Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን ክፋት የሌለበት ቸር፣ በቀል የሌለበት የዋህ፣ ቍጣ የሌለበት ትዕግሥ | ሰዋስው/@zsewasw

ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን

ክፋት የሌለበት ቸር፣ በቀል የሌለበት የዋህ፣ ቍጣ የሌለበት ትዕግሥተኛ፣ ኃጢአት የሌለበት ጻድቅ፣ እድፍ የሌለበት ንጹሕ ፣ ጠማምነት የሌለበት ቅን ነው፣
ያለመከልከል ሰጪ፣ያለ መንፈግ ለጋስ፣ ያለ ቂምና ያለቅናት ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ነው፣

ለሚጠሩት ሰዎች የቀረበ ነው፣ ለሚፈሩትም በጎውን ነገር የሚያደርግ ነው፣ ለሚያንኳኩ ሰዎች የተከፈተ በር ነው፣ ያለ መሰናክል ጥርጊያ ጎዳና፣ እሾህ የሌለበት ንጹሕ ፍለጋ ነው ፣
የአማልክት አምላክ፣ የአጋዕዝት ጌታ እግዚአብሔር እርሱ ብቻ ነው ።
(ቅዱስ ኤጲፋንዮስ)
ድንቅ ሰንበት
ዲን አክሊል ዘሰዋስው
join

@zsewasw
@zsewasw
@zsewasw