Get Mystery Box with random crypto!

ሰባት ነገሮችን አይተህ ሰባት ነገሮችን ፈፅም ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

ሰባት ነገሮችን አይተህ ሰባት ነገሮችን ፈፅም


ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ ጓደኞች ቢኖሩትም ቀብር ሲገባ እንደሚተውት አይተህ መልካም ተግባርን ጓደኛ አድርግ ። መልካም ስራህ እስከመቼውም አይለይህምና ።

《ነፍሱን ከስሜቱ የከለከለ በእርግጥ ጀነት መቀመጫው ናት》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ስሜትህን በአሏህ መንገድ ምራት ። ስሜትህ በመጥፎ እንጅ በጥሩ አታዝህምና ።

《አሏህ ዘንድ በላጩ አሏህን ይበልጥ የሚፈራው ነው》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ አሏህ ዘንድ ቦታ እንድኖርህ ነፍስህን የአሏህን ፍራቻ አስለምዳት ።

《እኛ አኗኗራቸውን ከፋፍልነው (በሀብት ለያየነው) 》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ያንተም አሏህ የወሰነልህ ብቻ መሆኑን አውቀህ ምቀኝነትን ራቅ ።

《 በርግጥ ሸይጧን የናንተ ግልፅ ጠላት ነው》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ ከሰዎች ጋር መናቆርህን ትተህ ጠላትህን ሸይጧንን ብቻ አድርገው ።

《መሬት ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ (ህይወት ያለው) ነገር የለም ፤ የሱ ሲሳይ (ሪዝቅ) አሏህ ጋር ቢሆን እንጅ》 የሚለውን የአሏህን ቃል አይተህ አንተ አሏህ ጋር ያለህን አሏህ ራሱ እንደሚሰጥህ አረጋግጠህ እሱ አንተ ላይ ያለውን አደራ (የዲኑን ህግጋት) ፈፅም ።

《በአሸናፊውና በመሀሪው (ጌታህ) ተመካ》 የሚለውን የአሏህ ቃል አይተህ መመኪያህን አሏህን ብቻ አድርገው ።

《ወንድሜ (እህቴ) ሆይ ከነዚያ ከዝንጉዎች አትሁኑ ። ከነዚያ አሏህን ረስተው አሏህ ነፍሳቸውን ካስረሳቸው እንድሁም ከአዱኒያና ከአኼራ በጎ ነገሮች አሏህ ካራቃቸው አትሁኑ ።》【ያህያ ቢን ሙዓዝ አለይሂ ራህመቱሏህ】

《ለወላጆች ኡፍ ከማለት የበለጥ ወንጀል ቢኖር ኖሮ አሏህ በቁርኣኑ ይከለክለው ነበር ።》【ሰይድና አሊይ ኢብን አቢጧሊብ ረድየሏሁ አንሁ ወአርዷህ 】

《ለወላጆች ዱዓን መተው (ዱዓ አለማድረግ) የልጅን ህይወት ያጣብባል ።》

《ወንድሜ ሆይ አንተ ስትሞት ዓለምን ትገላገላታለህ ወይስ እሷ አንተን ትገላገልሃለች? 》

《ጊዜን ያለምንም ኢባዳ ካሳለፍከው ፥ በዚያ ባለፈው ጊዜም ካልተቆጨህ ልብህ መድረቁን (መበላሸቱን) እወቅ ።》

ጥሩ መፅሀፍ የከፍተኛ መንፈስ ውድ የህይወት ደም ነው ። ከህይወትህ ባሻገር ህይወት በሚሰጥ መዓዛ የተሞላ ታላቅ ሀብት ነው ።》
አላህ ይዘንልን!!!!

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh