Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ዜና ! *ከ404 ሆስፒታሎች 7ኛ ደረጃ! በአዲስአበባ ዮኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክ | Abrehot Library

መልካም ዜና !

*ከ404 ሆስፒታሎች 7ኛ ደረጃ!

በአዲስአበባ ዮኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ትምህርት ቤት የሚገኘው የአጥንት ህክምና ትምህርት ክፍል በ2022 አመተ ምህረት (እ.አ.አ) በመላው ዓለም በ60 ሀገራት ከሚገኙ SIGN IMN የሚባለው የረጃጅም አጥንቶች ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ከሚሰራባቸው 404 ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦፕራሲዮን ከተሰራባቸው የመጀመርያ አስር ማዕከላት መካከል(Top Ten) 7ኛው መሆኑን አሜሪካን ሀገር የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ክፍል የሚገኘው ይህ ፕሮግራም በፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ የሚመራ ሲሆን በመላው ኢትዮጲያ ከሚገኙት 40 ፕሮግራሞች የመጀመሪያውና በርካታ ከባባድ የአጥንት ኦፕራሲዮኖች በማድረግም በአንደኝነት የተቀመጠ መሆኑን SIGN FRACTURE CARE INTERNATIONAL አስታዉቋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ የሚመራው ዲፓርትመንትም ለዚህ ደረጃው ከጤና ሚንስቴር እውቅና ተሰጥቶታል።

የSIGN IMN Fixation System በመኪና አደጋና በጦርነት ለሚከሰቱ የትልልቅ አጥንት ስብራቶች በኦፕራሲዮን ማከሚያ ዋና ፍቱን መሳርያ ሲሆን ዋጋውም ውድ ነው።