Get Mystery Box with random crypto!

ሩስያ ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን #ወዲያው እ | Zodiac Sign

ሩስያ ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን #ወዲያው እንደምታቆም አስታወቀች።

ሩስያ ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ፦

1ኛ. ወታደራዊ እርምጃ እንድታቆም።

2ኛ. ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ህገመንግስቷን እንድትቀይር (እንደ #NATO አይነት ጥምረት ውስጥ እንዳትገባ እንድታረጋግጥ)

3ኛ. ክሬሚያን እንደ ሩሲያ ግዛት እንድትቀበል።

4ኛ. የዶንቴስክ እና የሉሀንስክ ተገንጣይ ሪፐብሊኮችን እንደ ነፃ ሀገር እንድትቀበል የሚሉት ናቸው።

እነዚህ ከተሟሉ ሩስያ ዩክሬን ውስጥ ምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ ወዲያውኑ እንደምታቆም ገልፃለች።

የክሬምሊን ቃልአቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በስልክ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ ዩክሬን ቅድመ ሁኔታዎቹን እንደምታውቅ እና ተፈፃሚ የሚሆኑ ከሆነ የወታደራዊ ዘመቻው ወዲያውኑ እንደሚቆም እንደተነገራት ገልፀዋል።

ከዩክሬን ወገን በኩል ወዲያው የተሰጠ ምላሽ የለም።

በሌላ በኩል ፥ የሩስያ እና ዩክሬን ሶስተኛው ዙር ድርድር ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

via tikvahethiopia