት ቁጭ ብለው የተማሩ፣ ያልተረዱትን ነገር አላህ በሌላ የቁርአን አንቀፅ መልክቱን እየገለፀላቸው፣ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እያብራሩላቸው፣ የአላህን ውዴታ ያገኙት ሰሃባዎች ናቸው።
7) አላህ ሰሀባዎች በመልካም ፈለጋቸው ከተከተል የእሱን (የአላህ ውዴታ) እንደምናገኝ ነግሮናል።
8) የእነሱ ፈለግ ማለት ቁርአንና ሀዲስን ሰሀባዎች በተረዱበት መንገድ መረዳት ነው። ይሄ ከጥመት ይጠብቃል። የአላህ ውዴታም ያስገኛል። ወደ ጀነት ለመዳረስ አጭሩ መንገድ ይሄ ነው።
9) ያማረ ህይወት በዱናያ መኖር ከፈለግን፣ በአኸይራ ጀነትን በአላህ ፍቃድ ለመጎናፀፍ፣ ከእሳት ለመጠበቅ
– የመጨረሻው መልክተኛ ነበዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የወረደውን ቁርአን ማክበር፣ የህይወት ህግ አድርጎ መውሰድ፣
– የእሳቸውን ሱና ከቁርአን ህግ አለመነጠል፣
– የሶሀባዎች አረዳድ መከተል።

አላህ ለህጉ ከሚያድሩት፣ መልክተኛውን ሙሉ ለሙሉ ከሚከለቱት፣ የወደዳቸው ሰሀባዎችን አረዳድ ከሚረዱት ያድርገን።☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh