Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት አላችሁ ዛሬ አንድ ስሰማው በጣም ያስደነቀኝን እና ያስገረመኝን ታሪክ ልንገራችሁ በአን | addicted to holy spirit

እንዴት አላችሁ
ዛሬ አንድ ስሰማው በጣም ያስደነቀኝን እና ያስገረመኝን ታሪክ ልንገራችሁ

በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ አንድ የተለመደ ስርዓት ያላቸው ህዝቦች ይኖሩ ነበር። በዚህ ስርዓት መሰረት አንድ ልጅ ወይም ወጣት ለአቅመ አዳም መድረሱን ለማረጋገጥ እና ከዚያም እንደ አዋቂ እንዲታይ አንድ ለሊት ብቻውን ጫካ ውስጥ እንዲያድር ይደረግ ነበር። ያቺን ለሊት ተቋቁሞ ማለፍ ከቻለ የትልቅነት ማዕረግን ይገኛል። እናም በዚህ ስርዓት ውስጥ ማለፍ የነበረበት አንድ ወጣት ተራው ይደርሳል ። እንደተለመዱው ዐይኑን ታስሮ በዚያ ጨለማ ወደ ጫካ አባቱ ይዞት ይሄዳል። እናም በአንድ ዛፍ ግንድ ስር እጁን እና እግሩን በገመድ ያስረው ጀመር። ገና ታስሮ ሳይጨርስ እንኳን የተለያየ የአውሬ ድምፅ ይሰማው ነበር። በጣም ፈራ ይንቀጠቀጥ ጀመር ከፍርሀቱ የተነሳ ሰውነቱ በላብ ተጠመቀ ነገር ግን ላሰበው ክብር ለመብቃት የግድ ያ ለሊት ሲነጋ ነው የታሰረው ዐይኑን እና እጁን መፍታት የሚችለው ። አንበሳ ሲያገሳ፣ ጅብ ሲጮህ እና እባብ በአጠገቡ እየተሳበ ሲያልፍ እየሰማ እንዲው እንደተሳቀቀ እያለቀሰ...... እይነጋ የለምና ነጋ።
የፀሀይዋ ብርሃን በታሰረው ዐይኑ ላይ ሲያርፍ ትልቅ ደስታ እና ኩራት ተሰማው ወዲያውም እጁን ቀጥሎም ዐይኑ ላይ ያለውን ጨርቅ መፍታተ ጀመረ ። ዐይኑን ሲገልጥ ግን ያልጠበቀውን ነገር ነበር የተመለከቱው የሆነ ሰው ጦር ይዞ አጠገቡ ቆሞ ነበር.... ይህም ሰው አባቱ ነበር ።ለካ በራሱ አልነበረም የተረፈው፣ ለካ ሊበሉት የነበሩትን አውሬዎች አባቱ ነበር የከለከለለት፣ ለካ አባቱ ጥሎት አልሄደም ነበር፣ ለካ እርሱ ማየት ተስኖት እንጂ አባቱ አጠገቡ ነበር ። አባቱም እነሆ ልጄ አለሁልህ ብሎ አቀፈው ።
እህት ወንድሞቼ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳላችሁ አላውቅም ግን አንድ ነገር ልበላችሁ ዛሬን ማየት የቻልነው እግዚአብሔር ስለጠበቀን ነው እንጂ በራሳችን አይደለም እናም አሁንም በጭንቅ ብቻዬን ነኝ ላላችሁ እርሱ የናንተን ጥንካሬ እንጂ ክፉ አይሻምና አሁንም አጠገባችሁ ነው። ስለ መልካም አባትነቱ እግዚአብሔር ይመስገን ።
እዚህ ላይ አበቃሁ ተባረኩልኝ
@ addictedtoholyspirit