Get Mystery Box with random crypto!

ቅዲስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሆኗል ፈረሰኞቹ የ 2014 የውድድር ዓመት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ | Abisiniya Media

ቅዲስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሆኗል

ፈረሰኞቹ የ 2014 የውድድር ዓመት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት በጉጉት በተጠበቀው መርሐ ግብር አዲስ አበባ ከተማን በመርታት የሊጉን ዋንጫ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን አውጀዋል።

ፈረሰኞቹ ከ 2009 የውድድር ዓመት በኋላ ያጡትን የሊጉን ዋንጫ ዳግም ወደ ካዝናቸው ማስገባት ችለዋል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ፋሲል ከነማ በቀጣይ ዓመት ሀገራችን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ሽንፈት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ በሊጉ ወደታችው እርከን መውረዳቸውን ያረጋገጡ ሶስተኛው ክለብ ሆነዋል።

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

@abisiniyans