Get Mystery Box with random crypto!

💖 ዝማሬ መላዕክት 💖

የቴሌግራም ቻናል አርማ zmaremelaekt — 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖 ዝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zmaremelaekt — 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖
የሰርጥ አድራሻ: @zmaremelaekt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.39K
የሰርጥ መግለጫ

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ዝማሬ መላዕክት።
👇ተቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/Y3OMR1rU9lk1NmU0
ለማንኛውም ሃሳብ፣አስተያየት
በ👉 @Elaa24u @Te_best 👈 ወይም
በ👉 @Zmaremelaekt_Bot 👈 ላይ ያድርሱን።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-05 21:36:38 ባለ ውለታዬ
ሊቀ.ቴድሮስ ዮሴፍ
===============
ባለውለታዬ /2/
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
አዝ------------------------------//
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አደርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘኝ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /2/
አዝ------------------------------//
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
አንድ ወርድ ከዛፉ አዘዘኝ ጌታዬ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /2/
አዝ------------------------------//
ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አያቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሠላም ሂድ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ /2/
አዝ------------------------------//
የማምነውም አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ሥራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ /2/
1.0K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:33:15 <<ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ>>
ማር 13፡18


ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው

#ክረምት የብሉይ ኪዳን ዘመን ምሳሌ ነው

የክረምት ገበሬ ጠዋት ጾሙን ይወጣል
ቀን ከላይ ዝናም እየወረደበት ከታች ጭቃ እየሆነበት ሲሠራ ውሎ ማታ እራት ጎመን ይቀርብለታል
ድካምና ረኃብ
ፍርሃትና ስቃይ ይፈራረቁበታል!
ነቢያት በዘመነ ብሉይ እንዲሁ ነበሩ።
ያለ ልጅነት ወጥተው ያስተምራሉ ፤ትንቢት ይናገራሉ
ሲመሽ ማታ (ሲሞቱ) በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደሲኦል ይወርዳሉ(የጎመን እራት)!


#ክረምት የቃል ኪዳን መገለጫ ነው

ክረምት በብሉይም በሐዲስም ከተደረጉ ኪዳናት ጋር ተያይዞ ይገለጻል
በተለይም ቅዱስ ያሬድ ክረምትን ከኖኅ ኪዳን ጋር እያነጻጸረ የገለጸው የዜማ ድርሰት አስደናቂ ነው
"ያከርም በበዓመት ተዘኪሮ ዘመሐለ ለኖኅ ገብሩ" የሚያስደንቀኝ ገለጻ ነው! (ዘፍ 8፥22)

#በክረምት፦

መብረቅ
ነጎድጓድ
በረድ (በረዶ)
ማዕበል ሞገድ አለ

ሰማዩ ይጠቁራል
ደመናው ይከብዳል
መሬቱ ይላላል
ወንዙ ይሞላል
ዘመድ ከዘመድ ሳይጠያየቅ ይከርማል
ስለዚህም በዚህ ወቅት ወርኀ ክረምቱን በሰላም እንዲያሳልፍልን ጸሎት/አስተምሕሮ ይደረጋል
ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው የአስተምህሮ ጊዜው የዚሁ አካል ነው።

ዝናሙ ዝናመ ምሕረት
ጠሉ ጠለ በረከት
ነፋሱ ነፋስ ምሕረት እንዲሆን አስተብቁዖት(ምልጃ) ሊደረግ ይገባል።

#ክረምት የምጽአተ እግዚእ ምሳሌ ነው
ማቴ 24፥27

ክረምት የጌታ መምጣት የዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ሆኖም ይነገራል
በክረምት ከሚሰማው ነጎድጓድ በላይ የሆነ ነጎድጎድ በዕለተ ምጽአት ይሰማል
ጌታም እንደ መብረቅ ብልጭታ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ያለ ወሰን በምልዓት በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ይገለጣል
ይህን እያሰብን በጎ እንድንሠራ ክረምት አስፈሪ ምልክቶች ይታዩበታል!
ምልክቶቹም አቅማችንን አውቀን፣ ተፈጥሮ ከእኛ አቅም በላይ መሆኑን ተገንዝበን ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ የሚያሳስቡ ናቸው!

#በዚህ ክረምት መርከብ መሥራት በመርከቡ መቀመጥ ያስፈልጋል

#መርከቡም፦
ሃይማኖት
ቤተ ክርስቲያን
ጸሎት
ንስሐ
በጎ ሥራ ነው!

