Get Mystery Box with random crypto!

የሰዎች የመንቀሳቀስ መብት የተረሳበት ዝግጅቶች መበራከት አሁን አሁን በኢትዮጵያ የተለያዩ ዝግጅ | (ABC) Amhara Broadcasting Corporation

የሰዎች የመንቀሳቀስ መብት የተረሳበት ዝግጅቶች መበራከት

አሁን አሁን በኢትዮጵያ የተለያዩ ዝግጅቶች ለመዘጋጀት በማለት በርከት ህዝብ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀምባቸውን መንገዶች የለም ቅድመ ንግግር ውይም ለህዝብ ከሳምንት ወይም ከ3 ቀናት በፊት ሳያሳውቅ መንገዳችን መዝጋት ማለፍ ክልክል ነው ማለት እየተለመደ እና ህብረተሰብን ደግሞ ለማጉላላት እየዳረገ ይገኛል።

በተላይ መንግስት ወደ ስልጣን በመጣበት ወቅት ህብረተሰብ ላይ የምንዘነጋው መንገድ የለም ቢል ቅኑ እየሆነ ያለው ግን በተቃራኒ ሁኗል በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል በዓል መክበሪያ በሆነው መስቀል አደባባይ ያለ እረፍት የተለያዩ ዝግጅቶች መንግስት በማዘጋጀት የመዲናዋን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ችግር ውስጥ እያስገባ ይገኛል።

በተላይ በዚህ የመንገድ መስተጓጐል መክንያት የተቸገሩ ሰዎች የሚነሱት ሀሳቦች በሚዲያ አልተነገረም ለምን በእረፍት ቀን እሁድ አያደርግም ወይም ህዝብን በሚያስቸግር መልኩ ለምን በአዳራሽ አይደርጉም የሚል ሀሳቦችን ያሰማሉ።

የመፍትሔ ሀሳብ መንግስት እንደነዚህ ትልቅ መንግሥታዊ ስነስርዓት በሚካሄድበት ወቅት ለህብረተሰቡ ተለዋጭ አማራጭ ማመቻቸት እንዲሁም ጉዳዩን በአዳራሽ ውስጥ መከወን ተገቢ ነው።

መረሳት የሌለበት ደግሞ አንድ የህዝብ መንገድ ከመዝጋት በፊት በህግ የተቀመጠውን ለህብረተሰቡ ቀድሙ ማሳወቅ እንዲሁም ከአካባቢው የህዝብ እንደራሴዎች ጋር ውይይት ማድረግ መዘንጋት የለበትም።

https://t.me/JournalistNetsanetGetachew