Get Mystery Box with random crypto!

የቻይና መንግሥት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለሚማሩ ለ116 ተማሪዎች በ | Abrehot Library

የቻይና መንግሥት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለሚማሩ ለ116 ተማሪዎች በቻይና ነጻ የትምህርት እድል በዛሬው ዕለት ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይንኛ ቋንቋ፣ ለ6 የሦሰተኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ለ12 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች እንዲሁም ለአንድ ተማሪ የጥናትና ምርምር ነጻ የትምህርት እድል ተሰጥቷል።

ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦሰተኛ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው ።

የአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና እንደገለጹት የትምህር እድል የተሰጣቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው እገዛ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።

ዩኒቨርስቲው በትምህርታቸው እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የቻይና መንግሥት ለሰጠው የትምህርት እድል አመስግነዋል።

እድሉን ያገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር አገራቸውንና እራሳቸውን እንዲጠቅሙ ያስችላል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሺን ቺንሚን ቻይና ለተማሪዎች የሰጠችው የትምህርት እድል የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በቀጣይም የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያን ጥናትና ምርምር እንዲሁም ትምህርት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የትምህርት ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች በበኩላቸው ባገኙት እድል መደሰታቸውን ገልጸው ተምረው እራሳቸውንና አገራቸውን ለመጥቀም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል

የቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ነጻ የትምህርት እድል ከአምስት አመት በፊት የተጀመረ ሲሆን በትምህርታቸው ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል።