Get Mystery Box with random crypto!

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhyder — የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhyder — የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
የሰርጥ አድራሻ: @abuhyder
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.56K
የሰርጥ መግለጫ

ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-09 21:03:02 እንኳን ለተወደደውና ለተከበረው ለ1,443ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢዱል-አድሓ በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል
ዒዱኩም ሙባረክ
3.3K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 23:16:23 8/ የዒዱል አድሓን እርድ ለመፈጸም የነየተ የአላህ ባሪያ (ወንድም ሆነ ሴት) ወሩ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ፡- የሰውነት ጸጉሩን መላጨትም ሆነ መቀነስ፣ የእጁንም ሆነ የእግሩን ጥፍር ማስተካከል፣ ከገላው ላይ የተወሰነ ቆዳንም ቢሆን ቆርጦ ማንሳት አይፈቀድለትም፡፡ ይህ ብይን የሚመለከተው የዒዱን እርድ በራሱ ወጪ ለማረድ የነየተውን ግለሰብ ብቻ ነው፡፡ ቤተሰቦቹን ብይኑ አይመለከታቸውም፡፡

ሰውየው በቀጥታ እራሱም አራጅ ሆነ፡ ወይም በወኪል ቢያሳርድ ኃላፊው እሱ እስከሆነ ድረስ ብይኑ ይመለከተዋል፡፡ ወኪል ሆኖ የሚያርደውን ሰው ግን ብይኑ አይመለከተውም፡፡

ኡሙ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዙል-ሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና አንዳችሁም ኡድሑያን (እርድን) ከነየተ፡ ጸጉሩንና ጥፍሩን (ከመቀነስ) ይቆጠብ" (ሙስሊም 1977)፡፡

በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ ‹‹ከጸጉሩና ከሰውነቱ (ቆዳው) ይቆጠብ›› ይላል፡፡
ስለዚህ ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ የዚል-ቂዕዳህ 29ኛው ቀን ስለሆነ፡ ወሩ በዚያው ሊጠናቀቅም ስለሚችል፡ የመግሪብ አዛን ከተሰማ በኋላ ያለው ምሽት የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ሆኖ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ወሩ ሠላሳ ከሞላ ደግሞ፡ ከእሁድ መግሪብ በኋላ ወሩ የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናም ለዒዱ እርድን የነየታችሁ ወንድምና እህቶች ሆይ! ከዛሬ መግሪብ አዛን በፊት (የጸጉር፣ የጥፍርና የቆዳ) ጣጣችሁን ጨርሱ፡፡

ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር፡ እርዱን የነየተ ሰው፡ በዙል-ሒጃህ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ጸጉሩን ወይም ጥፍሩን ቢቀንስ፡ ከፋራው ‹ካሳው› ተውበትና ኢስቲግፋር ብቻ ነው በማለት ዑለሞች ፈትዋ ሰጥተዋል (ኢብኑ ቁዳማህ፡ አል-ሙግኒይ 9/346)፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።

Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://t.me/abuhyder
7.5K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 23:16:23 ዙል–ሒጃና አሥርቱ ቀናቶቹ!!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
እንግዲሕ በአላህ ፈቃድ ካላንደር እንደሚያሳየው ነገ የፊታችን ጁምዓ የዙል-ሒጃ ወር ይጀምራል፡፡ ዛሬ ዙል–ቂዕዳህ 29 ነው። ዙል-ሒጃ በእስልምና ወር አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው (የመጨረሻው) ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ካሉት 29/30 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ቀናቶች ናቸው፡፡ መከበራቸውን ከሚያመላክቱት ውስጥ:–

ሀ. አላህ የማለባቸው መሆኑ:–

" በጎህ እምላለሁ።በዐሥር ሌሊቶችም።" (ሱረቱል ፈጅር 1-2)።
ታላቅ የሆነው ጌታችን አላህ የሚምለውም ታላቅ በሆነ ነገር ስለሆነ የቀኑን ክብደት ይገልጽልናል፡፡ እነዚህ አሥር ሌሊቶች የተባሉት የዙል-ሒጃ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት እንደሆኑ አብዝሓኞቹ የቅዱስ ቁርኣን ተንታኞች ይገልጻሉ፡፡

ለ. እኔን አስታውሱባቸው ማለቱ:–

" ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።" (ሱረቱል-ሐጅ 28)።

" የታወቁ ቀኖች " የተባሉት እነዚሁ አሥርቱ ቀናት እንደሆኑ ሙፈሲሮች ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ አላህን በማንኛውም ጊዜ ማውሳትና ማወደስ ከመቻሉ ጋር በነዚህ ቀኖች አወድሱት ብሎ ቀኖቹን ለይቶ መጥቀሱ የተለየ ደረጃና ክብር እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡

ሐ. ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ መሆናቸው:–

ከጃቢር ኢብኒ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈው ሐዲሥ ረሱላችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-" ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጩ (የዙል-ሒጃ) አሥሩ ቀናት ናቸው " (ሶሒሕ አል-ጃሚዑ ሰጊር 1133)፡፡
በዚህ መሰረት እነዚህ አስርት ቀናቶች ልዩ ክብር የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

ምን እንስራባቸው?

ዐብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ሥራ ከዙል-ሒጃ አሥርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" ሶሓባዎችም፡- በአላህ መንገድ ጂሐድ ማድረግም (ጠላትን መታገልም) ቢሆን? ሲሉ፡ እሳቸውም፡- አዎ ጂሐድም ቢሆን! ሰውየው ከነፍሱና ከንብረቱ ጋር በዛው ሳይመለስ የቀረ ካልሆነ በስተቀር አይበልጥም " (ቡኻሪይ)።

ታዲያ ያለምንም የመግቢያ ክፍያ እንዲህ ዐይነት ታላቅ ኤግዚቢሽን ከተዘጋጀልን እኛስ ለመሳተፍ ምን ያህል ወስነናል?፡፡ ጠላታችን ሸይጣን እንዳንጠቀምበት ደፋ ቀና ማለቱ አይቀርምና እኛም አላህን ይዘን እሱን ድል በመምታት ቀኑን እንጠቀምበት፡፡ ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ውስጥ፡-

1. ሐጅና ዑምራህ:–

" ዑምራህ ቀጣዩ አመት ዑምራ እስኪመጣ ድረስ (በመሃል ለተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአት) ማስተሰረያ ነው፣ ትክክለኛ ሐጅ ደግሞ ከጀነት ውጪ ክፍያ የለውም" (ቡኻሪና ሙስሊም)።

2. ጾም:–

የፈለገ ሙሉውን ዘጠኝ ቀን: ካልሆነም የቻለውን ያክል መጾም ይችላል፡፡ዐብደላ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ስራ ከዙል-ሒጃ አስርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" በዚህ ሐዲሥ መሠረት ጾም "መልካም ሥራ" የተባለው ሐዲሥ ውስጥ ስለሚካተት በጾሙ የቻለውን ያክል መበርታት ይችላል፡፡

3. አላህን ማውሳት:–

" ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።" (ሱረቱል-ሐጅ 28)።

ይህ ቅዱስ አንቀጽ አላህን በነዚህ ቀናት ማውሳት: መዘከር እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ነቢዩ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "በነዚህ ቀናት ውስጥ ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢልለሏህ)፤ተክቢር (አላሁ አክበር)፤ተሕሚድ (አል-ሐምዱ ሊላህ) ማለትን አብዙ" (አህመድ 7/224)

ዐብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ወደ ገበያ በመውጣት በተክቢራ ሲያሞቁት ሰዎቹም እነሱን ተከትለው ተክቢራ ይሉ ነበር (ኢርዋዑል-ገሊል: አልባኒይ 651)።

4. ተውበት ማብዛት:–

"…ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።" (ሱረቱል አሕዛብ 31)።

5. መልካም ሥራዎችን ማብዛት:–

በኢስላም የመልካም ሥራ በሮች ብዙ ናቸው፡፡ ተቆጥረው አይዘለቁም፡፡ ከኛ የሚጠበቀው ስራው ላይ ተሳታፊ መሆን ነው፡፡ ከቤተሰብ ጀምረን እሰከ ሩቅ ሰው ድረስ አቅማችን የቻለውን ያህል በመርዳት ወደ አላህ እንቃረብ፡፡

6. በዒባዳህ መጠናከር:–

ከፈርድ ሶላት ቀጥሎ ያሉትን ሱንና ሶላቶችን ማብዛት፤ቁርኣንን ማንበብና ማዳመጥ፡፡

7. ከሐራም መቆጠብ:–

ከላይ የተጠቀሱት መልካም ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የአላህን ተውፊቅ ያላገኘ ሰው ቢያንስ ከሱ እጅና ምላስ ሌሎች ሰላም እንዲሆኑ እራሱን ማቀብ፡፡እሱም ትልቅ ተውፊቅ ነውና፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያርገን

#የኡድሑይያህ እርድ

1/ ኡድሑይያህ ማለት:– በዙል ሒጃህ ወር ከአሥረኛው ቀን አንስቶ እስከ አያመ–ተሽሪቅ (አስራ ሶስተኛው ቀን ድረስ) ወደ አላህ ለመቃረብ ሲባል ከቤት እንሰሳት (ግመል፣ ከብት፣ ፍየል/በግ) አንዳቸውን በመምረጥ የማረድ ስርአት ማለት ነው።

2/ የኡድሑይያህ ስርአት በጣም ጠንካራ ሱንና ከሆኑ የአምልኮ ዘርፎች ይመደባል። የአላህ ቃልም:– "ለጌታህም ስገድ፣ በስሙም እረድ" (አል–ከውሠር 3)። ባለው መሠረት በአላህ ሥም ይታረዳል።

3/ የኡድሑይያህ የእርድ ስርአት ሱንና ነው። ዋጂብ አይደለም። የተወው ሰው በኃጢአት አይከሰስም። ሲታረድም ለአላህ ተብሎና በአላህ ሥም ነው የሚታረደው።

4/ የኡድሑይያህ የእርድ ቀናት ከዒዱ ቀን ሶላት መጠናቀቅ ጀምሮ (የውሙ–ነሕር 10ኛው ቀን ማለት ነው) እስከ አያሙ–ተሽሪቅ የመጨረሻው ቀን (11፣ 12 እና 13ኛው ቀን ፀሀይ መግባት ድረስ) የሚቆይ ይሆናል። በጥቅሉ አራት ቀናት ይኾናል ማለት ነው። 10ኛው ሶላቱል ዒድ የሚሰገድበት ቀን (የውሙ–ነሕር)፣ 11ኛው ቀን፣ 12ኛው ቀን፣ 13ኛው ቀን።

5/ በዋጋ ጠንከር ያለ፣ ስጋው በዛና ሞላ ያለ፣ ከነውር የፀዳ፣ የእርድ አይነት መግዛቱ በላጭ ይኾናል። ኡድሑይያህ የነየተውም አካል: ከእርዱ ላይ እራሱም ሊበላ፣ ቤተሰቡንም ሊያበላ፣ ዘመድና ወዳጆቹንም ሊጋብዝ፣ ለምስኪኖችም ሊያከፋፍል ይወደድለታል።

6/ የሚታረደው የእርድ አይነት ግመል ከሆነ አምስት አመት የሞላው፣ ከብት (በሬ/ላም) ከሆነ ሁለት አመት የሞላው፣ ፍየል ከሆነ አመት የሞላው፣ በግ ከኾነ ስድስት ወር ያለፈው ከኾነ ለእርድ የበቃ ይኾናል።

7/ የእርዱ አይነት እውር ወይም አንካሳ ወይም በሽተኛ ከሆነ አይበቃም። ጆሮው ወይም ጭራው የተቆረጠ፣ ጥርሶቹ በመላ የረገፉ ከኾነ ደግሞ እሱን ለእርድ ማቅረብ የተጠላ ይኾናል።
7.0K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:02:39

