Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚ | 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖

የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚኽ እግዚአብሔር ስለ እመቤታችን ጥንታዊ የልደቷን አመጣጥ በየጊዜው ምልክት እንደሚሰጥ ልብ አድርገን ማስተዋል ይገባናል) በማለት አብራርተው ተርጒመዋል፡፡

❖ ሊቁ አባ ሕርያስቆስም በቅዳሴው በቊ ፴፪ ላይ "ተናግዶቱ ለአብርሃም" (የአብርሃም እንግድነቱ አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን ጠቅልሎ የገለጠውን ይኽነን ድንቅ ምስጢር፤ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ በስፋትና በጥልቀት፡-

"ወዓዲ ኀይመት ዘአብርሃም ዘውስቴታ ተአንገደ እግዚአብሔር አኮ ከማሁ ዘኮነቶ ምጽላለ በእንተ ምዕር አላ ኮነቶ እመ ወተከድነ ሥጋሃ ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ" (ዳግመኛም እግዚአብሔር (በሦስትነት) በዕንግድነት ያረፈባት የአብርሃም ድንኳን አንቺ ነሽ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ መጠለያን፣ መጠጊያን የኾነቺው አይደለም፤ እናትን ኾናው ሥጋዋን ተዋሕዶ ከመለኮቱ አንድ አደረገው እንጂ) በማለት በአብርሃም ድንኳን ብትመሰልም እንኳ ክብሯ ከፍ ያለ፤ ለዘላለም የአምላክ ማረፊያውና እናቱ መኾኗን አብራርቶ ገልጧል፡፡

❖ ሊቅነትን ከንግሥና ጋር ያስተባበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሥላሴ መጽሐፉ ላይ፦
"ኦ ብእሲ ዘትትከሓድ አይኑ ዕለት ለአግዚአብሔር ሰገዱ ሎቱ ምስለ መላእክቲሁ በዕሪና እምነ ኩሉ ፍጡራኒሁ..." (ሥላሴን የምትክድ አንተ ሰው ሆይ ከፍጡሮች ወገን በመላ እግዚአብሔርን ከመላእክቱ ጋር በአንዲት ዕሪና የሰገዱለት በማናቸው ዕለት ነው? በማናቸው ዕለት እግዚአብሔር ከፈጠራቸው መላእክቱ ጋር ተካክሎ እግሩን ታጠበ? በማናቸው ዕለት በሰው መጠለያ በታች ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ ተጠለለ? በማናቸው ዕለት ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ እግዚአብሔር በላ? በማናቸው ዕለት ከአዳም ልጆች ወገን ሰው ወደ ፈጣሪው በለመነ ጊዜ መላእክቱ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ተካክለው እንዲኽ አድርግ መቼ አሉ? አንተ ሥላሴን የካድኽ ከሓዲ ፍጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር በመተካከል እንዲሰገድላቸው ለምን ታመጣቸዋለኽ? ፈጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር ተካክለው በአብርሃም ቤት እንደተጠለሉ፤ እግራቸውን እንደታጠቡ፤ ዐብረው እንደበሉ አድርገኽ ለምን ታስተካክላለኽ? አንተ ከእኛ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የኾንኽ ክርስቲያን አንዱ እግዚአብሔር ነው፤ ኹለቱ መላእክት ናቸው አትበል) በማለት አስፍቶ ይጽፋል፨

❖በቤተ አብርሃም የገቡ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዘወትር በቤተ ልቡናችን ውስጥ ግቡልን፨❖
[ለበለጠ ምስጢር "መልክአ ሥላሴ ንባቡና ትርጓሜው" መጽሐፌን ያንብቡ]፨