Get Mystery Box with random crypto!

አርተፊሻል ቆንጆ በኩል አሳምራ ለስና ቅንድቧን ክሬም ተቀብታ ሁለት ጉንጮቿን በጋለ ካዊያ ተተ | قناة أَبي ماحي محمد اَلحبشي الْوَلّوي

አርተፊሻል ቆንጆ

በኩል አሳምራ ለስና ቅንድቧን
ክሬም ተቀብታ ሁለት ጉንጮቿን
በጋለ ካዊያ ተተኩሳ ፀጉሯን

አጭር ቀሚስ ለብሳ ገልጣ ሰውነቷን፣
ስትል ሰበር ሰካ አድርጋ ታኳዋን፣
በምድር ላይ ሳለች ከሷ ወዲያ ሴት
በዚህ አለም ቆንጆ የለለ መስላት፣

በጉራ ተገፍታ በትእቢት ተወጥራ፣
ልታይ ልታይ ብላ ስትል ኮራ ኮራ፣
ወዲያው ወረደና የዝናብ መአት፣
ለመሮጥ አትችል ልብሷ ሲወጥራት፣

ተበላሸ ተኩሱ ፀጉሯም በሰበሰ፣
የጉንጮቿ ክሬም በአይኗ ኩል ራሰ፣

ዝናብ አጠበና ሜካፑን ወሰደው፣
ፅጌሬዳ መስላ ከቤቷ ስትወጣ፣
ዝናቡ አስመሰላት ጭራሽ የሰው ጦጣ፣

ያ ያ ያ ሁሉ ቅባቅብ ሂጃቧን ያስጣላት፣
ለካስ አርተፊሻል ሰው ሰራሽ ቆንጆ ናት

https://t.me/EmuIkramAselefiya
https://t.me/EmuIkramAselefiya