15.8K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 09:51:09 https://t.me/mahircomp123 ወደዚህ ግረፕ ግቡና በኢስላም ላይ የሚነሱ የጠላት ክሶችንና ምላሾቹን በማንበብ: እራሶትን በዕውቀት ያንጹ።
13.7K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 14:32:25 #የሸዋል ፆም ፍች (ትንሹ ዒድ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡
በተወሰኑ (ሁለት ወይም ሶስት) ብሔሮች ዘንድ ከረመዷን ዒድ (ዒዱል-ፊጥር) ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን እንደ ዒድ ያከብሩታል፡፡ ምክንያቱን ጠይቄ ለማወቅ እንደሞከርኩት ይህን ይመስላል፡-
የዒዱል-ፊጥር ቀን ደብዘዝ ብሎ በደንብ ሳይሞቅ የምናሳልፈው ቀኑ አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ሁለቱንም (ረመዷንንም ሸዋልንም) እንጨርስና ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡
ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር ለመዘያየር የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሸዋል ዒድ አለ ብለን አይደለም የሚል ነው፡፡
ማስተካከያ፡-
1ኛ/ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፡ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቢድዐ ይባላል፡፡ የሸዋል ወር 8ኛው ቀን የሸዋል ፆም መፍቻ ዒድ ቢሆን ኖሮ፡ በዒድ ቀን መፆም ሐራም ነውና በዚህ ቀን አትፁሙ የሚል ትእዛዝ በሐዲሥ በሰፈረ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
2ኛ/ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው መብላትና ማብላት፣ መዘየርና መደሰት የሚቻለው ያለው ማነው? የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም? ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከላይ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም፡፡
3ኛ/ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡ እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡
4ኛ/ ከዒዱል-ፊጥር ማግስት ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስድስት ቀናት የጾመ ቤተሰብ በቀጣዩ ቀን በመብላትና ቀኑን እንደ ዒድ ቆጥሮ ሲያሳልፈው፡ ከመሐከላቸው አንድ ሰው ጾሙን ባለመጨረሱ (ቀዷእ ቢኖርበት ወይም ዘግይቶ ቢጀምር) እነሱ የሚበሉበትን ቀን ቢጾመው የቤተሰቡ አካላት ይቃወሙታልን? በዒድ ቀን እንዴት ትበላለህ ይሉታልን? አዎ! ከሆነ ምላሹ፡ ሰዎቹ ቀኑን ዒድ አድርገው ይዘውታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዲነል-ኢስላም ላይ የተጨመረ ፈጠራ ‹‹ቢድዓህ›› ይባላል፡፡ አላህና መልክተኛው ከዒዱል-ፊጥር እና ከዒዱል አድሓ ውጪ የበዓል ቀን አልደነገጉልንም፡፡ የሸዋል ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ቢድዓ መሆኑን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡
4. ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፡- ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን ስድስት ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡ የዒዱል-ፊጥር ቀንንም በአግባቡ ሊያከብረው ይገባል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
15.9K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 23:13:35

13.8K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:42:22 ሸዋልን አደራ!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡

የሸዋል ወር በእስልምናው አቆጣጠር ከረመዷን ቀጥሎ የሚመጣ 10ኛ ወር ነው፡፡ ሸዋል የወሩ ስም እንጂ በወሩ ውስጥ የሚፆመውን 6ቀናት የሚመለከት ስም አይደለም፡፡ ይህ ወር እንደተቀሩት 11 ወራቶች እሱም 29/30 ቀናት አሉት፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ደግሞ 6ቀናትን በማከታተልም ይሁን በማፈራረቅ መፆም እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡ ዋጋውም (አጅሩም) በአሥር በመባዛት የስልሳ ቀን (ሁለት ወር) ፆምን አጅር ያስገኛል፡፡ ከረመዷን አንድ ወር ፆም (አሥር ወር አጅር) ጋርም በመደመር የአንድ ሙሉ ዓመት ፆም ምንዳ(ክፍያ) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ አላህ ይቀበለን፡፡ ይህንን በተመለከተም አሽረፈል ኸልቅ (የፍጥረቱ ሁሉ የበላይ) የሆኑት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት አስተምረዋል፡፡ ኡመታቸውንም አነሳስተዋል፡-
"የረመዷንን ወር ጹሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው" (ሙስሊም 1164)፡፡

