Get Mystery Box with random crypto!

ቢድዓ [ፍልስፍና] ➩➪➩➪➩➪➧ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

ቢድዓ [ፍልስፍና]
➩➪➩➪➩➪➧
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

ቢድዓ [ፍልስፍና]
➪➩➪➩➪➩➪

የኛ ሀይማኖት እስልምና የተሟላ እና ጭማሬ የማይፈልግ ሙሉዕነቱ የተረጋገጠ ነው።

الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡
[ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 3]

በአላህ ምስክርነት ዲናችን የተሟላ ነው። ስለዚህ ቢድዓ አያስፈልግም፤ ለምን ከተባለ ሃይማኖታችን ሙሉ ነውና!!!

ለመሆኑ ቢድዓ ምንድን ነው?
➷➘➷➘➷➘➷➷➘➷
ቢድዓ ማለት ቁርአናዊ እና ሐዲሳዊ ማስረጃዎች እንደዚሁም እንደኢጅማዕ ያሉ ትክክለኛ ማስረጃዎች የማይደግፉት እና ለዲን ተብሎ ወይም ወደ አላህ ያቃርበኛል ተብሎ የሚሰራ ተግባር ነው። ዱንያዊ ፈጠራዎች እዚህ ውስጥ አይገቡም።

➲ በዲን ውስጥ አዲስ ነገርን ማምጣት የተከለከለ ለመሆኑ፤ እንደዚሁም አላህ እና መልእክተኛው - ﷺ - ያዘዙንን ተግባር ሳንጨምር ሳንቀንስ መስራት እንዳለብን ከሚጠቁሙ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ ማስረጃዎችን ከብዙ በጥቂቱ እንመልከት፦

وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
[ሱረቱ አል-ሐሽር - 7]

➽ ጌታችን አላህ በዚህ አንቀፅ መልዕክተኛው ﷺ ያመጡትን በቻልነው እንዲንተገብር፤ የከለከሉትንም ከመፈፀም እንዲንቆጠብ ያስገነዝበናል። ቢድዓ ደግሞ መልዕክተኛው ﷺ የከለከሉት ነው።

فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡
[ሱረት አል-ኑር፣ - 63]

➼ የመልዕክተኛውን ﷺ ትዕዛዝ መጣስ መከራ እና አሳማሚ ቅጣት ያከናንባል። ቢድዓ ደግሞ መልዕክተኛውን ትዕዛዝ መጣስ ነውና እንጠንቀቅ!!!

የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"إياكم ومحدثات الأمور فإن كل محدثة بدعة، وكل بدعة ضلالة، وكل ضلالة في النار"
“እናንተንም አዳዲስ ፈጠራዎችንም አስጠነቅቃችኃለሁ፤ ማንኛውም አዲስ ፈሊጥ ፈጠራ ነው፡፡ አዲስ ፈሊጥ ደግሞ ጥመት ነው፤ ማንኛውም ጥመት ደግሞ የእሳት ነው፡፡”
ኢማሙ አህመድና ሌሎችም ዘግበውታል

በሌላ ሀዲስ ደግሞ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈውልናል፦

[من عمل عملا ليس عليه ﺃمرﻧﺎ فهو ﺭﺩ]
["የኛን ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው"]
(ሙስሊም : 1718)

ልብ እንበል ረሱል ﷺ በቢድዓ ላይ አላዘዙንም። ስለዚህ ባላዘዙበት ስራ መሰማራት ስራችንን ተመላሽ ያደርገዋል።

➲ ዒርባድ ኢብኑ ሳሪያህ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ሐዲስ ላይም ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ፦ [አዳዲስ ፈጠራዎችን አደራችሁን ተጠንቀቁ፤ ፈጠራ ሁሉ ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።]
(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)

➩ ቢድዓን አስመልክቶ ከሰለፎች ንግግር የተወሰነ ለመመልከት ያክል፦
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - እንዲህ ይላሉ፦
"ቢድዓ ሁሉ ፈጠራ ናት፤ ምንም እንኳን ሰዎች መልካም ነች ብለው ቢያዩዋትም።"
አልላለካኢይ "ሸርሑስ-ሱንና" 1/92) ላይ ዘግበውታል።

ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
"ተከተሉ፤ አዲስን ነገር (ቢድዓን) አትፍጠሩ፤ በእርግጥም ተብቃቅታችኋል፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው"
አድ-ዳሪሚ 211 ላይ ዘግበውታል።

ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - በሌላ ቦታ እንዲህ ይላሉ፦
"በሱንና ላይ ማሳጠር(መብቃቃት) በቢድዓ ላይ ጥረት(ትግል) ከማድረግ ይበልጣል፤ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።"
አልላለካኢይ "ሸርሑስ-ሱንና" 114 ላይ ዘግበውታል።

ኢማሙ ማሊክ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ውስጥ መልካም አድርጎ የሚያያትን አዲስን ፈጠራ (ቢድዓ) የፈጠረ ሰው፤ በእርግጥም ሙሐመድ - ﷺ - መልእክቱን አላደረሰም በማለት ሞግቷል፤ ምክንያቱም አሏሁ - ተዓላ - [| .. ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡...|] ስለሚል ነው። የዛን ጊዜ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን ሊሆን አይችልም።
"(ኢብኑሐዝም "አሕካም" 2/231 ላይ ኢማም አሽ-ሻጢቢ 1/49)
ላይ ዘግበውታል።

በአጠቃላይ ከቢድዓ አይነቶች በሙሉ መራቅ ይጠበቅብናል። አላህ ከቢድዓ ርቀው በሱንና ጠንክረው እሱን ከሚገናኙ ደጋግ ባሮቹ ያድርገን
https://t.me/Adnan567mh