Get Mystery Box with random crypto!

ማንበብ ባህል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐ | Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ማንበብ ባህል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው።

የንባብን ባህል ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው። በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ለ አንድ መቶ ቀናት ንባብን ሲያበረታታ ቆይቷል። ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

መጪው ክረምት ነው። ብዙ ወጣቶች ዕረፍት ላይ ይሆናሉ። ጊዜያቸውን በንባብና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያሳልፉ በብርቱ ልንሠራ ይገባል።