ስለዚህም የሸዋል ወር ፆም ረመዷንን የፆመ ሙስሊምን ሁሉ ይመለከታል ማለት ነው፡፡ የአዋቂዎችና የአባቶች ፆም ነው በማለት ሌላው አካል መዘናጋት የለበትም፡፡ ወይንም፡- ባልፆመው የማስጠይቀኝ፡ ግዴታ ያልሆነ ተግባር ነው ብለን አንሳነፍ፡፡ በመፆማችን ደግሞ የምናገኘውን አጅር እናስላ፡፡ አንድ ወር ሙሉ በተከታታይ በአላህ ተውፊቅና እገዛ መፆም ከቻልን ስድስት ቀናትን መፆም ደግሞ እንደምን ይጠናብናል?
አንዳንዱ ደግሞ ፆሙ ይከብዳል እንደ ረመዷን አይቀልም ይላል፡፡ እውነት ነው የሸዋል ወር ፆም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም፡- አንድ፡ በረመዷን የታሰረው ቀንደኛው ጠላታችን ሸይጧን ከዒድ ሶላት መጠናቀቅ በኋላ ተፈትቷልና ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ ደግሞም ይህንን የሸዋልን ፆም ልክ እንደ ረመዷኑ ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የመስጂድ ጀመዓዎች ሁሉም ስለማይፆሙት በሚፆሙት ላይ (አላህ ያገራለት ሲቀር) ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም አላህ ዘንድ የሚገኘውን ሽልማት ያሰበና ያመነ ባሪያ ሊከብደው አይገባም፡፡

እንዴት እንጹመው?

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሸዋል ሙሉ ወር በመሆኑ 29/30 ቀናት አሉት፡፡ የመጀመሪያው ቀን የዒዱ ቀን ነበር፡፡ ከዛ በኋላ የሚቀረው 28 ቀናት ይሆናል ማለት ነው (ወሩ 30 ለመሙላቱ እርግጠኛ መሆን ስለማንችል)፡፡ በነዚህ 28 ቀናት ውስጥ የሸዋልን ስድስት ቀናት በተከታታይ በማከታተልም ይሁን ቀናቱን ለያይቶ በማፈራረቅ መፆም ይቻላል፡፡ ከፈለገ ሰኞና ሀሙስ እደረገ፡ በአንድ ኒያ የሰኞና የሀሙስን እንዲሁም የሸዋልን ፆም በመነየት ሁለት አጅር መሰብሰብ ይቻላል፡፡

ቀዷ ያለበትስ?

የረመዷን ቀዷ (በህመም፣ በሐይድ እና በመሳሰሉት) ያለበት ሰው፡ ቀዷው እያለበት የሸዋልን ፆም በመፆም ከዛ ቀዷውን ወዲያው ወይም በሌላ ጊዜ ማስከተል ይችላል ወይስ ቅድሚያ ቀዷውን ከዛም የሸዋልን ፆም? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ እነሱም፡-
1. ከሑክም አንጻር
2. ከሚገኘው አጅር አንጻር

1ኛ. ከሑክም (ከሸሪዓዊ ፍርድ) አንጻር፡ ጉዳዩ በዑለማዎች (የኢስላም ሊቃውንት) መሐል ኺላፍ ቢኖርበትም፡ በላጩ ሐሳብ፡- ማንም ሙስሊም የረመዷን ቀዷ ቢኖርበት፡ ያንን ቀዷ ከመክፈሉ በፊት ሌሎች የሱንና ፆሞችን መጾም አይችልም የሚል መረጃ የለም የሚለው ነው፡፡ ይልቁኑ ቅዱስ ቁርኣን በግልጽ የሚናገረው፡ በበሽታም ይሁን በሙሳፊርነት እንዲሁም በሌላ ምክንያት የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው ‹በሌሎች ቀናት ቀዷውን ያውጣ› በማለት ተናገረው እንጂ፡ በሸዋል ወር ውስጥ ቀዷውን ይክፈል የሚል አይደለም፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"...فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ... " سورة البقرة 184-185
"…ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት…" (ሱረቱል በቀራህ 184-185)፡፡
ስለዚህም የረመዷንን ቀዷ የመክፈያ ጊዜው እስኪመጣ በዚያ መሐል የሸዋልን 6ቀናት፣ ሰኞና ሀሙስ፣ የዙል-ሒጅጃህ ቀናት (በተለይ የዐረፋ ቀን) እና መሰል ፆሞችን መጾም አይቻልም አይባልም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

