Get Mystery Box with random crypto!

★10 የዑስማንያ (የኦቶማን) ኸሊፋ የትዳር ህጎች: - 1. በራስ ፍቃድ ትዳር የመያዣ እድሜ ከ1 | Abdurahman Jeylan

★10 የዑስማንያ (የኦቶማን) ኸሊፋ የትዳር ህጎች: -

1. በራስ ፍቃድ ትዳር የመያዣ እድሜ ከ18-25 ነው። ከ25 እድሜ በላይ የሆነ ሰው ማግባት ግዴታው ሲሆን ኑሮው ዝቅተኛ ደረጃ ከሆነ "ከበይተል ማል" ገንዘብ ተመድቦለትና ስራ ተመቻችቶለት እንዲያገባ ይደረጋል።

2. እድሜው ከ25 በላይ ሆኖ በበሽታ ምክንያት ትዳር ያልያዘ ጎረምሳ ካለ ሙሉ የህክምና ምርመራ በመንግስት ወጪ ይደረግለታል። ከበሽታው የመዳን ተስፋ ካለው እስክድን እርዳታ እየተደረገለት ይታከማል። ካልዳነ የማግባት ግዴታው ይነሳለታል። ከዳነ ያገባል።

3. 25 እድሜ ሞልቶት ትዳር አልይዝም ቢል ከቀን ገቢው 1/4 እየተቆረጠ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል። ይህ ቅጣት ተሰብስበው ትዳር ፈልገው ብር ለሌላቸው ወጣቶች ይሰጣል፣ እነሱ ይዳሩበታል፣ ይቋቋሙበታል።

4. እድሜው 25 ሞልቶ ያላገባ ወጣት በፍፁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች አይቀጠርም። የሚሰራበት የመንግስት መስሪያ ቤት ካለም 25 ሞልቶት ካላገባ ይባረራል።

5. እድሜው 50 ሞልቶት ሁለት ሚስት የማግባት አቅምም አቋምም እያለው ሁለት ሚስት ያላገባ በእርዳታ ድርጅቶች ላይ እንድሳተፍ ይገደዳል። አልያም አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት የቲሞችን (ወላጅ አልባ) ህፃናትን እንዲንከባከብ ግዳጅ ይጣልበታል።

6. ከ8-25 ባለው እድሜ ክልል ውስጥ ሆኖ ምንም ሳይኖረው ለሚያገባ ማንኛውም ወጣት ከሀገሪቱ የመሬት ባንክ 900 ካሬ ይሰጠዋል። የንግድ ወይም የሙያ ልምድ ካለውም ሰርቶ እንድለወጥ የብድር አገልግሎት ይመቻችለታል።

7. ወጣቱ ወላጆቹን የሚኻድ ም ከሆነና የሚያግዘው ወንድም ወይም እህት በሌለበት ሁኔታ ትዳር ቢይዝ የግዳጅ ዘመቻ ድንጋጌው ይነሳለታል።

8. ጎረምሳው ከ18-25 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ 3 ልጆችን ቢወልድ እንደ ሽልማት ልጆቹ አዳሪ ትምህርት ቤት በነፃ እንድማሩ ይደረግለታል።

9. ተማሪው በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪ ትምህርቱን እየተከታተለ ከሆነ ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ ትዳር እንዲይዝ አይገደድም።

10. በስራ ጉዳይ ከሀገር ለተወሰኑ ዐመታት ሊወጣ ካሰበ ሚስቱን ይዞ እንዲሄድ ይገደዳል። አሳማኝ ምክንያት ካቀረበ ግዴታነቱ ይነሳለታል።

ቤተሰብ ይሁኑ →Abdurahman Jeylan Official https://www.facebook.com/profile.php?id=100082999208494