Get Mystery Box with random crypto!

ሚስ አዳብና ያዳብኒ መልካማ : ባህልን ጠባቂ፣ ታሪክን ጠያቂ፣ ጠይቆም ሚረዳ፣ ለቀጣይ ትውልድ የበ | አዳብና መልቲ ሚዲያ

ሚስ አዳብና ያዳብኒ መልካማ : ባህልን ጠባቂ፣ ታሪክን ጠያቂ፣ ጠይቆም ሚረዳ፣ ለቀጣይ ትውልድ የበኩሉን አላፊነት ሚወጣ ጠያቂ እና  ባህሉን ሳይለቅ የዘመነ ትውልድን የመፍጠር አላማን አንግቦ የተነሳ ትልቅና የሁሉም የኔነት ስሜት ሚፈልግ ሀሳብ ነዉ።

           ሚስ አዳብና ሌላው አላማው ከቤት የጀረውን ወደ አካባቢው ቀጥሎም ለሀገር እያለ ለአለም ይዞት ሚወጣው: ውብ ባህልን ፣ መገልገያ ቁሶችን፣ አልባሳትን፣ መዋቢያ ጌጣጌጦችን፣ ባጠቃላይ የአኑዋኑዋር ዘያችንን እና ግብረ ገብነትን ጨምሮ ያልጠቀስኳቸው ቱባ ባህል እና ታሪክን በአለም መድረክ ከፍ አድርገጎ ማሳየት ነው ።

      ብዙ ከራሳችን አልፈው አለምን እጁዋን በአፋዋ ሊያስጭን የሚችል ድንቅ እና በታሪክ ቀደምት የሆነ ብዙ ትውፊት አለን። ለዚህም ነው ባህላችንና ታሪካችን ለትውልድ ሳይደበዝዝ እንዲተላለፍ እንዲሁም ለአለም ተደራሽ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣ እያልኩ መልክቴን አስተላልፋለሁ።


ከሞዴል መነን ዳንኤል

ባህላችን ለዓለም እናሰተዋውቅ!
ቅርሶቻችን በአንድነት እንጠብቅ!

አዳብና  መልቲ ሚዲያ Telegram ሊንኩን በመንካት ይቀላቀሉ። https://t.me/Adabnamidea

አዳብና You tube like share subscribers
በማድረግ ባህላችንን  ቅርሶቻችንን እናሳድግ ።

አዳብና ሚዲያ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCbihhwTdI6hy-e7Kj6T_J8g