2ኛ. ከሚገኘው ምንዳ አንጻር፡- ዋናው ቁልፉ ያለው እዚህ ጋር ነው፡፡ ሙሉ አመቱን እንደፆመ እንዲቆጠርለትና አጅሩም ተቀማጭ እንዲሆንለት የፈለገ ሰው ግን ግዴታ ቀዷውን ቀድሞ ማጠናቀቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ከላይ በሐዲሡ ላይ እንደተገለጸው የሸዋልን ወር ፆም ያስከተለ የተባለው ‹ረመዷንን ለፆመ› ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ረመዷንን ጹሟል የሚባለው ሙሉውን ሲያጠናቅቅ ነው፡፡ የተወሰነ ቀሪ ዕዳ ካለበት፡ ረመዷንን የፆመ የሚለው ሐዲሥ ውስጥ አይካተትም፡፡ ስለዚህም የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ቅድሚያ ቀዷችንን በማጠናቀቅ ከዚያም ወደ ሸዋሉ ፆም መግባት ይቻላል፡፡ ደግሞም ቅድሚያ ዕዳን ከፍሎ ማጠናቀቁ ተገቢ ተግባር ነውና፡፡ የተሟላውን የአመት አጅር ለማግኘት ከሸዋል ወር ስድስት ቀን ጾም በፊት ቅድሚያ የረመዷን ቀዷ መከፈሉ ግድ መሆኑን ከሚገልጹ የዑለማዎች ፈትዋ መሐከል፡-

1. ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ 918
2. ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ አል-ሐረሙል መኪይ ካሴት ቁ 7

አቋራጭ መንገድ ካለ?

መቼም ይሄ (shortcut) አቋራጭ መንገድ የሚባለው ነገር ተላምዶናል፡፡ በሰላምታ ወቅት (as wr wb) በሰላዋት ጊዜ (s.a.w) በምስጋና ተግባር ላይ (jzk)… ታዲያ አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፡ የረመዷንን ቀዷና የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም በአንድ በመነየት አጣምሮ መፆም ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡
ይህን ጥያቄ ፈዲለቱ-ሸይኽ ሙሐመድ ቢን-ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን እንዲህ ይመልሱታል፡- ‹‹የረመዷን ቀዷ እያለበት የዐረፋን ቀን ወይም የዐሹራእን (የሙሐረምን 10ኛ ቀን) የፆመ ሰው ፆሙ ትክክል ነው፡፡ ደግሞም እነዚህን ቀናት የረመዷንን ቀዷእ በመክፈል ኒያ በአንድ ላይ ቢፆማቸው ሁለት አጅርን ያገኛል፡፡ የዐረፋ ቀን ፆምና የዐሹራእ ፆምን አጅር ከረመዷን ቀዷእ አጅር ጋር ማለት ነው፡፡ እሱም እነዚህ የሱና ፆሞች ቀጥታ ከረመዷን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው፡፡ የሸዋል ወር ስድስት ቀናት ፆም ግን ከረመዷኑ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ምክንያት በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆሙ አይሆንም፡፡ ቅድሚያ ቀዷውን ከፍሎ ከዛም የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከትል›› (ፈታዋ-ሲያም 438)፡፡
ወላሁ አዕለም

Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
17.2K views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 00:33:39 እንኳን ለተከበረው 1,443ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

አላህ ወሩን የዒባዳ፣ የድል፣ የአንድነት ያድርግልን
16.7K views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 18:08:44 አዲስ ተከታታይ ደርስ
ፃምን የሚያፈርሱ ነገራቶች
ክፍል 7

አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
18.5K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