Get Mystery Box with random crypto!

#ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ #የመመረቂያ_ጽሁፍ_ሪሰርች_ለሚሰሩ_ለተመራቂ_ተማሪዎች Good re | Research

#ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ

#የመመረቂያ_ጽሁፍ_ሪሰርች_ለሚሰሩ_ለተመራቂ_ተማሪዎች

Good research presentation (Defense)
ጥሩ አቀራረብ እንዲያደርጉ የሚረዱዋችሁን አንዳንድ ነጥቦች።
ጥናታዊ ጽሑፍን በጥሩ ሁኔታ ለማቅረብ (good presentation) ከሚረዱ ቁልፍ ነገሮች አንዱ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (PowerPoint) ነው። እርስዎ #ጥሩ ማብራሪያ ነጥብ (power point) እንዲኖርዎ ደግሞ እነዚህን ይጠቀሙ፦
.
#1ኛ . ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Powerpoint) ብዙ ስላይድ አይኑረው። በ15 ደቂቃ ለማቅረብ እስከ 15 በዛ ከተባለ ከ20 እስከ 25 ማሳያ (slide) እጅግ በቂ ነው።
«Oral presentation is visual as well as an auditory medium» በቃልዎት የሚያብራሩት ቢሆን የተሻለ ዋጋ ያለው መሆኑን እና የጥናቱ ባለቤት መሆንዎን የሚያረጋህጥ መሆኑን አይርሱ።
.
#2ኛ . ማሳያ (slide) በብዙ ጽሑፍ የተጠቀጠቀ መሆን የለበትም። ከጽሑፍ ይልቅ ፎቶዎችን፣ ግራፎችንና ሰንጠረዦችን በደምብ ይጠቀሙ። "አንድ ፎቶ ወይም ሰንጠረዥ ከ1000 ቃላት በላይ ገላጭ ነው" የሚለውን አባባል ልብ ይበሉ።
.
#3ኛ . መብራራት የሚፈልጉ ቃላትን ብቻ በርዕስ መልክ ይጻፉ። ማብራሪያቸውን የግድ ማሳያ (slide) ላይ መፃፍ አይጠበቅብዎትም።
«One of the most common fault or error commited by graduate student is to write every single words and detail full sentences on their slides» ነው የሚለው። Please never crowd each slide !!!
.
#4ኛ . የሚቀርበው ጥናት እጅግ ሰፊ ይዘት ያለው ቢሆን ለመመጠን ሳይቸገሩ በማሳያ (slide) ላይ ለመዳሰስ ማሳያዎትን (slide) በክፍል በክፍል (part) ይክፈሉት።
....... Introduction (መግቢያ)
....... Main Body (ሃተታ) as Discussion
....... Conclusion ( መደምደሚያ) ያድርጉት።
.
#5ኛ . ከአንዱ ማሳያ (slide) ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ (ሲሸጋገሩ) ጊዜ እንዳይወስድብዎ (እንዳይንቀረፈፍ) Animation ባይጠበሙ ይመረጣል።
.
#6ኛ . በማሳያዎ (slide) ላይ የሚሰፍሩ ጽሑፎች በትንሹ በ24 መጠን (Font Size) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ከዚያ በታች ከሆኑ ላይታዩ ስለሚችሉ ታዳሚዎትን ያስከፋሉ፣ ሥራዎትን ይደብቃሉ ማለት ነው።
.
#7ኛ . የጽሑፎቹ ቅርጽ አይነት (Font type) "Time new roman" ቢሆን የተሻለ ነው። ከዚህ ካለፉ ግን Nyala እና Countur ይጠቀሙ።
በተለይ ግን script አይነት ቅርፅ ያለው ጽሑፍ አያድርጉት። የማሳያው ጀርባ ወይም መደብ (Background) ከፊደሎቹ ቀለም (font color) ፍጹም ተቃራኒ ቀለም ያለው መሆን አለበት። ብዙ ጊዜ በነጭ መደብ ላይ ጥቁር ቀለም ያላቸውን ፊደላት (ጽሑፎች) መጠቀም ቢችሉ ይመከራሉ።
.
#8ኛ . ሙሉ ሃሳብዎን ለመግለፅ ትላልቅ ፊደላትን (Capital letter) ከመጠቀም ይቆጠቡ። ለማንበብና ለመረዳት ቀላሉ ትናንሽ ፊደላትን (Small letters) መጠቀም መሆኑ አይዘንጉ።
.
#9ኛ . የማሳያ (slide) ጽሑፎች እጅግ ብዙ የቀለም (Font colour) ዝብርቅርቅ የበዛበት ከሆነ አትኩሮትን ግራ ስለሚያጋባ ብዙ ቀለም አይጠቀሙ። ከተቻለ በአንድ አይነት ቀለም ቢሆን ካልሆነ ግን ልዩ ገለጻ የሚፈልጉትን ለማቅለም ሁለት ቀለሞች በቂ ናቸው።
.
#10ኛ . የ (Spelling of words, gramatical structure of sentences, punctuations… ) ስህተት እንዳይኖርብዎት ቢጠነቀቁ የተሻለ ውጠኣማ ይሆናሉ።
#11ኛ . አስተያየት (professional recommendation) በሚለው የጥናት ክፍልዎ ውስጥ ከተማሩበት አንጻር ለደረሱባቸው ችግሮች መንገዶችን ለመጠቆም ይሞክሩ ይንጅ "#ድርጅቱ_ይህንን_ችግር_ማስተካከል_አለበት" የሚል ደረቅ ትዕዛዝ ከማስገባት ይቆጠቡ። የሚያስተካክለው እንዴት ባለ ዘዴ፤ መቼ፣ በማን፣ የት፣ ለምን.. እንደሆነ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትዎን አይርሱ።
.
#11ኛ. ያዘጋጁትን ማሳያ (slide) ከማቅረብዎ በፊት ደጋግመው ያንብቡ።
.
አዘጋጁ
~ አለባበሱ ?
~ ከሰላምታ ጀምሮ እስከ ምስጋና ያለው አነጋገሩ ?
~ መጠቀም የሌለበት ቃላት ?
~ የቡድን ሥራ ሲሆንስ ?
~ ጥያቄና መልስ ምን መምሰል አለበት ?
የሚሉትን በቀጣይ ክፍሎች ለመዳሰስ እንሞክራለን። Research ከtitle መረጣ እስከ ማጠቃለያ (Discussion, conclusion and reccomendation 
ማንኛውንም አይነት አሳይመንት እናግዛለን።
ማንኛውንም እገዛ በጥራት እና በፍጥነት
ለእገዛ  
@researcher13 or
          
@promoter14 ላይ ይጠይቁ
          
+251966368812
Channel
@zresearcher
Group
https://t.me/joinchat/3KxEeE-mxXs2MGQ8
Don't forget to
#follow_us_and_Share !

#Share #Share #Share. #Share #Share