Get Mystery Box with random crypto!

Addis mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismerja — Addis mereja A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismerja — Addis mereja
የሰርጥ አድራሻ: @addismerja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56
የሰርጥ መግለጫ

🔴ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራትና ጥቆማ ለመስጠት👇

@ADDIS_MERJABOT
🌟 አዲስ መረጃ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ✔
✔ የYOU TUBE ቻናላችንን SUBSCRIB ያድርጉ👇👇👇👇
https://youtu.be/2KRSJcBNcf4
✔ADDIS MEREJA ET
buy ads:https://telega.io/c/addismerja
© ሰኔ 2011 ተመሰረተ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 20:51:22
የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፤ በኮቪድ -19 እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ከሐምሌ 20 እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም ምዝገባ በማከናወን፥ ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም መጀመር እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለተማሪዎቻቸው አስቀድመው ጥሪ ያደረጉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ እያደረጉ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለማወቅ ችሏል።

@Addismerja
@Addismerja
1.7K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:22:03
በጋምቤላ ከተማ የሠዓት ዕላፊ ተጣለ!

ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በጋምቤላ ከተማ የሚታዩ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የሠዓት ዕላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኅፈት ቤት አስታወቀ።

በመሆኑም በጋምቤላ ከተማ የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሠዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11 ሠዓት 30 ድረስ መገደቡን እና ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ገልጸዋል።

የሠዓት ዕላፊው የድንገተኛ ሕክምና ማመላለሻ አምቡላንስ እና የጸጥታ ኃይል ተሽከርካሪዎችን እንደማይመለከት ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ ከተማ ሠላማዊ ሁኔታ መኖሩን ያመለከቱት ኃላፊው ፣ በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

አቶ ኡገቱ ÷ የጸጥታ ኃይሉ የከተማውን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ኅብረተሰቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ መረጃ በመስጠት ጭምር እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሠዓት ዕላፊ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

@Addismerja
@Addismerja
2.4K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:51:46
"በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል"፦ መከላከያ ሠራዊት

ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ ሰሞኑን በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እየተሽሎከሎኩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀስ በነበሩ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የአሸባሪው ሸኔ ሽፍቶችን በማሳደድ ላይ ከሚገኙ የሠራዊታችን ክፍሎች መካከል የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ሲሆን፤ በኮማንዶ ክፍል ጦር የሠራዊት አዛዥ እንደተናገሩት "የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ የሆነው የሸኔ አባላት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ እርምጃ ተወስዶባቸዋል"።

በዚህ ኦፕሬሽን 5 ኤኬሜ (የክላሽ) ጠብመንጃ፣ 2 የእጅ ቦንብ፣ 200 የክላሽ ጥይት፣ 164 የብሬን ጥይት ከነሸንሸሉ፣ 4 የወገብ ትጥቅ እና 12 የክላሽ ጠብመንጃ መጋዘን ከአሸባሪው ሸኔ እጅ መማረኩንም አዛዡ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@Addismerja
@Addismerja
3.0K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:04:19
የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፤ በኮቪድ -19 እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ከሐምሌ 20 እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም ምዝገባ በማከናወን፥ ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም መጀመር እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለተማሪዎቻቸው አስቀድመው ጥሪ ያደረጉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል::

@Addismerja
@Addismerja
3.1K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:57:17
የቀድሞ የጋምቢያ የስለላ ተቋም ኃላፊ የሞት ፍርድ ተበየነባቸዉ

የጋምቢያ ፍርድ ቤት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ የጭካኔ አገዛዝ የመጨረሻ ቀናት በ2016 በአንድ የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ላይ ግድያ የፈጸሙ የሀገሪቱን የቀድሞ የስለላ ሀላፊ ያንኩባ ባድጂ እና ሌሎች አራት የደህንነት አባላት ላይ የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል፡፡

የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ኤብሪማ ሶሎ ሳንዴንግ የተቃዋሚው የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ግንባር ከፍተኛ አመራር የነበረ ሲሆን በጸረ መንግስት ተቃውሞ በያህያ ጃሜህ አገዛዝ ዘመን ታስሯል።ከሁለት ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኃላ በድብደባ ህይወቱ አልፏል።

የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ኤብሪማ ሶሎ ሳንዴንግ ግድያ ህዝባዊ ቁጣዉን በማባባስ ለ22 አመታት ስልጣን የጨበጡት ፕሬዝዳንት ጃሜህ ከስልጣን እንዲወገዱ ምክንያት ሆኗል።ጃሜህ እ.ኤ.አ በ2017 ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሸሽተው በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡

