Get Mystery Box with random crypto!

ጥሩ የዲፌንስ ፍረሃትን ማስወገጃ ዘዴዎች መመረቂያ ፅሁፋችሁን ለምታቀርቡ ተማሪዎች የተዘጋጀ ፍ | Research

ጥሩ የዲፌንስ ፍረሃትን ማስወገጃ ዘዴዎች

መመረቂያ ፅሁፋችሁን ለምታቀርቡ ተማሪዎች የተዘጋጀ

ፍርሀትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን?


ፕረዘንቴሽን በትምህርት ሂወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን ሂደቶችና የመፈተኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ላይ መምህራን አሳሳይንመንቶችን ፣ ፕሮጀክቶችን ፣ የምርምር ስራዎችን እና የመሳሰሉትን ተማሪዎች በክላስ ውስጥ ፕረዘንት እንዲያደርጉ ይጠይቃሉ፡፡

ከትምህርት አለም ውጪም በተለያዮ የስራ ጉዳዮች ላይ ፕረዘንት እንድናደርግ ሊጠበቅብን ይችላል፡፡
ታዲያ በፕረዘንቴሽን ጊዜ የብዙዎች ችግር ፍርሀት ነው፡፡ ሰው ፊት ቆሞ የመናገር ፍርሀት፡፡
የፕረዘንቴሽን ፍርሀት የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እስከ 80 % የሚሆኑትን ሰዎች ጋር ያለ ችግር ነው፡፡ በእርግጥ ችግር ነው ተብሎም ሊነሳም አይችል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መምህራንን ጨምሮ የ public speaking ልምድ ያላቸው አርቲስቶች፣ ፓለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች ሁሉ የሚጋሩት common ስሜት ስለሆነ ነው፡፡

ይህ የፕረዘንቴሽን (public speaking) ፍርሀት ጤናማ ስሜት ነው፡፡ የሁሉም ሰው የጋራ ሰሜትና እንዲያውም የራሱ ጥቅሞችም ያሉት ስሜት ነው፡፡ ችግር የሚሆነው ፍርሀቱ በጣም ከበዛና ቅጥ ካጣ ነው፡፡
የሚከተሉት መንገዶች የፕረዘንቴሽንን ፍርሀት ለመቀነስና ውጤታማ ፕረዘንቴሽን ለማድረግ ያግዛሉ፡፡
#1 . የፕረዘንቴሽን ፍርሀት ጤናማና common ስሜት እንደሆነ መረዳት፡፡
Literally ሁሉም ሰው ይፈራል፡፡ ልዮነቱ፡አንዳንዶች ማኔጅ ያደርጉታል አንዳንዶች አያደርጉትም፡፡
ይህ የፍርሀት ስሜት ሊያስደነግጠን ሳይሆን በደንብ እንድንዘጋጅ ሊያመላክተን ይገባል፡፡
ፍርሀት ጥቅም አለው፡፡ ይሄውም ባዮሎጂካሊ በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞንን መጠን ከፍ በማድረግ የበለጠ ኢነርጂ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
#2 . ፕረዘንቴሽን ልምምድ (rehearsal )
ፕረዘንቴሽን ልምምድ ይፈልጋል፡፡ ፕረዘንት የምናደርገውን ነገር በደንብ ማወቃችንን፣ ቋንቋችንን፣ ድምፃችንን እንዲሁም ሰአት አጠቃቀማችንን የምናስተካክለው በልምምድ ኀው፡፡
ፕረዘንት የሚያደርግ ሰው ልክ እንደ መድረክ ተዋናይ ነው፡፡ ፕረዘንቴሽንም በራሱ በተወሰነ መንገድ ትወና ነው፡፡ በመሆኑም ማንም ተዋናይ በደንብ ሳይለማመድ መድረክ ላይ እንደማይወጣ ፕረዘንት የሚያደርግ ሰውም በበቂ ሁኔታ ልምምድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
በምንለማመድበት ጊዜ ጓደኞቻችን ፊት ሊሇን ይችላል ወይም ብቻችንን ቆመን ሰው ፊት እንዳለን በማሰብ መለማመድ ይቻላል፡፡
" Practice makes perfect"
#3 . መረጋጋት፣ እራስን ማረጋጋት
#4 . በቂ አየር መውሰድ ፣ መተንፈስ
#5 ፕረዘንት የምናደርግበትን ቦታና መምህራኑን ቀድሞ ማወቅ፡፡ ይህም ሲባል ፕረዘንት የምናደርግበት ቦታ ቀደም ብለን በመሄድ ማየትና የምንቆምበትን ቦታ ስሜቱን መረዳት ነው፡፡
#6 . አለባበስን ማስተካከል፡፡ ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንን ይጨምራል፡፡
#7 . ፕረዘንት የማድረግ ፍላጎትን ማዳበር፣ ይህም ሲባል ፕረዘንቴሽንን እንደ ግዴታ ሳይሆን የሰራነውን ነገር ለሰዎች እንደምናሳይበት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መውሰድ፡፡
#8 . በቂ አረፍት ወስዶ መገኘት
#9 . ቀደም ብሎ መገኘት (አለማርፈድ)
#10 . ከመጀመሪያው ውጤታማ ስራ መስራት፡፡ ምክንያቱም የአንዳንዶች የፍርሀት ምንጭ በቂ ስራ ካለመስራትና ካለመዘጋጀት ነው፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው

#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራም ቻናላችን ምርጥ ምርጥ ስራዎችን እና ነፃ የትምህርት እድሎችን /scholarships መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/vacancy3

በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this channel
#ሼር_ያድርጉ

@zresearcher @zresearcher

Research ከtitle መረጣ እስከ ማጠቃለያ (Discussion, conclusion and reccomendation 
ማንኛውንም አይነት አሳይመንት እናግዛለን።
ማንኛውንም እገዛ በጥራት እና በፍጥነት
ለእገዛ  
@researcher13 or
          
@promoter14 ላይ ይጠይቁ
          
+251966368812
Channel
@zresearcher
Group
https://t.me/joinchat/3KxEeE-mxXs2MGQ8
Don't forget to
#follow_us_and_Share !

#Share #Share #Share. #Share #Share