Get Mystery Box with random crypto!

ሚስ አዳብና * ማህበራችን የአዳብና በክስታኔ አዳብናንና የማህበረሰባችን ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ | አዳብና መልቲ ሚዲያ

ሚስ አዳብና
*
ማህበራችን የአዳብና በክስታኔ አዳብናንና የማህበረሰባችን ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ የሚስ አዳብናን ሀሳብ በማመንጨትና ሙሉ ወጪው በመሸፈን እንዲሁም በማስተባበር ከእኛ ጋር መስራት ሌሎች አካላቶችንም በማካተት ለመጀመሪያ ጊዜ ሚስ አዳብና/የአዳብኒ መልካማ ከአዳብና ፌስቲቫል ጋር በማያያዝ እንዲካሄድ አድርጓል።

ማህበራችን ይሄንን የሚስ አዳብና ሀሳብ ሲያመነጭና በተግባር ላይ ሲያውለው ዋና ዓላማው አዳብናንና የማህበረሰባችንን ባህልና እሴት ማስዋወቅ ነው።

ማህበራችን የሚስ አዳብና ውድድር አጋዥ አካላቶችን በመጨመር በሰፊውና በልዩ ሁኔታ የሚሰራበትና ባህላችን ማስተዋወቁ የሚቀጥል ይሆናል።

በቅርቡም የ2016ዓ.ም የሚስ አዳብና ውድድር አካሄድና መስፈርቶች እንዲሁም እቅዶችን ኢፋ የምናደርግ ይሆናል።