" ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር " - ቮልድሚር ዜኔንስኪ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ጠያቄ አቀረቡ። ዜሌንስኪ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው። ፕሬዜዳንቱ ፤ " ጦርነቱን ለማቆም #ብቸኛው አማራጭ ከፑቲን ጋር በቀጥታ መነጋገር ነው " ብለዋል። ዜሌንስኪ ለፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ሩሲያን እያጠቃን አይደለም፤ ለማጥቃትም እቅዱ የለንም። ከእኛ ምንድነው የምትፈልገው ? መሬታችንን ትልቀቅ " ብለዋል። ፕሬዜዳንቱ አክለው ፤ " ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር። 30 ሜትር ሳይርቅ " በማለት ፑቲን ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ጋር በረዥሙ ጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ያደረጉትን ንግግር አስታውስዋል። ዜሌኒስኪ በመግለጫቸው ላይ #ምዕራባውያን ተዋጊ አውሮፕላኖችን እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። " የአየር ክልሉን መዝጋት የማትችሉ ከሆነ ፤ አውሮፕላኖችን ስጡኝ " ሲሉ ነው ዜሌንስኪ የጠየቁት። ምዕራባውያን የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዩክሬን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ የዩክሬንን አየር ክልል እንዲዘጉ ሲጠየቁ ቆይተዋል። ዜሌንስኪ ፤ " በቀጣይ ሩሲያ ላትቪያ ፣ ሊትዌኒያ እና ኢስቶኒያን ልትወር ትችላለች " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሌላ መረጃ ፥ የሩስያ እና ዩክሬን ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ዛሬ በቤላሩስ ተጀምሯል። via tikvahethiopia 4.1K viewsedited 18:25