"ግበር ታቦተ በዘትድኅን" የምትድንበትን መርከብ ሥራ!
አምላካችን እግዚአብሔር ክረምቱን በሰላምና በጤና ያሳልፈን!!!

አሜን!
1.3K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:47:35 ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::
https://t.me/zmaremelaekt
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 27 2013 ዓ.ም
1.4K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:04:34 ከሰይጣን ዓላማዎች አንዱ፦
ወደ ክርስቶስ የሚያሳዩ ምልክቶችን ማጥፋትና እርሱን የሚያሳስቡ ሕያዋን ሐውልቶችን ማፍረስ ነው፡፡
==========================
★ 2ቆሮ. "በሰይጣን እንዳንታለል ፣
የእርሱን አሳብ አንስተውም"

ሰይጣን በእባብ ገላ ተሰውሮ ክፋት ያላወቁትን አዳምንና ሔዋንን አታሏቸዋል፣ ያላቸውንም ሁሉ አሳጥቶ ባዶ አስቀርቷቸው ነበር ፡፡
እንደ ተስፋው ቃል የአዳምና የሔዋን ዘር የቅድስት ፣ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ፍጹም ሰው ሆኖ ምንም የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት በምድረ በዳ ከሰይጣን የቀረበለትን ፈተና ሁሉ ድል አደረገ፡ ይልቁኑ ሰይጣን ራሱ ተሸንፎ አፎሮ ባዶው ተመለሰ እንጂ፡፡

እኛም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆን የእግዚአብሔር ልጆች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ነንና በሰይጣን አንታለልም ፣ ከሰይጣን ተንኮል የሚበልጠው የመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በውስጣችን ስላለ፡፡
=========================
✿ በሰይጣን ወጥመድ ፈጥነው
የሚወድቁት እነ ማናቸው?

1ኛ ወደ እወነት ያልመጡ ፍጥረታውያን ሰዎች፡፡
2ኛ በክርስትና ትምህርት ሕጻናት የሆኑ ወይም ያልበሰሉ ክርስቲያኖችን ናቸው፡፡
ማቴ 13፥18-23
===========================
★ የሰይጣን መንገድ ፦

ፍጥረታውያን ሰዎች ጭራሹኑ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ዘለዓለም ሕይወት እንዳያስቡ ፣ ራሳቸውን እንዳያውቁ እንዲሁ እንደ እንስሳት እንዲኖሩ ዐይነ ልቡና ቸውን ያሳውራቸዋል ፣ ያደነዝዛቸዋል ያደነቁራቸዋል፡፡

ይህ እኳ ባይሳካለት ከክርስትና ውጪ የሆነ ክርስቶስን የሚጠላ ሃይማኖት እንዲመሰርቱ ያደረጋቸዋል ይህም በተዘዋዋሪም እርሱን እንዲያመልኩ ማለት ነው ፡፡

ስለ እግዚአብሔር ፣ ስለ ዘለዓለም ሕይወት ፣ ስለ ክርስቶስ መምጣት ፣መከራ ፣ሞትና ትንሣኤ ማሰብና መናገርን እንደ ሞኝነት እንዲቆጠሩ፣ እንዲፀየፉት ያደርጋል፡፡

ወደ ኢየሱስ ክርስቶሰቶ ሊያመለክቱ የሚችሉ ምልክቶችን ፣ እርሱን የሚያሳስቡ ነገሮችን ሁሉ ማስረሳት ፣ ማጥላላትና ማጥፋቶ ነው፡፡

በአንድ ወቅት የኢየስስ ክርስቶስ ስም በምድር ላይ ዳግመኛ እንዳይነሣ ፣ በይሁዳና በአይሁድ ልብ አድሮ ንጹሁ ክርስቶስ ለኃጢአተኞ ተላልፎ እንዲሰጥ ፣ ዘግናኝ መከራ እንዲቀበል ፣ ከሞት ሁሉ የከፋውን የመስቀል ሞት እንዲሞት አደረገ፡፡

ክርስቶስ ግን መሞቱ ለመነሣት ነበርና አስቀድሞ እንደሚነሣ በተናገረው መሰረት ሙስና መቃብርን አጥፍ መግነዝ ፍቱልኝ ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል " ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም" ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረውየይሁዳው አንበሳ ሞትንና ሲኦልን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ ሐዋ 2 ፥ 24

