Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን በጀርመን እና ስኮትላንድ መካከል የተደረገውን የ17ኛው የአውሮፓ የእግር ኳስ ዋንጫ የመክ | Abay Bank

ባንካችን በጀርመን እና ስኮትላንድ መካከል የተደረገውን የ17ኛው የአውሮፓ የእግር ኳስ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ውጤት በ“ይገምቱ ይሸለሙ” መርሐግብሩ በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ ትክክለኛ ግምት የሰጡ አሸናፊዎችን ለመሸለም ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት ያሸነፉ ሶስት ተሳታፊዎችን የለየን ሲሆን አሸናፊዎቹ የተመረጡት፡-
• ትክክለኛ ግምት በመስጠታቸው፣
• ቀድመው በመመለሳቸው ፣
• ግምታቸውን በባንካችን የፌስቡክ ገጽ የውስጥ መልዕክት (Inbox) በመላካቸውእንዲሁም
• የፌስቡክ ገጻችንን ለሌሎች ሰዎች በማጋራታቸው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተመረጡ ጨዋታዎችን በ“ይገምቱ ይሸለሙ” መርሃ ግብራችን እንደምናቀርብ ለማስታወስ እንወዳለን!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!