Get Mystery Box with random crypto!

የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀ | Addis mereja

የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፤ በኮቪድ -19 እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ከሐምሌ 20 እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም ምዝገባ በማከናወን፥ ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም መጀመር እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለተማሪዎቻቸው አስቀድመው ጥሪ ያደረጉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ እያደረጉ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለማወቅ ችሏል።

@Addismerja
@Addismerja