ከበፊቱ ይልቅ የትንሣኤው ዜና
ያስደነገጣቸው ሰይጣንና አይሁድ የትንሣኤውን ብርሃን በገንዘብና በሐሰት በተፈጠረ ተረት ለመቅበር ሙከራ አደረጉ፡፡

ይኸውም ለመቃብር ጠባቂዎቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት "እኛ ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ" በማለት (ማቴ.28 ፥13) በሐሰት ትርክት የትንሣኤውን መልካም ዜና ለመቅበር ሞከሩ።

ሰይጣን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰዎች የክርስቶስን የመምጣቱን ፣ የመከራውን ፣ የሞቱንና የትንሣኤውን ዋና ዓላማ እንዳያያዩና እንዳይረዱ የሚጠቀመው በዋናነት ገንዘብንና በገንዘብ ፍቅር የሰከሩ የሐሰት አሰተማሪዎች ነው፡፡

★ሰይጣን ሰዎች ክርስቶስን እንዳያዩ የትኛውንም መጋረጃ ይጠቀማል ፣ ወደ ክርስቶስ እንዳይደርሱ መንገዶቹን ሁሉ ለመዝጋት ሰከንድ ሳያባክን ይሞክራል፡፡

★ የሰይጣን ትልቁ ፈተና ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዳያወሩ አይደለም አጥብቆ የሚታገለው ሰዎች ክርስቶስን በትክክል እንዳይረዱ ፣ እንዳያዩ ፣ በእምነት ፣ በንስሓ ወደ ክርስቶስ እንዳይቀርቡ ነው፡፡ ማቴ.7 ፥21

> ገላ .3 ፥1 "የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ከዐይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር ፣ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማነው? "

ለዚህ ጥያቄ መልሱ ከሰይጣን ውጪ ማን ሊሆን ይችላል!? የሚል ነው ። በዐይናቸው ፊት ያለውን ማየት እንዳይችሉ አደንዝዟቸዋል፡፡

★ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ጥቂት መረጃ ስላገኙ ብቻ ክርስቶስን እንዳወቁ እንዲሰማቸው አደረጋቸው ይህ አንዱ የሰይጣን ማደንዘዣ ወይም አዚም ነው፡፡

★ አንዳዳንዱን ደግሞ በየመንገድ ዳርና በተመቻቹ ፣ ባሸበረቁ አውደ ምሕረቶች ስለ ኢየሱስ ስለተናገሩ ብቻ ወንጌል እንደሰበኩ እንዲያስቡና በዚህ ረክተው አርፈው እንዲቀመጡ በውዳሴ ከንቱ ጠላልፎ እግረ ልቡናቸውን ሽባ አድርጎ አስቀመጣቸው፡፡

በየ አውደ ምሕረቱም ሆነ ባገኘነው አጋጣሚ ሰዎች ክርስቶስን አምነው ፣ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ማድረግ መልካም ቢሆንም ይህ ብቻውን ግን ወንጌል መስበክ አይደለም፡፡ ወንጌል ሕይወት ነው፡፡ ክርስቶስ መገለጥ ያለበት በአንደበታችን ብቻ ሳይሆን በሕይወታችንም ነው፡፡
★ላልዳነውና እየጠፋ ላለው ዓለም የክርስቶስን ፍቅርና ማዳን የምንገልጠው ባማረ አንደበትና ልብስ ሳይሆን በፍቅርና በቅድስና በተሞላ ሕይወት ነው፡፡

★ ሰይጣን ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አንንዳይመለከቱ ምልክቶችን ያጠፋል ፣ ክርስቶስን የሚያሳስቡ ሕያዋን ሐውልቶችን ያፈርሳል ካልን ፦

እስኪ እነዚህ ምልክቶችና ሕያዋን ሐውልቶች ምንድናቸው የሚለውን እንመልከት ..........(ይቀጥላል)



