2022-07-07 20:43:51
የአረፋን ቀን መፆም ጥብቅ የሆነ ሱና /سنة مؤكدة/ነው ይህን ቀን ልንፆም ሰዎችም እንዲፆሙ ልናነሳሳ ይገባል
عن أبي قتادة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم سئل عن صوم يوم عرفة فقال : ( يكفر السنة الماضية والباقية )
"ያለፈዉን አምትና የተቀረዉንም ያሳብሳል "
رواه مسلم (1162)
وفي رواية له : ( أحتسب على الله أن يكفر السنة التي قبله والسنة التي بعده).
"ያለፈውን እና ከዚያ በኋላ ያለውን አመት ያስምራል ብዬ በአላህ ተስፋ አደርጋለሁ"
قال النووي رحمه الله في "المجموع" (6/428) ـ من كتب الشافعية ـ :
" أما حكم المسألة فقال الشافعي والأصحاب : يستحب صوم يوم عرفة لغير من هو بعرفة .
وأما الحاج الحاضر في عرفة فقال الشافعي في المختصر والأصحاب : يستحب له فطره لحديث أم الفضل . وقال جماعة من أصحابنا : يكره له صومه , وممن صرح بكراهته الدارمي والبندنيجي والمحاملي في المجموع والمصنف في التنبيه وآخرون " انتهى .
በጉዳዩ ላይ ያለውን ብይን በተመለከተ አል-ሻፊዒ እና ባልደረቦቻቸው እንዲህ ብለዋል፡- "በሃጅ ላይ ካሉት ሰዎች ውጭ የአረፋን ቀን መፆም ሙስተሐብ ነው።
በአረፋ ላይ የሚገኘውን ሀጃጅ በተመለከተ አል-ሻፊኢ በአል-ሙክታሳር እና በአል—አስሃብ ላይ እንዲህ በለዋል ፡- ማፈጠሩ ይወደድለታል ከኡሙ አልፈደል በተላለፈው ሀዲስ መሰረት ።
የሻፉኢያን መዘሀብ ከሚያረምዱት የተወሰኑት እንዲህ ብለዋል፡- ለሁጃጆች መፆም የተጠላ ነው፣ መፆሙን ውድቅ ካደረጉት መካከል አል-ደራሚ፣ አል-ባንዳኒጂ እና አል-መሃማሊ በአል-መጅሙዕ እና አል-ሙሰነፍ ተንቢህ ላይ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
وقال ابن قدامة رحمه الله في المغني (4/443) ـ من كتب الحنابلة ـ :
" وهو يوم شريف عظيم ، وعيد كريم ، وفضله كبير ، وقد صح عن النبي صلى الله عليه وسلم أن صيامه يكفر سنتين ." انتهى
"ይህ ታላቅ የተከበረ ቀን ነው፣ የተከበረ በዓል ነው፣ ምግባሩም ታላቅ ነው፣ ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሶሂህ በሆነ መልኩ የተዘገበው ይህን ቀን መፆም የሁለት ዓመታትን ወንጀል ያሰረዛል።"
.
وقال ابن مفلح رحمه الله في الفروع (3/108) ـ من كتب الحنابلة أيضا ـ :
" ويستحب صوم عشر ذي الحجة ، وآكده التاسع ، وهو يوم عرفة ، إجماعا . " انتهى .
"የዙልሂጃን አስር ቀናት መፆም ይወደዳል ከአስሩ ቀናትም ጥብቅ የሆነው ዘጠነኛው ቀን ነው ይህም ቀን የዐረፋ ቀን በመሆኑ ላይ ኢጅማዕ አለ ።"
ወንድሜ ነገ ዘጠነኛው (የአረፋ) ቀን ነው ስዘለዚሀ ይህን ቀን ልንፆም ይገባል ለሌሎችም እንዲፆሙ ልናስታውስ ይገባል
ይህን ቀን ፁመው በመልካም ከሚመነዱት ያድርገን
አሚን
ማሳሰቢያ: —
1:—ነገ ጁሙኣ ነው ስለዚህ የጁመኣን ቀንን መፆም አይፈቀድምና የአረፋ ቀን የጁሙኣ ቀን ጋር ቢግጥምብን ምን ማድረግ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ አካለቶች በትላልቅ መሻይኮች የተመለሰዉን ድመፅ ፋይል እናድምጥ እላለሁ
የሼክ ቢን ባዝ ድምፅ ፋይል
https://t.me/abutoiba/3082
የሼክ ሱለይማን አር—ሩሃይሊ ድምፅ ፋይል
https://t.me/abutoiba/3083
የሼክ ቢን ኡስይሚን ድምፅ ፋይል
https://t.me/abutoiba/3084
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
109 views17:43