Get Mystery Box with random crypto!

#መዲናችን_መፀዳጃ_ቤት_ሆነች አሁን አሁን በከተማችን ህዝብ በሚበዛባቸው የከተማዋ እንብርት ስፍራ | (ABC) Amhara Broadcasting Corporation

#መዲናችን_መፀዳጃ_ቤት_ሆነች

አሁን አሁን በከተማችን ህዝብ በሚበዛባቸው የከተማዋ እንብርት ስፍራዎች እንደ መገናኛ ሜክሲኮ አደባባይ እና ሌሎች ሰዎች የሚበዙባቸው አካባቢዎች ላይ እንደ መደበኛ ነገር በመሀል አደባባይ ላይ በፕላስቲክ ላይ ሽንት መሽናት እና መሽናት እየተለመደ ነው።

በተላይ እንዚህ የፕላስቲክ ሽንት መሽኛ ስፍራዎች አካባቢ ላይ ያለው አስከፊ ሽታ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ ማህበረሰብ ከፍተኛ የጤና ችግር ሁኗል ነገር ግን በአካባቢው ያሉ የደንብ አስከባሪዎችም በዝምታ ያለፉት ጉዳይ ሁኗል።

መንግስት ህዝብ እና ተቋማት አካባቢያቸውን ከቆሻሻ ንፁህ እንዲደርጉ እና አረንጓዴ አካባቢ እንዲፈጥሩ ጥሪ በሚደረግበት በዚህ ወቅት እንደዚህ ለትውልድ መልካም አርያ የማይሆን ለከተማ ውበትና ለጤና ችግር የሆነ የመንገድ ዳር የሽንት መሽናት ማሸናት ተግባር ሀይ ሌባል ይገባዋል።

ነገሩ ግን ትኩረት ሳያገኝ ከቆየ ይህ መጥፎ ልምድ እየተበራከተ በመሆደ የሀገራችን የጋራ ከተማ የሆነችውን አዲስአበባ መፀዳጃ ቤት እየሆነች ትመጣለች የሚል ስጋት አለኝ በአካባቢው መጥፋ ሽታ ማሽተት የተለመደ ይሆናል ይህም እንደ ጉንፋ፣ያሉ በሽታዎች በየ ቀኑ የምንጋለጥ እንሆናለን።

የመፍትሔ ሀሳብ በተላይ መንግስት በየ አካባቢው የሰራቸውን የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች በአግባቡ እና ተገቢ በሆነ የክፍያ መርህ ለታለመው አላማ እንዲሰራ ማድረግ በተጨማሪም የከተማ መፀዳጃ ቤት እጥረትን በአግባቡ ጥናት በማድረግ ተጨማሪ ግንቦት ማድረግ እና በዚህ ህጋዊ ባልሆነ ስራ ላይ ጤናቸውን ችግር ላይ የጣሉ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት ችግሩን መፍታት ተገቢ ነው።

በመጨረሻም መልክት እባካችሁ በተቻለ መጠን ከመፀዳጃ ቤት ውጭ ባለመፀዳዳት አካባቢያችንን በጋራ ከበሽታ እንጠብቅ!!

@JournalistNetsanetGetachew