24/10/2014 ዓ/ም
1.5K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:15:46 ተወዳጆች ሆይ በመንፈሳዊው ህይወታችን
:ስለ ሰላም ዋጋ የምንከፍለው ፣ወንጌል የምንሰብከው፣ መከራ የምንቀበለው፣ የራሳችንን ክብር በሰዎች ዘንድ ለመገንባት ነው? ወይስ በወንጌል ስም ታዋቂ ለመሆን?
ወይስ በኛ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ብርሃን አለምን ለማሳየት?
በእውቀት ልካችን ወንበር ለማደላደል?
ወይስ ዓላማችን ሰላምን በህዝብ ልብ ውስጥ ለማስረጽ ነው?
ስለክርስቲያኖች መገለጫ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል።
''በእኔ ሳላችሁ ... በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ... '' ዮሃ 16፣13
ደግሞም
''በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ....።'' ይላል።
ማር 13;13
አይገርምም በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ይላል:
ወንድሜ ግን አንተ ስለስሙ ትጠላ ይሆን? የተጠላሃውስ በየትኛው ግብርህ ነው? በርባንነትህ ነው? ወይስ በህያው ብርሃን ስም አይን ስላበራህ?
የተጠላኸው ሠላምን የተጠማች አለም የህይወትን ውሃ ከሆድህ ስላፈለክላት? ወይስ ስለ እኔነትህ ውበት ብቻ እየተናገርክ?
የተጠላኸው በምድር ስላለችው የእግዚአብሔር መንግስት ተልዕኮ ለመፈጸም አቅም አጥተህ ነው? ወይስ አንደበትህ ስለተሳሰር ይሆን?
ወንድሜ አንተን አለም ስትጠላህ ስንፍናህ ሸክም ሆኖባት ነው። ስንፍናህን የእግዚአብሔር ቸርነቱ ተጨምሮበት ፣ በትጋትህና በትምህርት ልትለውጠው ትችላለህ። ይሄ ግን የሰማዩን በር አይከፍትልህም። ሸክምህን ተሸክሞ ነጻ ስላወጣህ እውነት የተጠላህ ጊዜ ግን በምድርም በሰማይም ባለጸጋ ነህና በእግዚአብሔር ዘንድ ትከብራለህ።ደስ ይበልህ፡፡
ቃሉ ህያው ፣ ዘመንም ተሻግሮ የሚሰራ ነውና በእውነት ደስ ይበልህ፡፡ አለም የምትመስልህና የምትወድህ ከሆነ እንደ ማስቲካ አኝካ ሳትተፋህ አስቀድመህ በሞተልህ ክንድ ተደገፍ።ምንም ብትጠላህ ጣዕሟ አንተ ነህና። በመውጣት በመግባት ዘመንህ ሁሉ የሰማይ ቤትህን ለመስራት እሩጥ።
መከራም የሚበረታው ስለ ወንጌል ስለ ስሙ መከራ በሚቀበሉት ላይ ነው። ስለዚህም የማዕዘኑ ራስ ዲንጋይ ስለሆነው ክብር ፣ ስለ ሃይማኖት የሚከፈል ዋጋ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን፣ የክብሩም ተካፋይ ያደርጋል፡፡ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብራለች እንዳለች እመቤታችን። ለመክበር እግዚአብሔርን በህይወትህ አክብር። እግዚአብሔር ውለታ አይረሳምና ብድራትንም ይከፍላል። ስሙ ቡሩክ ይሁን።አሜን፡፡
1.9K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:49:32 #ኪዳነ_ምህረት_እናቴ

ኪዳነ ምህረት እናቴ
ሚስጥረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሰአይወጣ ሳልነግርሽ /2/

#አዝ
አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውሃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ በአንቺ ታበሰ /2/

#አዝ
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልርሳሽም እናቴ /2/

#አዝ
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የእኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደ ሚፈፀም አውቃለሁ
ሁሉን በግዜው አያለሁ /2/

#አዝ
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባየ ቀድሞ ዝም አልኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂኝ /2/
1.7K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 22:36:24 https://www.facebook.com/117159900989698/posts/122630307109324/?flite=scwspnss
1.7K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 13:22:39 https://www.facebook.com/117159900989698/posts/128282659877422/?flite=scwspnss
1.8K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 22:53:47 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን
2.0K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 08:07:47 ፍ ሬ የ ለ ቅ ጠ ል ብ ቻ
ተ ግ ባ ር የ ለ ም ወ ሬ ብ ቻ ፡፡
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ዛሬ ጠዋት አንድ ሱቅ በር ላይ" በትዕዛዝ እንደፋለን " የሚል ጽሁፍ ተንጠልጥሎ አየሁ፦
ባለሱቋም ደጃቸውን እያጸዱ ነበርና ጠጋብዬ "ምንድ ነው የምትደፉት ? ስል ጠየኳቸው፡፡
አሳቸውም ቆፍጠን ብልው " እኛስ በትዕዛዝ ዳቦ እንደፋለን " አንዳንዱ ግን ያለ ማንም ትዕዛዝ ሌሊት ሌሊት በሰው በር ላይ ቆሻሻ ይደፋል" አሉ፡፡
ታዲያ "ዳቦ " የሚለው ጽሁፍ የት አለ? ብዬ ደግሜ ስጠይቅ " አይ ምን ዳቦ አለ? "ዳቦ የሚለው ጠፍቶ " አሉ፡፡

