Get Mystery Box with random crypto!

الســــلام عـــلــــيـــكـــم ورحــــمــــة الــــلــه وبـــــ | قناة أَبي ماحي محمد اَلحبشي الْوَلّوي

الســــلام عـــلــــيـــكـــم ورحــــمــــة الــــلــه وبـــــركـــــاتـــه
ወጣቶች ብቻ የሚሳተፉበት ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም/ድግስ
መስጂደ አስ  ሱና (በደሴ ከተማ)  ቁጥር ③

  የፊታችን እሁድ በቀን  (04/10/2015) ከጧቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ዙሁር ሶላት  የሚቆይ

በውቢቷ
ወሎ መናገሻ ደሴ ከተማ   ላይ  ታላቅ የዳዕዋ ፕሮጋራም ማዘጋጀታችንን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

ተጋባዥ ወንድሞች ፦

① ወንድም አብዱል መሊክ ያሲን {ኸሚሴ}
ርዕስ:— የሸሐደተይን  ትርጉም
② ወንድም  አቡ ሙስዓብ (ሳሊም)  {ሀርቡ}
ርዕስ:— የኢልም አሳሳቢነት
③ ወንድም አልይ (አቡ ሀሳን) {ዉጫሌ}
ርዕስ:—አንድነት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው
④ ወንድም አቡ ሂበቲላህ  {ደሴ}
ርዕስ:—ሱናን አጥብቆ መያዝ
⑤ ወንድም አቡ ሀፍሷ {ደሴ}
ርዕስ:— ወንድማማችነት
⑥ ወንድም አቡ አዒሻ {ገራዶ}
ርዕስ:— ሀሜትን ስለመጠንቀቅ
⑦ ወንድም ኑረዲን አል አረቢ {ከገጠር}
ርዕስ:— እውነተኝነት
⑧ ወንድም አልይ ሰዒድ  {ደሴ}
ርዕስ:—ለምን ቅድሚያ ለተውሂድ እንላለን 
⑨ ወንድም ኑር ሰላም {ደሴ }
ርዕስ:—በዲን ላይ መታገስ (ሶብር)
①∅ ወንድም አቡ ማሂ  ሙሀመድ {ኮቻ }
ርዕስ:— ምክር ለወጣቶች

ሌሎችም ብርቅየና በሳል የሆኑ የሱና ወንድሞቻችን ይጋበዛሉ ኢን ሻ አላህ

መጨረሻ ላይ አጠር ያለ ውይይትም ይኖረናል ኢን ሻ አለሏህ


በሱና ወንድሞቻችን የሚቀርቡ የግጥም ፕሮግራሞችም  ይኖራሉ
ኢን ሻ አላህ



ማሳሰቢያ :—በደሴና በዙሪያዋ ያላችሁ መሻይኾች፣ኡስታዞች፣ዳኢዎች የልፋታችሁን ውጤት እንዲታዩና ማስተካከያም ሲኖር እንዲታስተካክሉ ፕሮግራሙ ላይ እንዲትገኙልን  ስንል ጥሪችንን እናስተላልፋለን

ጥሪን ማክበር ደግሞ ግዴታ ነው
እንዴ ሰዓቱ ሁኔታ ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይኖራሉ

በደሴ እና በአከባቢዋ   ያላችሁ የሱና ወንድሞችም ሆነ እህቶች  እንድሁም መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ጥሪ ተደርጎላችሗል።
ፕሮግራሙ የሚጀመረው በአሏህ ፈቃድ ሻርፕ
2:30 ላይ ነው።
ለሴቶችም በቂ ቦታ አለን




ማርፈድ ያስቆጫል፤መቅረትማ  በፍፁም ሊታሰብ አይገባም
ቦታ:— መስጂዴ ሱና ፣ደሴ ከተማ ፣አውራ ጎዳና ከወንዝ ወዳ ማዶ ከሪል ስቴቱ ጎን ላይ

ቦታው ከጠፋባችሁና የበለጠ መረጃ ማገኘት  ከፈለጋችሁ

+2519 23751497  አልይ (አቡ ፋጢማ)
+251914516161 ኑር—ሰላም (አቡ ሉቅማን)
https://t.me/mesjidesunnahbedessie8800