@Addismerja
@Addismerja
3.4K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:20:23 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ሕንፃዎችን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች አስተላለፉ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የተገነባውን “80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት” ለአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች በዕጣ አስተላልፈዋል፡፡
ሕንፃዎቹ ለነዋሪዎቹ የተላለፉት ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል እንደ ነበራቸው የመኖሪያ ቤት ሥፋትና መጠን መሠረት ነውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባዋ በልቤ ፋና ትምህርት ቤት በመገኘት ያስገነቧቸውን ሁለት ተጨማሪ ሕንጻዎች ማስረከባቸውን ከከንቲባ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡

@Addismerja
@Addismerja
3.6K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:23:58
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@Addismerja
@Addismerja
4.3K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:52:25
12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በዛሬው እለት ተጀመረ

መንግስት ለዜጎች ትኩረት በሰጠበት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እስካሁን በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቄ አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከሳውዲ አረቢያ ውጭ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሳራቅ ሀጋራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲንቀሳቅስ መቆየቱን ገልፀዋል።

በዚህም በዛሬው እለት 12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

ከታንዛኒያ፣ከማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ ፣ ጁቡቲ ሱዳን፣ የመን እና ኦማን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚመለሱት ከአለም የፍልሰት ድርጅት አይ ኦ ኤም  ጋር በተደርገ የጋራ ስራ እንደሆነም አምባሳደር መለሰ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

መንግስት ከሳውዲ አረቢያ ከመጋቢት 21 ጀምሮ በተደረጉ 126 በረራዎች 102 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችንም መመለሱንም አንስተዋል ። እነዚህ ዜጎች በሶስት ወራት ውስጥ ከሪያድ እና ከጅዳ የተመለሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@Addismerja
@Addismerja
4.0K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:05:15
በቴዲ አፍሮ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን አዲስ መጽሐፍ ለገበያ ሊበቃ ነው

በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

መጽሐፉ በዘላለም ሙሉ የተፃፈ ሲሆን የፊታችን ረቡዕ ለገበያ እንደሚቀርብ ነው የተነገረው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ #ልክ_በዛሬዋ_እለት ዝግጅታችን የብላቴናው ልደት ዛሬ መሆኑን እናንሳ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ልክ በዛሬዋ እለት ሐምሌ 7 1968 አ.ም ነበር በአዲስ አበባ የተወለደው።

ዛሬ 46ተኛ የልደት በአሉን እያከበረ ሲሆን አድናቂዎቹም በያመቱ ለሱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ ቀኑን ደም በመለገስና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ያከብሩታል።

@Addismerja
@Addismerja
4.2K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:02:48 የሳሙና አምራች ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃ እጥረትና እስከ 480 በመቶ በደረሰ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት በቂ ምርት እያመረቱ አለመሆናቸው ተገለጸ።

ለሳሙና ምርት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እያሳዩ መሆናቸውንና በቂ አቅርቦትም አለመኖሩን፣ የቲቲኬ ኢንዱስትሪስ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛው መጨጊያው ገልጸዋል።

ለሳሙና ምርት የሚውሉ በርካታ ግብዓቶች በአብዛኛው ከውጭ የሚመጡ ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችም አሉ። በተለይ ‹‹ኑዱልስ›› የተባለው ጥሬ ዕቃ በአንድ ዓመት ውስጥ 480 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የታየበት መሆኑን የገለጹት አቶ ግዛው፣ ይህም በኪሎ ግራም 50 ብር ከነበረበት ወደ 240 ብር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡ በየቀኑ ጭማሪ እያሳየ ይገኛልም ብለዋል።

በአገር ውስጥ ከሚገኙት ግብዓቶች ውስጥ ‹‹ዶኖማይት›› የተባለው ጥሬ ዕቃ አሶሳ አካባቢ እንደሚገኝ፣ በተለይም በፀጥታ ችግር ምክንያት በበቂ መጠን ማግኘት አለመቻሉን ገልጸው፣ በዋጋውም ላይ ከነበረበት በኪሎ ግራም ከሦስት ብር ወደ አሥር ብር ከፍ ማለቱን አክለዋል።

በጥሬ ዕቃ እጥረት ምክንያት በአምራቾች ላይ የሚደርሰው ጫና በተጠቃሚዎች ላይም የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በአንድ የሳሙና ምርት ላይም እስከ 70 በመቶ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስረድተዋል፡፡

@Addismerja
@Addismerja
4.5K views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