✿ እኔም ዳቦው ጠፍቶ "በትዕዛዝ መድፋት"
ብቻ ቀረ ? ብዬ ደጋግሜ ማሰላሰሌን በጠልኩ፡፡
============================
✿ ማስታወቃያ ብቻ ፦
=============
ዘመኑ የማስታወቂ ነው ፣ ሰውንም ይሁን ፣ ሥራን ፣ ምግብንም ይሁን ሀገርን ማስተዋወቅ መልካም ቢሆንም ነገር ግን ከሚተዋወቀው ነገር በላይ ማስታወቂያው ከበለጠ ወይም እንደተገለጠው ካልሆነ ውሸት ይሆናል፡፡

✿ ቴሌቪን ስትከፍት ለ30 ደቂቃ ፕሮግራም 40 ማስታወቂያ ማየት ግድ ነው፣ ጆሯችንን ባደነቆረው ማስታወቂያ ተመርተን አንድ ዕቃ ብንገዛ አብዛኛዎቹ ከእውነቱ በጣም የራቁ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
✿ በተለያየ መድረክ ሙስና (ሌብነት) ሲወገዝ እንሰማለን ፣ ከልቡ ሌብነትን የሚጠላ ግን በጣም ጥቂት ነው፡፡

✿ ጤና ጣቢያ ፣ሆስፒታልም ሆነ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በር ላይ ጽፈው ከለጠፉት ዓላማቸውና ተልዕኳቸው በተቃራኒ ሆነው አናያቸዋለን፡፡

✿ መስሪያ ቤቶችና ሠራተኞች አሉ ሥራ ግን የለም፡፡ አሁን ሀገራችን ላይ ሕዝብ የማይንገላታበትና የማይማረርበት መስሪያ ቤት የቱ ነው!?፡፡

✿ ተግባር የለ ወሬ ብቻ ፣
ፍሬ የለ ቅጠል ብቻ ።

ተግባር ጠፍቶ ወሬ ብቻ ቀርቷል፡፡
መልካም መልካሙ ጠፍቶ ክፉ ቀርቷል፡፡
ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ነግሷል፡፡
አንድነት ጠፍቶ ዘረኝነት ነግሷል
እኛነት ጠፍቶ እኔነት (የኔነት) ነግሷል፡፡
ሰዎች ተብለው የሚጠሩ አሉ ሰውነት/ሰብዓዊነት ጠፍቷል፡፡
ትዳር አለ ፍቅር ግን የለም፡፡
በሁሉም ዘርፍ የነገሮቻችን በድኑ አለ ሕይወት ግን የለውም፡፡
===========================
✿ ግብዝነት( ማስመሰል) ብቻ፦

★ ቤተ ክርስቲያን አለች እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡

★ የንስሓ ስብከትና የንስሓ አባት አለ ንስሓ የሚገቡ ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡

★ቅዳሴ አለ ፣ የሚያስቀድሱም ብዙናቸው በቅድስና የሚኖሩና የሚቆርቡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡
★ ሰዓታቱ ፣ሥርዓተ ማህሌቱ አለ ከልቡ የሚያመሰግን ግን ጥቂት ነው ፡፡

★ ክብረ በዓላት እጅግ ብዙ ናቸው እግዚአብሔርን ማክበሪያ መሆኑ ቀርቶ በገንዘብ መክሪያ ሆነዋል ፡፡
★የጾም ወራት ብዙ ናቸው ፣ እውነተኛ ጿሚዎች ግን ጥቂት ነው፡፡
★ የቃሉ ሰባክያን እጅግ ብዙ ናቸው ፣ በሕይወታቸው ምሳሌ የሚሆኑ ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡
★ ነጭ ለብሶ የሚመላለስ ብዙ ነው ንጹሕ ልብ ያለው ግን ጥቂት ነው፡፡

★በቅዱሳን ስም የሚጠሩ ብዙዎች ናቸው በእምነትና በምግባር ቅዱሳንን የሚመስሉ ግን በጣም ጥቂቶችና ነው፡፡

መፍትሔው አንድ ነው የተግባር ሰው መሆን ፣ እምነቱን በተግባር የሚገልጽ እውነተኛ ክርስቲያን ሆኖ መገኘት ነው፡፡
2.2K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