2023-04-09 10:13:01
ጠ/ ሚ ዐብይ አህመድ ልዩ ሀይልን በሚመለከት ምን አሉ?
*የልዩ ኃይል አባላትን ወደ መከላከያ ወይም ወደ ፖሊስ እንዲገቡ የማድረግ አጀንዳ ለረጅም ጊዜ ሲታሰብበትና ሲመከርበት የቆየ ጉዳይ ነው።
* ጉዳዩ እንዲነሣ ያደረጉት ሁለት ምክንያቶች ናቸው። አንዱ የልዩ ኃይል አባላትን ጥቅማ ጥቅም፣ ዕድገትና ማዕረግ የተመለከተ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ አደረጃጀቱን ምክንያት በማድረግ በተደጋጋሚ ያጋጠሙንን ፈተናዎች የተመለከተ ነው።
* በሀገር ውስጥና በውጭ የሚሰጡ ወታደራዊ ትምህርቶችንና ሥልጠናዎች ሊደርሷቸው ያስፈልጋል። የላቁ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ሊታጠቁ ይገባል። ከፍ ያሉትን ወታደራዊ ማዕረጎች በቆይታቸውና በጀብዷቸው ሊቀዳጁ ይገባል።
*ይህ መሆን የሚችለው ደግሞ ወደ መደበኛ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ማለትም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ አልያም በፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ እና በክልሎች ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ መካተት ሲችሉ ብቻ ነው።
*እነዚህን የመሰሉ በውጊያ የተፈተኑ ኃይሎች በጊዜያዊ የልዩ ኃይል አደረጃጀት ብቻ ወስኖ ማስቀረት ሀገርንም አባላቱንም መጉዳት ነው።
*ኢትዮጵያ ከክልል ልዩ ኃይሎች ጋር በተያያዘ ከአንዴም ሁለት ጊዜ የሀገርን ሉዓላዊነትና አንድነት የተገዳደሩ ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበር አይዘነጋም። ከአንድነትና ሉአላዊነት ሥጋትነት በመለስም በክልሎች መካከል የማያስፈልግ ተፎካካሪነትና ተገዳዳሪነት እንዲፈጠር መንስኤ ሲሆኑ እናያለን።
* ከሕገ ወጥ የኬላ ዝርጋታ፣ ከኮንትሮባንድ፣ ከሽፍትነት፣ ወዘተ ጋር የተያያዙ ፈተናዎችም እየተስተዋሉ ናቸው። እነዚህ ችግሮች የመነጩት ለጊዜያዊ መፍትሄነት የፈጠርናቸውን አደረጃጀቶች እንደ ዘላቂ መፍትሄ መቁጠር በመጀመራችን ነው።
*የክልል ልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በይደር ያቆየንበት ምክንያት ነበረን። አንደኛው የመከላከያ ኃይላችንን በበቂ መልኩ ለማደራጀት ጊዜና ዐቅም ስላስፈለገን ነበር። ሁለተኛው ደግሞ በወቅቱ በሀገራችን ላይ ከተጋረጠብን አደጋ አንጻር እነዚህን መሳይ ሥራዎች ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ ስላልተፈጠረ ነበር።
*ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከሕዝብ ጋር በተደጋጋሚ በተደረጉ ውይይቶች ልዩ ኃይሎች ወደ መከላከያ እንዲጠቃለሉ ሕዝቡ ጠይቋል። የልዩ ኃይል አባላትም ከሜካናያዝድ ሥልጠና፣ ከደመወዝ፣ ከማዕረግ ዕድገት፣ ከትምህርት ዕድሎችና ከሌሎችም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ነገሩን በተደጋጋሚ አንሥተውታል።
*የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ ሲወሰን፣ ተገቢው ዝግጅት ተደርጎበት ነው።
*የልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት እንዲወያዩበት ማድረግ፣ወደ ሌሎች ጸጥታ መዋቅሮች የማስገባቱ ተግባር በሁሉም የክልሎች ልዩ ኃይሎች ላይ እንዲተገበር፣ አባላቱ ወደ መከላከያ፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ወደ ክልል ፖሊስ እንዲገቡ፣ ጉዳዩ የትጥቅ መፍታት ጉዳይ ሳይሆን የበለጠ ሥልጠናና ትጥቅ አግኝተው ሀገርን በተሻለ ወደሚያገለግሉባቸው መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያደርግ መሆኑንና ይሄንን ሥራ ለማደናቀፍ የሚነሡ አካላት እንደሚኖሩ፤ መጀመሪያ በመወያየትና በማሳመን፤ ከዚህ ያለፈ ተግባር የሚፈጽሙ ካሉም ሕግ የማስከበር ሥራ እንዲሠራ የሚሉ ናቸው።
*ዛሬም የየክልሉ ልዩ ኃይሎችን እስከ ዛሬ ለሰጡት አገልግሎት አመስግነን፣ ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የምናካትትበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ይህ ውሳኔ በሁሉም ክልል አመራሮች በጋራ የተወሰነና በጋራ የሚተገበር ነው።
702 viewsedited 07:13