2022-11-02 13:47:31
❖አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
✠A) ማውጫ (Table of contents)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
✠B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው ሃሳቦች
☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡
✠C) መግቢያ (Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡
✠D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ
ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡
✠E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ
ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
✠F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-
☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡
✠G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-
☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡
✠H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-
☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡
✠I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-
የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቼና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡
✠J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-
☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡
☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡
✠K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):
ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-
☞ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
☞ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
☞ የግምገማ ዕቅድን
☞ ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ
✠L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):
ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
When you need professional support contact us with the following phones
ለእገዛ @researcher13 or
@promoter14 ላይ ይጠይቁ
+251966368812
Channel https://t.me/+VkMfRkfah72HjeSS
Group https://t.me/joinchat/3KxEeE-mxXs2MGQ8
1.1K viewsedited 10:47