Get Mystery Box with random crypto!

ተወዳጆች '፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ' ማቴ | ሰዋስው/@zsewasw

ተወዳጆች

"፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። "
ማቴ 5: 3
ለሁላችንም አንድ አስተማሪ ታሪክ አለ በዜና አበው ላይ የተቀመጠ።
አባ ሖር ይባላሉ ምግብ ሲመገቡ ተቀምጠው ተመግበው አያውቁም ፣እየሄዱ ነው የሚመገቡት፣ እና ከእለታት አንድ ቀን ወደ እርሳቸው የመጣ አንድ መነኩሴ፣ ለምንድነው ተቀምጠው እንደ አባቶች ስርዓት የማይመገቡት ሲላቸው፣ ስጋዬ ደስታ እንዳይሰማው ወደ ኃጢአት እንዳይወስደኝ ብየ ነው።ልክ እንደስራ እንዲየው፣ተቀምጨ ስመገብ ደስታ እንዳይሰማው ብየ ነው አሉ።
አባቶች ምንም ይሁን ከቅድስና ሕይወት የሚያወጣቸው፣ ነገር ፈጽመው አያደርጉትም፣እኛ በዓለም ለምንኖር አባቶቻችን የሚያስተምሩን፣እራሳችን በስራ፣በስነስርዓት ሕይወትን እንድንመራ ነው።
የአባቶቻችን ረድኤት በርከት ይደርብን።
ድንቅ እለት ተመኘሁ
ዲን አክሊል ዘሰዋስው
ነሐሴ 20-2014 -ጎንደር ኢትዮጵያ
join
@zsewasw
@zsewasw
@zsewasw